2016-06-17 15:31:00

ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ፥ ቤተ ክርስቲያን አጥሮችን በማስወገድ ለቤተሰብ ቅርብ ትሁን


ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ እ.ኤ.አ. ሰኔ 16 ቀን 2016 ዓ.ም. በጳጳሳዊ ቅዱስ ዮሓንስ ዘላተንራኖ የሮማ ሰበካ የጠራው ዓመታዊ ቤተ ክርስቲያናዊ ጉባኤ በሰጡት ሥልጣናዊ ምዕዳን ማስጀመራቸው የቫቲካን ረዲዮ ልኡክ ጋዜጠኛ ፋብሪዚዮ ማስትሮፊኒ ገለጡ።

የሮማው ሰበካ ቤተ ክርስቲናዊ ጉባኤ የፍቅር ኃሴት በሚል ርእስ ሥር ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስ የደረሱት ሓዋርያዊ ምዕዳን መሠረት በማድረግ ቤተሰብ ርእስ ዙሪያ የሚመክር መሆኑ የገለጡት ማስትሮፊኒ አያይዘው፥ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራቸስኮ መሪ ቃል ለግሰው እንዳበቁም ከተጋባእያኑ ለቀረቡላቸው ጥያቄ መሰረት በሰጡት መልስ ምዕዳን የሰጡም ሲሆን፡ ይኸንን እ.ኤ.አ. ሰነ 19 ቀን 2016 ዓ.ም. የሚዘልቀው የሮማ ሰበካ ቤተ ክርስቲያናዊ ጉባኤ ሲያስጀምሩ፥

በአሁኑ ሰዓት እየተስፋፋ በመሄድ ላይ ያለው ምንጩም የበለጸገ ዓለም መሆኑ የሚነገርለት የጊዚያዊነት ባህል በጥልቀት በማብራራት፡ ጊዚያዊነት፡ ተጠቅሞ መጣል የሚለው ባህል ብቁና ተገቢ መልስ የማይሰጥ መሆኑ እየታየ ነው። ይኽ ባህል ሁሉንም ሰብአዊ ጉዳይ በመንካትም ይሁን ዘርፈ ብዙ ችግሮችንም በማስከተል ሁሉም በጊዚያዊነት ባህል እንዲጠቃና ዘላቂነት ከሚለው መሆናዊ እማኔ እያራቀው መሆኑ የገለጡት ቅዱስ አባታችን ከዚህ ጋር በማያያዝም ቤተ ክርስቲያን ከዚህ ዓይነቱ ባህል እራሷን ጠብቃ ልጆችዋን እንዲጠበቁ ታስተምራለች። ይኸንን ቤተሰብና የፍቅር ኃሴት በሚል ርእስ ሥር የሚካሄደው ቤተ ክርስቲያናዊ ጉባኤ ምስጢረ ተክሊል ቀጣይነቱ በቤተ ክርስቲያን ውስጥና በኅብረትሰብ ዘንድ ዋስትና ማግኘት ይኖርበታል፡ ስለዚህ ጋብቻ በቤተ ክርስቲያን ውስጥና በኅብረተሰብ ዘንድ ያለው ሚና ለይቶ ጋብቻ በገዛ እራሱ የማይዘጋ የሚያፈራ ያንን ብዙ ተባዙ የሚለው ጥሪ እግብር ላይ የሚያውል ነው። ይኸንን ጥሪ በእርግጠኝነት ለመኖር በጊዚያዊነት ባህል ከመጠቃት አደጋ መከላከል ያስፈልጋል፡ በጋብቻም ይሁን በገዳማዊ ሕይወትም ለመላ ሕይወት የሚል ማህላ ይፈጸማል፡ ጥሪ ነው፡ ነገር ግን ተጠቅሞ መጣልና የጊዚያዊነት ባህል በተስፋፋበት ዓለም ለመላ ሕይወቴ የሚል ማህላ የሚሰጠው ትርጉምና ግንዛቤው ምን ይሆን፡ ለዚህም ነው ብዙ ጊዜ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ የተፈጸሙ ጋብቻዎች መሻር የሚያፈልገው፡ ስለዚህ ከዚህ ጊዚያዊነት ከሚለው ባህል መፈወስ  ያስፈልጋል እንዳሉ ልኡክ ጋዜጠኛ ማስትሮፊኒ አስታውቀዋል።

ብዙዉን ጊዜ ሴቱቱ ነፍሰ ጹር በመሆንዋ ምክንያት ጋብቻው ተፋጥኖ ሲፈጸም ይታያል። ሆኖም ጋብቻ ሊስተዋልና ተገቢ ግንዛቤ ሊሰጠው ክርስቲያናዊ ትርጓሜውም በትክክል መገንዘብ ያስፈልጋል። ካልሆነ ጋብቻ በቀላሉ ላደጋ ይጋለጣል። ለጋብቻ የሚገፋፋው ቅዉም ነገር ላንድ ጋብቻ ዘላቂነትና መፈረካከስ ምክንያት መሠረት ነው፡ ስለዚህ ለጋብቻ የሚገፋፋው ምክንያት ማወቅ ማስተዋል ያስፈልጋል፡ ሚስጢረ ተክሊል ያለው ውበት ማሳወቅ የቤተ ክርስቲያን ግዴታ ነው፡ በቅድሚያም በአሁኑ ሰዓት እየተኖረ ያለው የጊዚያዊነት ባህል ዘላቂው ባህል በማስፋፋት መዋጋት ያስፈልጋል እንዳሉ የገለጡት ማስትሮፊኒ አያይዘው፥ የሚካሄደው ዓውደ ጉባኤ በወጣቶች መካከል የሚኖር ፍቅር፡ ለሚስጥረ ተክሊል የማሰናጃ ሕንጸት፡ ኃላፊነት ለበስ ጋብቻ፡ ታማኝነት፡ ሕይወት መስጠት ያለው ደስታ ቤተሰብና ወንድማማችነት በተሰኙት የውይይት ርእሶች ተሸኝቶ እየተካሄደ መሆኑ ያመለክታሉ። 








All the contents on this site are copyrighted ©.