2016-06-14 18:42:00

ር.ሊ.ጳ. ፍራንሲስ በሮም የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የዓለም የምግብ ፕሮግራም ይፋዊ ጉብኝትአድርገዋል


ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ ዛሬ ከቀትር በፊት እዚህ ሮም ውስጥ በሚገኘው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት  የዓለም የምግብ ፕሮግራም ይፋዊ ጉብኝትአድርገዋል። ቅድስነታቸው የዓለም የምግብ ፕርግራም ዋና ጽሕፈት ሲደርሱ የድርጅቱ ባለ ሙያዎች አቀባበል አድርግውላቸዋል።

የዓለም የምግብ ፕሮግራም ፈጻሚ አካል የዓመቱ አጠቃላይ ጉባኤ እያካሄደ መሆኑ እና በዚሁ አጋጣሚ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት የተባበሩት መንግስታት ዓለም አቀፉ የምግብፕሮግራም እንዲጐበኙ የፈጻሚ ካሉ ዳይረክተር ወይዘሮ ኮውሲን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳትን መጋበዛቸው በቫቲካን የተሰጠ መግለጫ አመልክተዋል። ቅድስነታቸው ለተደረገላቸው ጥሪ አመስገነው የዓለም የምግብ ፕሮግራሙ ከተመሰረተ ጀምሮ በ1962 እንደ ጎርጎርዮስ አቆጣጠር ጸር ርሃብ የሚያካሄደው ትግል አመስግነዋል።

በተለያዩ የዓለም ዙርያዎች ለርሃብ የተጋለጠ ህዝብ በሚልዮን እንደሚቆጠር ጠቅሰው እዚህ ሲገባ በድርጅቱ የሚገኘው ርሃብተኞችን ምግብ  ለመስጠት  ሕይወታቸው አሳልፈው ለሰጡ የዓለም የምግብ ፕሮግራም አባላት የመዘክር ግድግዳ መጸለያቸው አመልክተው ርሃብን ለመግታት ብሎም ለማምከን የሚደረገው ጥረት ቀጣይ እና ስኬታማ እንዲሆን ተስፋ እንደሚያደርጉ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ባሰሙት ቃል አስገንዝበዋል። አንድ ተቋም በሚሰጠው መግለጫዎች ሳይሆን በተግባሩ እንደሆነ ያመለከቱ ቅድስነታቸው ተግባሩም የሙያው ምስክር እንደሆነ አመልክተዋል።

ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ በማያያዝ ርሃብ ጸጸር ሰላም ሰብአዊ ኑሮን የሚያቃውስ አደገኛ መሆኑ ጠቅሰው ርሃብ መከሰቱ መናገር ሳይሆን ለመጨቱ ሌተ ቀን ጥረት ማካሄድ እንደሚሻ አሳስበዋል። ሰብአዊ ማሕበራዊ ተክኒካዊ እና ኤኮኖምያዊ እድገት ሰዎች ማሕበረ ሰቦች እና ህዝቦች ርሃብን ለመግታት እና ብሎም ለመቅጨት መንገድ እንደሚከፍታላቸው በማያያዝ ገልጠዋል።

ለሚራቡ የዓለም ህዝቦች ርዳታ መስጠት ብቻ ሳይሆን የእድገት መሳርያዎች መስጠት እና ማስተማር ራሳቸው ርሃብን ለመታገል የሚያስላቸው ተክኒክ ማስተማር የግድ መሆኑ ጠቁመው የዓለም የምግብ ፕሮግራም ተፈጥሮአዊ እና ሰው ሰራሽ  ችግሮች በመሻገር ለተራበ የህዝብ ዓለም የሚሰጠው ሰብአዊ ርዳታ ሊመስገን ይገባል ሲሉም ንግግራቸው በማያዝ አስገንዝበዋል።

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የምግብ ፕሮግራም 14ሺ ባለ ሙዎች ያሉት በተለያዩ ምክንያቶች በድርቅ በተፈጥሮአዊ መቅሰፍ የርሃብ ሰለባ ለሚሆኑ ሰብአዊ ርዳታ የሚለግስ  መሆኑ ይታውቃል። ለድርጅቱ ባለ ሙያዎች እና ቤተ ሰቦች ከሃኤ ኩሉ እግዚአብሔር መለከኮታዊ ቡራኬ  ይስጣችሁ እንድትጸልዩልኝ እማጸናችሁለሁ እግዝአብሔር ይስጥልን በማለት ንግግራቸውን አጠቃልለዋል።

አንድ የቅድስት ካቶሊካዊት ቤተ ክርስትያን ርእሰ  ሊቃነ ጳጳሳት የተባበሩት መንግስታት የምግብ ፕሮግራም ድርጅት ሲጐበኙ ይህ  ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ ዛሬ ረፋድ ላይ ያካሄዱት ጉብኝት የመጀመርያ ግዜ መሆኑ ይታወቃል።

በሌላ በኩል ደግሞ በቅድስት መንበር የፍትሕና ሰላም ጳጳሳዊ ምክር ቤት ሊቀ መንበር ብጹዕ ካርዶናል ፒተር ታክሰን ርሃብ ከመሰረቱ ካልተወገደ ሰብአውነት በሰላም ለመኖር አዳጋች መሆኑ ስለሆነም ርሃብን ለመግታት የሁሉም መረባረብ እንደሚጥይቅ መግለጫ ሰጥተዋል። ትብብር አለመኖር እና ከስስት አለመላቀቅ  የርሃብ ጠንቅ መሆናቸውም በማያዝ አመልክተዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.