2016-06-13 15:35:00

የብፅዕና አዋጅ


በኢጣሊያ ሲችሊያ ከፍለ ሃገር በሚግኝው በሞንረአለ ካቲድራል እ.ኤ.አ. ሰኔ 11 ቀን 2016 ዓ.ም. ከሰዓት በኋላ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮን በወከሉት የቅድስና ጉዳይ በሚከታተለው ቅዱስ ማኅበር ኅየንተ ብፁዕ ካርዲናል አንጀሎ አማቶ በሲቺሊያ ክፍለ ሃገር ብፁዓን ጳጳሳትና ከብራዚል ከአልባኒያ ከመክሲኮ ከማዳጋስካር ማለትም የማኅበሩ ደናግል በወንጌላዊ ልኡክነት ተሰማርተው አገልግሎት ከሚሰጡባቸው አገሮች በተወጣጡ ብፁዓን ጳጳሳት ታጅበው በመሩት መሥዋዕተ ቅዳሴ ለእግዚአብሔር አገልጋይ የካፑቺን የንጽሕት ቅድስት ድንግል ማርያም ዘሉርድ ደናግል ማኅበር መሥራች እናቴ ማሪያ ዘኢየሱስ ሳንቶካነናለ ብፅዕና እንደታወጀላቸው የቫቲካን ረዲዮ ልእክት ጋዜጠኛ ማሪና ታማሮ ገለጡ።

እኚህ ብፅዕና የታወጀላቸው በፓሌርሞ ከተማ እ.ኤ.አ. ጥቅምት 2 ቀን 1852 ዓ.ም. ካንድ ሃብታም ቤተሰብ የተወለዱ በዚያ ፖለቲካዊ ማኅበራዊ ሥር ነቀላዊ ለውጥ ይታይበት በነበረው ወቅት በዓለማዊ ነገር ሳይሳቡ በቁምስናቸው ንቁ ተሳታፊ በመሆን በማገልገል ላይ እያሉ በ1887 ዓ.ም. ወደ ከተማ ቺኒዚ ከወላጆቻቸው ጋር ከተዛወሩም በኋላ በቁምስና ትምህርተ ክርስቶስ በማስተምር በግብረ ሠናይ አገልግሎት ተሰማርተው በማገልገል ላይ እያሉ፥ በዚያኑ ዓመት የፍራንቸስካውያን ካፑቺን ሥርዓት በመከተል የምንኩስን ልብስ በማጥለቅ መላ ሕይወታቸውን ለወንጌል አገልግሎት ማዋል እንደጀመሩ የታሪክ ማህደራቸውን ዋቢ ያደረጉ ታማሮ ያመለክታሉ።

እኚሕ ብፅዕና የታወጀላቸው የካፑቺን የንጽሕት ቅድስት ድንግል ማርያም ዘሉርድ ደናግል ማኅበር መሥራች ከእግዚአብሔር የተሰጣቸው ኵላዊት ቤተ ክርስቲያን እውነት ነው ያለቸው መንፈሳዊ ዓላማ በገዳማዊ ሕይወት ለመኖር የተከተሉት መንገድ የማረካቸው እግዚአብሔር በጠራቸው አባላት ቁጥር ከፍ እያለ ድኾችን ከትምህርት ገበታ የተገለሉትን ህሙማንን በማገልገል ያንን ብፅዕት ማሪያ ዘኢየሱስ የተቀበሉት መንፈሳዊ ተልእኮ በመኖር እኚህ ብፅዕት ለቅድስት ድንግል ማርያም ዘሮዛርየም የነበራቸው ፍቅር በመመስከር ቤተ ክርስቲያንና ሕዝበ እግዚአብሔርን እያገለገሉ እንደሚገኙም ብፁዕ ካርዲናል ኣማቶ የብፅዕና አዋጅ መሥዋዕተ ቅዳሴ መርተው ባሰሙት ስብከት ገልጠው፥ ብፅዕት ማርያ ዘኢየሱ ለማኅበሩ ደናግሎችም በእግዜብሔር ፍቅር መራመድ ብቻ ሳይሆን ከፍ ብሎ መብረር ያስፈልጋል፡ እግሮቻቸውን በመሬት ልባቸውም በእግዝአብሔር ዘንድ በማኖር በዚያ ወሰን በሌለው ፍቅር ሁሉንም  በማፍቀር እንዲያገለሉ አደራ ይሉ እንደነበርም የታሪከ ማኅደራቸውን ጠቅሰው በማብራራት፥ ከኢየሱስ ጋር የተገናኘ በሌሎች የሚገለጠውን ኢየኡስን ለማገልገል የተጋ ይሆናል እንዳሉ ታማሮ ያመለክታሉ።








All the contents on this site are copyrighted ©.