2016-06-13 15:23:00

ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ፥ ሕይወት ጉዞ ነውና አደራ በቁም ተራመድ እንዳይሆን


በኢጣሊያ ከማቸራታ ከተማ ተነስቶ ወደ ሎረቶ ማርያማዊ ቅዱስ ሥፍራ የሚደረገው 28 ኪሎ ሜትር የሚያጠቃልለው የሰላም የእግር ጉዞ ምክንያት ቅዱስ ኣባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ እ.ኤ.አ. ሰኔ 11 ቀን 2016 ዓ.ም. “ካለ መራመድ መኖር አይቻልም” የሚል ቅዉም ሃሳብ ማእከል ያደረገ የስልክ መልእክት በማስተላለፍ ለእነዚያ የዘንድሮ የሰላም የእግር ጉዞ ተሳታፍያንን እንዳበረታቱ የገለጡት የቫቲካን ረዲዮ ልእክት ጋዜጠኛ ሮበርታ ባርቢ አያይዘው፥ የአንኰናና ኦዚሞ ሰበካ ሊቀ ጳጳሳት ብፁዕ ካርዲናል ኤድዋርዶ መኒከሊ ባሳረጉት መሥዋዕተ ቅዳሴ ተባርኰ ወደ ተጀመረው የሰላም የእግር ጉዞ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ባስተላለፉት መልእክት፥ ሕይወት ጉዞ ነውና አደራ በቁም መራመዱ ይቅር። ሁሌ እንጓዝ። እኔም በቁም የሚራመድ እንዳልሆን ሁሌ እራመድም ዘንድ ስለ እኔ ጸልዩ” እንዳሉ ያመለክታሉ።

ሕይወት ማኅበራዊ ወዳጅነት ቅን ኅብረትሰብ ለመገንባት የተጠራ ነውና ይኽንን ለማረጋገጥ የሚቻለውም ሕይወት ጉዞ መሆንን ስንገነዘብ ነው። ስለዚህ ለሰው ልጅ  መልካምነት መጓዝ ያስፈልጋል፡ የኢየሱስን ወንጌል ለማወጅ መራመድ መጓዝ ያስፈልጋል ያሉት ቅድስ አባታችን በዚህ የዛሬ 38 ዓመት በፊት በተጀመረው ከማቸራታ እስከ ሎሬቶ በሚካሄደው የሰላም የእግር ጉዞ ተሳታፍያን ጉዞአቸውን ምንም’ኳ አድካሚ ቢሆንም ቅሉ የጸሎት የአስተንትኖ የኃሴት ጉዞ በማድረግ በቅዱስ ቁርባን ከሚገለጠው ኢየሱስ ክርስቶ ጋር ለመገናኘ የሚከወን ነውና የተስፋ ጉዞ ይሁንላችሁ ብለው ሁሉንም ተሳታፋንን ባርከው፡ ሰላም ለኪ ጸሎት መድገማችውም ሮበርታ ባርቢ ገለጡ።

የዘንድሮው የሰላም የእግር ጉዞ መርሆ “አንተ ልዩ ነህ” የሚል ሲሆን። ጌታችን ልዩ ነው የእርሱ ትከታይ የሆኑትም ልዩ መሆናቸው የሚያስገነዝብ መርሆም ሲሆን። ምንም’ኳ እ.ኤ.አ. ሰኔ 11 ቀን 2016 ዓ.ም. ሌሊት ኃይለኛ ዝናብ ቢዘንብም መንፈሳዊ ነጋዲው በዚህ ሳይገታ አየጸለየ እየዘመረ ባደረገው ጉዞ ቅዱስ አባታችን ባስተላለፉት መልእክት ዝናብ የእግዚአብሔር ጸጋ ነው ብለው፡ የእግዚአብሔር ጸጋ ልክ እንደ ዝናብ ነው፡ በእኛ ላይ የሚፈስ ጸጋው ውስጣችንን እኛነታችንን ያረሰርሳል እንዳሉ ባርቢ አስታውቀዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.