2016-06-10 15:21:00

የ “ይሴባሕ” ዓዋዲ መልእክት ሳምንት


የካቶሊክ ሥነ ምኅዳር ዓለም አቀፍ እንቅስቃሴ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮ ይሲባሕ በሚል ርእስ ሥር የደረሱት ዓዋዲ መልእክት ዝክረ አንደኛው ዓመት ምክንያት ያነቃቃው የይሴባሕ ሳምንት እ.ኤ.አ. ከሰነ 12 ቀን እስከ ሰነ 19 ቀን 2016 ዓ.ም. እንደሚካሄድ እንቅስቃሴ ያሰራጨው መግለጫ የጠቀሱ የቫቲካን ረዲዮ ልእክት ጋዜጠኛ ሊዛ ዘንጋሪኒ አስታወቁ።

በብዙ ሺሕ የሚቆጠሩ ቁምስናዎች ሰበካዎች ካቶሊካውያን ማኅበረሰብ ይኸንን የይሴባሕ ሳምንት ያንን ሰብአዊ ፍጡር የተፈጥሮና የፍጥረት ተንከባካቢ የሚለው ጥሪውን የሚያጎላ ሥነ ምኅዳር ጥበቃና እንክብካቤ ዙሪያ የተለያዩ ዓውደ ጥናቶች ትርኢቶች ከወዲሁ ማሰናዳታቸውና በተለይ ደግሞ ምሉእና የተወሃደ ምኅዳር በሚል ቅውሙ ሃሳብ ቅዱስ አባታችን በዓዋዲው መልእክታቸው ያያብራሩት ሃሳብ በሁሉም ሰው ዘር እንዲሰርጽና ሁሉም ስለ ጉዳዩ እንዲያስተውል ለማድረግ የሚያግዙ መርሃ ግብሮች መወጠናቸው የእንቅስቃሴውን መግለጫ የጠቀሱት የቫቲካን ረዲዮ ልእክት ጋዜጠኛ አያይዘው፥ ፍጥረትንና ተፈጥሮን እንንከባከብ ዘንድ መጽሓፍ ቅዱስ የሚያሳስበው ቃለ ላይ ያተኰረ የጸሎት ያስተንትኖ መርሃ ግብሮች ጭምር እንደሚካሄድ ያመለክታሉ።

የእንቅስቃሴን ላውዳቶሲዊክ ነጥብ ኦርግ በተሰየመው ይፋዊ ድረ ገጹ ላይ ሰፍሮ እንደሚገኝም ይሴባሕ ዓዋዲ መልእክት በማስደገፍ ወቅታዊው የምኅዳር ተጨባጭ ሁኔታ የሚዳስስ ዓውደ ጥናት እንደሚካሄድ ሲታወቅ። የጳጳሳዊ የሥነ ማኅበራዊ ተቋም ዋና እስተዳዳሪ ብፁዕ አቡነ ሳንቸስ ሶሮንዶና በኮሎምቢያ መንበረ ጥበብ የሥነ ማኅበራዊ ዘርፍ ተመራማሪ የጥበባዊ መጻሕፍት ደራሲ የመንበረ ጥበቡ የሥነ መሬት የምርምር ጥናት አስተዳዳሪ ፕሮፈሰር ጀፍረይ ሳችስና ሌሎች የሥነ ምኅዳር ሊቃውንት አበይት አካላትና ምሁራን በመሥመር ላይ የሚያሳፍ ውይይት እንደሚካሄድም ለማወቅ ተችሏል።

ይኽ የይሴባሕ ሳምንት በፊሊፒንስ እጅግ ሰፊና ጥልቅ በሆነ መልኩ ምእመናን ኣቢያተ ክርስትያን በአገሪቱ የሚገኙት መናብርተ ጥበብ ሰበካዎች ምሁራን የሚያሳትፍ መርሃ ግብር የተሰናዳም ሲሆን በተለይ ደግሞ ማኒላ በሚገኘው የካቶሊክ ቅዱስ ቶማስ መንበረ ጥበብ እ.ኤ.አ. ሰኔ 18 ቀን 2016 ዓ.ም. ይሴባሕ ዓዋዲ መልእክት ሥር ትርኢት ውይይትና ዓውደ ጥናት እንደሚካሄድም የእንቅስቃቄው መግለጫ የጠቀሱት ልእክት ጋዜጠኛ ዘንጋሪኒ አስታወቁ።








All the contents on this site are copyrighted ©.