2016-06-08 16:31:00

የካቶሊክ ትምህርት ተንከባካቢ ቅዱስ ማኅበር ኅየንተ በታይዋን


በታይፐ የሚገኘው ካቶሊካዊ ፉ ጀን መንበረ ጥበብ እ.ኤ.አ. ግንቦት 27 ቀን 2016 ዓ.ም. “ሦስት ሺሕኛው ዓመት፡ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ከተለያዩ ባህሎች ጋር ያላት ተግባቢነት” በሚል ርእስ ሥር አሰናድቶት በነበረው ዓውደ ጥናት የካቶሊካዊ ትምህት ተንከባካቢ ቀዱስ ማኅበር ኅየንተ ብፁዕ ካርዲናል ጁሰፐ ቨርሳልዲ መንበረ ጥበቡ ባቀረበላቸው ጥሪ መሠረት በመሳተፍ ሁለተኛው የቫቲካን ጉባኤና የቅዱስ ጴጥሮስ ተከታይ ሥልጣናዊ ትምህርት መሠረት በማድረግ የቤተ ክርስቲያን ቀዳሚው ተልእኮ አስፍሆተ ወንጌል መሆኑ በማስታወስ ይኸንን ተልእኮ በተለያዩ ባህሎች ውስጥ በመኖር ባህሎች እንዲሰበኩ በማድረግ የቤተ ክርስቲያን ተልእኮና ባህሎች በማገናኘት የሚከወን መሆኑ በስፋት እንዳብራሩና። በክልል የሚገኙት ካቶሊካውያን አቢያተ ክርስቲያን በሚገኙበት ሕዝብ ባህል የዚያን ሕዝብ ቋንቋ የሚናገሩ ናቸው። ስለዚህ በዚህ ረግድም ያንድ ሕዝብ ባህል ቋንቋ ልምድ ዕለታዊ ኑሮ ጭምር በጥልቀት በመኖር በወንጌል እየሰበከች የቤተ ክርስቲያን ኵላዊነት መስካሪያን ይሆናሉ እንዳሉ ሎ ሶርቫቶረ ሮማኖ የተሰየመው የቅድስት መንበር ዕለታዊ ጋዜጣ እ.ኤ.አ. ሰነ 7 ቀን 2016 ዓ.ም. ባወጣው ኅትመቱ አስነብቧል።

እ.ኤ.አ. ግንቦት 28 ቀን 2016 ብፁዕ ካርዲናል ቨርሳልዲ የቅዱስ ሮበርቶ በላርሚኖ የቲዮሎጊያ መንበረ ጥበብ እ.ኤ.አ ግንቦት 29 ቀን 2016 ዓ.ም.  ደግሞ በታይቹንግ የሚገኘውን መለኮታዊ ጠባቂ መንበረ ጥበብ ጎብኝተው ከመንበረ ጥበቡ አስተማሪዎችና ተማሪዎች ጋር ተገናኝተው የሚሰጠውን ቲዮሎጊያዊ ሰብአዊና መንፍሳዊ ሕንጸት አድንቀው ካበረታቱ በኋላ፡ በዚያኑ ዕለት ከሰዓት በኋላ በታይዋን በተካሄደው ብሔራዊ የቅዱስ ቁርባን ጉባኤ ተገኝተው የቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. መልእክትና ቡራኬ እንዳቀረቡ የገለጠው የቅድስት መንበር ዕለታዊ ጋዜጣ አክሎ እ.ኤ.አ. ግንቦት 30 ቀን 2016 ዓ.ም.  የአገሪቱ ብፁዓን ጳጳሳት ካህናትና ዲያቆናት እንዲሁም ከምእመናን ጋር ተገናኝተው የቅዱስ ጴጥሮስ ተከታይ መልእክት አስተላልፈው የካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ትምህርት ትርጉምና ዓላማውና የሚከተለው አርአያም ትስብእት መሆኑ በጥልቅት የሚያብራራ አስተምህሮ በመስጠት ይፋዊ ሐዋርዊ ጉብኝታቸውን እንዳጠቃለሉ አስታውቋል።    








All the contents on this site are copyrighted ©.