2016-06-08 16:26:00

ሃገረ ቫቲካን፥ ዓለም አቀፍ የተኃዳሲያን አቢያተ ክርስቲያን የአንድነት ጉባኤ ልኡካን


እ.ኤ.አ. ሰኔ 10 ቀን 2016 ዓ.ም. የዓለም አቀፍ የተኃዳሲያን አቢያተ ክርስቲያን ውህደት ልኡካን ከሮማዊት ካቶሊካዊ ቤተ ክርስቲያን ጋር ያለውን ግኑኝነት በጥልቀት ለማጤን በሚል ዓላማ ተመርቶ በአገረ ቫቲካን ይፋዊ ጉብኝት እንደሚያካሄድ የቫቲካን ረዲይ ልእክት ጋዜጠኛ ኢዛበላ ፒሮ ገልጠው ይኽ አገረ ቫቲክንን የሚጎበኘው የተኃዳሲያን አቢያተ ክርስቲያን ውህደት ጉባኤ ልኡካን በጉባኤው ሊቀ መንበር ጀርይ ኢላይና በጠቅላይ ዋና ጸሓፊ ክሪስ ፈራጉሶን ተመርቶ ከቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ከተገናኘ በኋላ ቀጥሎ ከተለያዩ የአብያተ ክርሲያን ውህደት ከሚያነቃቃው ጳጳሳዊ ምክር ቤትና ከጳጵሳዊ የፍትኅና ሰላም ምክር ቤት ጋርም እንደሚገናኙም አስታውቀዋል።

ይህ የውኅደቱ ጉባኤ ከካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ጋር በጳጳሳዊ የክርስቲያኖች ውህደት በሚያነቃቃው ምክር ቤት አማካኝነት የቆየው ግኑኝነት እዳለውም ያ “ድኅነትና ቅዱሳት ሚሥጢራት፡ ማኅበረ ክርስቲያን ለፍትኅ ዋነኛ መገልገያ” በሚል  ርእስ ሥር ያካሄደው የጋራው ውይይት መሠረት በማድረግ የዚህ የጋራው ውይይት የማጠቃለውያው ሰነድ ውይይቱ ባካሄደበት ርእስ ሥር ተጠናቅሮ በቅርቡ ለንባብ የሚበቃው ምስክር መሆኑ ያስታወሱት ልእክት ጋዜጠኛ ፒሮ በማስከተል፥ የኅዳሲያውያን አቢያተ ክርስቲያን ውህደት ጉባኤ ከተለያዩ አቢያተ ክርስቲያን ውህደት የሚያነቃቃው ጳጳሳዊ ምክር ቤት ጋር ያለው ግኑኝነት የቆየ ለመሆኑ በአክራ እ.ኤ.አ. በ 2004 ዓ.ም. የተካሄደው በጋራ ዓውድ ጉባኤ ፍጻሜ የማኅበራዊ ፍትኅ ቲዮሎጊያ በሚል ርእስ ያጸደቀው የጋራው ሰነድ በዋነኛነት ለመጥቀስ እንደሚቻል ገለጠው፡ ያ የጋራው ሰነድ ኤኮኖሚያዊ ፍትኅና ሥነ ምኅዳር የሚመለከቱ ጥያቄዎች ማኅበራዊ ፖለቲካዊና ግብረ ገባዊ ርእሰ ነግሮች ሥር መመልከት ብቻ ሳይሆን በኢየሱስ ክርስቶስ ላይ ከሚኖረው እምነት ተሟይነት ያለው መላ ቤተ ክርስቲያንን የሚመለከት ነው ሲል ያሰፈረው ነቢያዊ ሃሳብ የሁለቱ አቢያተ ክርስትያን ግኑኝነት ጥልቅ መሆኑ የሚመስክር ነው ብለዋል።

የጉባኤው ልኡካን ከቅዱስ አባታችን ጋር በሚያካሂዱት ግኑኝነትም ቅዱስነታቸ በደረሱዋቸው ወንጌላዊ ኃሴት ሐዋርያዊ ምዳንና ይሴባሕ ዓዋዲ መልእክት ያስደገፍ የሃሳብ ልውውጥ እንደሚደረግ ኢዛበላ ፒሮ ከወዲሁ በማስታወስ የኅዳሲያውያን አቢያተ ክርስቲያን ጉባኤውን በመከል በግኑኝነት የሚሳተፉት የጉባኤው ሊቀ መንበር መጋቤ ጀርይ ፊላይ፡ ጠቅላይ ዋና ጸሓፊና የጉኤው የፍትህ ምክር ቤት ተጠሪ መጋቤ ክሪስ ፈራጉስት፡ የቲዮሎጊያ ነክ ጉዳይ ለጉባኤው አማካሪ መጋቤ ዶራ አርሰ ቫለንቲን አሩና ግናዳሶን፡ የፕረስቢተሪያን አቢያተ ክርስቲያን የላቲን አመሪካና ካሪቢያን የኅዳሴ አቢያተ ክርስቲያን ቃል ኪዳን ሊቀ መንበር ኤልደር ጋብሬላ ሙልደር፡ የቫልደዝ አቢያተ ክርስቲያን የጋራ ውይይት መሪ መጋቤ ኤውጀንዮ በርናርዲኒ፡ የዓለም አቀፍ የኅዳሴ አቢያተ ክርስቲያን የአንድነት ጉባኤ የግኑኝነት ጉዳይ ምክር ቤት ተጠሪ ፊል ታኒስ መሆናቸው ያመለክታሉ።








All the contents on this site are copyrighted ©.