2016-06-07 13:46:00

ቅዱስነታቸው "የተራራው ስብከት ውስጥ የተጠቀሱ እሴቶች ክርስቲያኖች በእውነታኛው የሕይወት ጎዳና ላይ እንዲራመዱ ይረዳል" አሉ።


ቅዱስ አባታችን ፍራንቸስኮ ዘወትር ጥዋት በቅድስተ ማርታ የጸሎት ቤት መስዋዕተ ቅዳሴን እንደ ሚያሳርጉ የሚታወቅ ሲሆን በትላንትናው እለት ማለትም በግንቦት 29/2008 ካህናት፣ ደናግላን እና ምዕመናን በተገኙበት ባሰሙት ስብከት ክርስቲያኖች በተራራው ስብከት የተገለጹትን እሴቶች በመከተል  ስግብግብነትን፣ ትዕቢትን እና እራስ ወዳድነትን ማስወገድ ይጠበቅባቸዋል ማለታቸው ተገለጸ።

በእለቱ ከማቴዎስ ወንጌል ከምዕራፍ 5: 1-12 በተወሰደው እና የተራራው ስብከት ተብሎ በሚታወቀው ላይ በመመስረት ስብከታቸውን የጀመሩት ቅዱስነታቸው በተራራ ስብከት ውስጥ የተጠቀሱት ነጥቦች ክርስቲያኖች በክርስትና ሕይወት ጉዞዋቸው በትክክለኛ መንገድ ላይ “ይራመዱ” ዘንድ ብርሃንን በሚፈነጥቅላቸው እሴቶች የተሞሉ መሆናቸውን ገልጸዋል።

በእዚሁ የተራራው ስብከት ላይ ያጠነጠን ስብከታቸው ቅዱስነታቸው እንደ ገለጹት “ኢየሱስ በእለቱ ያደርገው አስተምህሮ የብሉይ ኪዳንን ህግ የሻረ ሳይሆን በአንጻሩ ወደ ፍጹምነት እና ወደ ሙላት ያደረሰው” መሆኑን ገልጸው “ይህ ጌታ የሰጠን አዲሱ ህግ ብለን የምንጠራው ደግሞ የተራራው ስብከት ነው” ካሉ ቡኋላ ይህ አዲሱ ህግ ደግሞ የክርስቲያን የሕይወት መንገድ አቅጣጫን በመጠቆም በትክክለኛው ጎዳና ላይ ወደ ፊት ይራመዱ ዘንድ የሚረዳቸው አቅጣጫ ጠቋሚ ህግ መሆኑን ገልጸዋል።

በተመሳሳይ ይዘት በሉቃስ ወንጌል ውስጥ የተጠቀሰውን የተራራው ስብከት ከግንዛቤ በማስገባት እና አራት ጊዜ የተጠቀሰውን “ወዩላችሁ!” በሚለው ቃል ላይ አስተያየት በመስጠት ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው “እናንተ ሀብታሞች ወዩላችሁ! አሁን ይጠገባችሁ ወዩላችሁ! አሁን የምትስቁ ወዩላችሁ! ሰዎች ሁሉ ስለ እናንተ መልካም ሲናገሩላችሁ ወዩላችሁ! (ሉቃ. 6,24-26) የሚለውን ከጠቀሱ ቡኋላ ሀብት በእራሱ ጥሩ ነገር መሆኑን ብዙ ጊዜ መናገራቸውን አስታውሰው ክፋቱ ግን አሉ ቅዱስነታቸው “ከሀብት ጋር መጣበቅ” መሆኑን ገልጸው ይህም ጣዖት እንደ ማምለክ እንደ ሚቆጠር ገልጸዋል።

“ይህም ፀረ-ህግ እና የተሳሳተ የሕይወት ቀዘፋ ነው። የተራራው ስብከት እሴቶች ወደ ሕይወት ጎዳና የሚወስደዱን ሲሆን ሦስቱ የምያንደላጥጡ እርምጃዎች ግን ወደ ዘላለማዊ ቅጣት የሚወስዱን ናቸው” ብለው እነዚህም ወደ ዘላለማዊ ቅጣት የሚመሩን ነገሮች በቅድሚያ “ከሀብታ ጋር መጣበቅ ወይም መቆራኘት. . . .ምክንያቱም ምንም አያስፈልገኚም” በማለት ሦስቱን ወደ ዘላለማዊ ቅጣት የሚወስዱትን ነገሮች ቀዳሚውን  በመጥቀስ የቀጠሉ ቅዱስነታቸው፣ በሁለተኛ ደረጃ የሚጠቀሰው ደግሞ “ግብዝነት (እብሪት). . .ሁሉም ስለ እኔ ጥሩ ነግሮችን ብቻ መናገር አለባቸው፣ አስፈላጊ ሰው እንደ ሆንኩኝ ሊሰማቸው ይገባል፣ ሁሉም በጣም ልጠነቀቁልኝ ይገባል. . .እና እኔ ሁል ጊዜ ትክክለኛ መሆኔ እርግጠኛ ነኝ” የሚለው ሁለተኛው ሲሆን እራሱን ያመጻደቀውን የፈሪሳዊው ሰው እና የግብር ሰብሳቢ የነበረውን እራሱን እንደ ኋጥያተኛ ይቆጥር የነበረውን ሰው ምሳሌ ዋቢ በማድረግ ቅዱስነታቸ እንደ ገለጹት “አምላኬ ሆይ: እንደ እዚህ ባልንጄራዬ ሳይሆን ጥሩ ካቶሊክ ስላደረከኝ አመሰግንሀለው!” የሚለው አስተሳሰብ እንደ ማያዋጣ ጨምረው ገልጸዋል።

“ሦስተኛው ኩራት ነው” ያሉት ቅዱስነታቸው “ኩራት ጥጋብ እና ልብን የሚዘጋ ደስታ” መሆኑን ገልጸዋል። ከተራራው ስብከት እሴቶች ውስጥ ከሁሉም የሚበልጥ እና ለየት ያለ አንድ እሴት ይገኛል በማለት ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው “ይህም የሁሉም ቁልፍ የሆነ  ቃል ነው እያልኩኝ ሳይሆን፣ ነገር ግን ማሰላሰል እንድንችል ያነሳሳናል ይሄውም የዋህነት ወይም ገርነት” መሆኑን ገልጸዋል።

“ኢየሱስ ስለ እራሱ እንዲህ ብልዋል: ‘ከእኔ ተማሩ፣እኔ በልቤ የዋህና ትሑት ነኝና’። የዋህ መሆን ወደ ኢየሱስ የሚያቀርበን ትክክለኛው መንገድ ነው” ብለዋል። “የእዚህ ተቃራኒ አመለካከት” አሉ ቅዱስነታቸው በስብከታቸው ማጠቃልለያ ላይ “ሁሌ ጥላቻን እና ጦርነትን. . .እንዲሁም ብዙ መጥፎ ነገሮችን ያስከስታል። ነገር ግን የዋህነት፣. . . የልብ የዋህነት ሞኝነት ማለት ግን አይደለም ሌላ ትርጉም አለው፣ ወደ ውስጥ ሰርጾ የመግባት ችሎታ፣ የእግዚአብሔርን ታላቅነት መገንዘብ እና እርሱን ማምለክ” መሆኑን ገልጸው ስብከታቸውን አጠቃለዋል።

 








All the contents on this site are copyrighted ©.