2016-06-06 16:46:00

ቅዱስ አባታችን የአለማውያን ምእመናን የቤተሰብና የሕይወት ጉዳይ ተንከባካቢ ጳጳሳዊ ምክር ቤት ቅዋሜ አጸደቁ


የቅዱስ ጴጥሮስ ተከታይ ተባባሪ የበላይ ሓዋርያዊ መሥተዳድራዊ መዋቅሮች ኅዳሴ እንዲደርግ በዚሁ ሂደት የሚተባበሩዋቸው ዘጠኝ ካርዲናሎች ያቀፈው ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ያቆሙት የኅዳሴ ድርገት ባቀረበላቸው ሃሳብ መሠረት  እ.ኤ.አ. ግንቦት 28 ቀን 1988 ዓ.ም. በሐዋያዊ መልካም እረኛ ሕግ መንግሥት አማካኝነት ሕጋዊ ቅዋሜ ያገኙት  የዓለማውያን ጉዳይ የሚንከባከበው ጳጳሳዊ ምክር ቤትና የቤተሰብ ጉዳይ ተንከባካቢ ጳጳሳዊ ምክር ቤት እ.ኤ.አ. ከመስከረም 2016 ዓ.ም. በአንድ ላይ የሚጠረንፈው የዓለማውያን ምእመናን የቤተሰብና የሕይወት ጉዳይ የሚከታተለው ጳጳሳዊ ምክር ቤት በሚል መለያ አንድ ሐዋርያዊ ሥልጣን እንድቆም የሚለው ውሳኔ ማጽደቃቸው የቅድስት መንበር የዜናና ኅትመት ክፍል መግለጫ አመለከተ።

ይኽ በአንድ ኃየንተና ተባባሪ ዋና ጸሓፊ ሥር የሚመራው አዲሱ ሐዋርያዊ ሥልጣን ዋና ጸሓፊው ሌሎች ሦስት ምክትል ዋና ጸሓፍት የሚኖሩትና እነዚህ ምክትል ዋና ጸሓፍቱም ከተለያዩ የዓለማችን ክልል የተወጣጡ ዓለማውያን ምእመናን ገዳማውያውን ጭምር ሊሆኑ እንደሚችሉም የገለጠው የቅድስት መንበር የዜናና ኅትመት ክፍል መግለጫ አክሎ፥ ይኽ አዲሱ ሓዋርያዊ የኅየንተሥልጣን ሥር የሚተዳደረው መዋቅር ጥሪ የዓለማውያን ተልእኮ በቤተ ክርስቲያንና በዓለም የሚያነቃቃ በጳጳሳዊ ሥልጣናዊ ትምህርትና ውሳኔ በመመራት የቤተሰብ ሐዋያዊ ግብረ ኖልዎ የሚንከባከብ የሚመራ በሚሥጢረ ተክሊል ላይ የተመሰረተው ቤተሰብና ይኽ ሚሥጢር ያለው ክብር በማጉላት የቤተሰብ በቤተ ክርስቲያንና በማኅበራዊ ሕይወት የሚኖረው አስተዋጽኦ ከማነቃቃትም አልፎ ተገቢ እውቅና እንዲኖረው የሚያነቃቃ ከዚያ ሚሥጢረ ተክሊል ቤተሰብና ሕይወት ከሚያነቃቃው በዮሓንስ ጳውሎስ ዳግማዊስ የሚጠራው የሚሥጢረ ተክሊልና የቤተሰብ ጳጳሳዊው ተቋም ጋር ቀጥተኛ ግኑኝነት ያለው መሆኑ አስታውቀዋል።

የኵላዊት ቤተ ክርስቲያን ግብረ ገብ ትምህርት የካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ሥልጣናዊ ትምህርቶች ላይ የጸና የተለያዩ ጥናቶችና ምርምሮችን በማነቃቃት በዚሁ ዘርፍ የሕንጸት መርሃ ግብሮችንም በመወጠን የሥነ ሕይወት ጥናትና በዚሁ የጥናት ዘርፍ የሚቀሰቀሱት ችግሮች የሕይወት ባህል ሕይወት ከመጸነስ እስከ ባህርያዊ ሞት እቃቤ በሰው ልጅ ሕይወት በዓለም በሕይወት ዙሪያ የሚቀሰቀሱት ርእዮተ ዓለሞችን በመለየት ርእዮተ ዓለሙ የሚያስከትለው ተጽእኖና የሚኖረው አሉታዊ ክስተስት ለይቶ ጥናት በማድረግ የሕይወት ባህል የሚያነቃቃ መሆኑ የቅድስት መንበር የዜናና ኅትመት ክፍል መግለጫ ተጠቁሞ፥ ጳጳሳዊ የሕይወት ተቋም በሐዋርያዊ ቅዋሜ አንቀጽ 11  የሚገለጠው የራሱ የሆነው የበቃ ኃላፊነቱን የጠበቀ እንደሚሆን አዲሱ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ባጸደቁት ሐዋርያዊ ሕገ ውሳኒ ዘንድ ተመልክቶ እንደሚገኝ ያስታውቃል።








All the contents on this site are copyrighted ©.