2016-06-06 16:08:00

ቅ.አ.ርሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ፥ ኅብረተሰብ በጸረ የሰው ልጅ ለባርነት ደራጊ ተጨባጭ ትግል ውህድነት ይኑረው


ከመላ አህጉራት የተወጣጡ ጳጳሳዊ የማኅበራዊ ሥነ ምርምር ተቋም ባሰናዳው የሰው ልጅ ለባርነት የሚዳርግ ወንጀል በጋራ ለመዋጋርና ይኽንን ጸረ ስብአዊ ተግባር ጨርሶ ለማጥፋት ሁሉም አገሮች በፍትኃ ብሔሮቻቸው አማካኝነት ዝግጁነት እንዲኖራቸው ለማነቃቃትና በዚሁ ትግል ትብብራቸውን ማጠናከር በሚል ዓላማ ሥር በጠራው በአገረ ቫቲካን በተካሄደው ዓውደ ጉባኤ የተሳተፉትን የሕግ ሊቃውንትና ዳኞች ጠበቆች በቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ እ.ኤ.አ. ሰነ 4 ቀን 2016 ዓ.ም. አቀባበል ተደርጎላችው መሪ ቃል እንደተቀበሉ የቫቲካን ረዲዮ ልእክት ጋዜጠኛ ደቦራ ዶኒኒ አስታወቁ።

በዓለም እንደ ሥርዓት ተደርጎ ይተገበር የነበረው የባርነት ሥርዓት ቢወገድም ቅሉ በአሁኑ ሰዓት ለየት ባለ መልኩ በዓለማችን የሚታየው የወንጀል ቡድኖች የሚፈጽሙት  ሰው ለሃብት ማደለቢያ ለመጠቀም ለተለያዩ ማለትም ላመንዝራነት ለመሳሰሉ ክብር ሰራዥ ተግባር መገልገያ እንዲሆኑ ከቦታ ቦታ በማዘዋወር የሚፈጽሙት ጸረ ሰብአዊ ወንጀል ከምድረ ዓለም ለማጥፋ በሚደረገው ትግል የመላ አገሮች የሕግና ፍትኅ አገልጋዮች በመተባበር ጸረ የአዳዲስ ባርነት ትግል በተቀናጀና በተወኃደ ሥልት እግብር ላይ እንዲያውሉ ለተወያየው ዓውደ ጥናት ተሳታፊያን ቅዱስ አባታችን፥ ኅብረተሰብ በጸረ የአዲስ ባርነት ትግል ውህድነት ሊኖረው ይገባዋል የሚል ጥሪ ማእከል በማድረግ በለገሱት ምዕዳ፥

በጸረ የአዲስ ባርነት ትግል ቤተ ክርስቲያን የምትሰጠው አስተዋጽኦ

የሰው ልጅ በሕገ ወጥ ተግባር ከቦታ ቦታ ማዘዋወር፡ ያደንዛዥ እጸዋት ንግድ፡ ያመንዝራነት፡ የሰው ልጅ የውስጥ የአካለ ብልት ለንግድ አቅርቦት የመሳሰሉት ድርጊቶች በጠቅላላ ጸረ ሰብአዊ ወንጀሎች ናቸው። በመሆኑም አለ ምንም ማቅማማትም ጸረ ሰብአዊ ወንጀል ብሎ መግለጥ ብቻ ሳይሆን በሕግ ደረጃ ውጉዝ ብሎ በመግለጥ በዚሁ ጸረ ሰብአዊ ወንጀል ቁጥጥር ሂደትም በዚሁ ዘርፍ የሚያገለግሉ አካላት ተቋማት የመንግሥት ተቋሞችና ፍርድ ቤቶች በዝሁ ዘርፍ ያካበቷቸው ልምዶች በመለዋወጥ ይኸንን አዲስ የባርነት ሥርዓት ለመዋጋት የሚደረገው ጥረት ማፋጠን ያለው አስፈላጊነትም ገልጠው፡ ቤተ ክርስቲያን የሰው ልጅ ቁስልና ስቃይ ድረስ በመሄድ ብቻ ሳይሆን የቆሰለው በስቃይ ላይ የሚገኘውን ከወደቀበት ክብር ሰራዥ አደጋ ለማላቀቅ ጥሪዋ ነው፡ ስለዚህ ይኽ ጉዳይም ፖለቲካዊ ጣልቃ ገብነት ታደርጋለች የሚያስብላት አለመሆኑም ጳውሎስ ስድስተኛ ፖለቲካ አቢይ የፍቅርና የአሳቢነት ስልት ነው ሲሉ እንደተናገሩት ነው፡ ቤተ ክርስቲያን በዚህ የላቀ የፖለቲካ ትርጉም ተመርታ ስለ ሰው ልጅ ክብር ከፖለቲካው ዓለም መወያየትና መመካከር ይገባታል ግዴታም አለባት እንዳሉ ዶኒኒ ገለጡ።

የዳኞች ተልእኮ በሕግ ቁጥጥር ውጭ የሆኑትን  ወንጀለኞች በቁጥጥር ሥር ማዋል

በዚህ በአሁኑ ሰዓት  ዓለማዊነት ትሥሥር በተረጋገጠበት ዓለም በሰው ልጅ ላይ የተደቀነው የግዴለሽነትና የአለመተሳሰብ ተግዳሮት ተጠቀሱት ቅዱስ አባታችን አክለው፥ ይኽ ተጋርጦ ዳኞች ላይ የሚደርስከትለው ተጽእኖ የተሰወረ አይደለም። ስለዚህ የዳኝነት ሙያ ግብረዊ ብቻ ሳይሆን ሰብአዊም ጭምር ነው። በዚህ አገልግሎት ነጻነቱን ሙያዊና ሰባአዊ ነጻነቱን አቅቦ የሚኖር መሆን አለበት። ነጻ መሆን አለበት፡ ነጻ ከምን፥ ከኃጢአተኛ መዋቅሮች ነጻ መሆን ይጠበቅበታል፡ ቅዱስ ዮሓንስ ጵውሎስ ዳግማዊ የኃጢአት መዋቅሮች በማለት እንደገለጡትም ነው፡ ስለዚህ ከማንኛውም ዓይነት መዋቅራዊ ኃጢአት ነጻ መሆን ይጠበቅባቸዋል።

አዳዲስ የባርነት ተግባሮችን በህሉም ዘርፍና ደረጃ መዋጋት

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ተቀባይነት ያለው ምሉእ የእድገት እቅድ ሥር በቁጥር 8.7 ማንኛውም ዓይነት ወቅታዊ የባርነት ድርጊቶች ከምድረ ዓለም እስከ 2025 ባለው የዓመታት ገደብ ውስጥ ማጥፋት በሚል የገላለጥ ያስቀመጠው ውሳኔ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ አስታውሰው፡ ይኽ ውሳኔ በመንግሥታት ደረጃ ብቻ ሳይሆን በሁሉም መስክ የተገባና እንደ ማዕበል መላ የዓለም ኅብረተሰብ የሚያቅፍ የሚያሳትፍ መሆን አለበት። ስለዚህ በዳኞች መካከል በሕግ ዘርፍ ይኸንን ጸረ ሰብአዊ ወንጀል ለማጥፋት በሚያካሂድት የትግል የእርስ በእርስ ገጠመኝ ልውውጥ መቀራረብና መማማር ይኖርባቸዋል። ኅብረተሰብ በዳኛው ተክለ ሰብነት የሕግ ሉኣልዊነት ብቻ ሳይሆን የሕግ ፍትኃዊነት መለየት የሚሻ ነው፡ ከዚህ አንጻር ሲታይ የዳኞች ኃላፊነት አቢይ መሆኑ አያጠያይቅም፡ ዳኞች በተጠሩበት አገልግሎትና ተልእኮ አለ ፍትኅ ስርዓት ተቀባይነት ያለው ምሉእ እድገት ማኅበራዊ ሰላም ጭምር ሊኖር እንደማይችል መስካሪያን ናቸው በመሆኑም ይኽ የሕግና ፍትኅ መዋቅር በዚያ መንግሥታና የሕግ ጉዳይ በሚያዳክመው ከሙስናና ከመልካም አስተዳዳር ጉድለት ተግባሮች አደራ የተጠበቁ ይሁን እንዳሉ የገለጡት የቫቲካን ረዲዮ ልእክት ጋዚጠኛ ዶኒኒ አያዘው፥

የሕግ ፍትሓዊነት የሚረጋገጠው ሰለባ የሆነውን በተሟላ አገልግሎት አማካኝንት የሚያበረታታ ለዳግመ ሕንጸት የሚደግፍ ወንጀለኛው ታድሶ ከኅብረሰብ ጋር ተቀላቅሎ ለመኖር የሚደግፍ ሲሆን ነው፡ ሕግ ተበዳዩ ከተበቃይነት መንፈስ የሚያላቅቅ በዳዩም በሠራው ድርጊት ተጸጽቶ ለመልካም ነገር ሁሉ ንቁ ለማረግ የሚደግፍ መሆን አለበት። ይኽ ሲባል ደግሞ ተስፋ የሚሰጥ መሆን አለበት ማለት መሆኑ ቅዱነታቸው አብራርተው። ይኸንን ሁሉ እግብር ላይ ለማዋል ባንድ ወቅት በአንዲት ሴት አስተዳዳሪነት ሥር ይመራ የነበረው ውህነት ቤት እንድጎበኙና በዚያ ወህኒ ቤት ወንጀለኛው ታድሶ ከኅብረተሰብ ጋር ተቀላቅሎ ለመኖር የሚያግዘው የድጋፍና ሕንጸት እንዳስደነቃቸው አስታውሰው። ሴት ልጅ ያላት አስተዋይነትና ነገሮችን የማደስ ተሰጥኦ የሚደነቅ ነው ለለዚህ በሕግና ፍትኅ ዘርፍ ለሴቶች ተገቢ ሥፍድራ ምስጠት አስፈላጊ ነው ብለው በመጨረሻም ንግራቸውን ሲያጠቃልሉ የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የተራራ ስብከት “ፍትህ (ጽድቅ) እንደ እህል የሚርባቸውና እንደ ውኃ የሚጠማቸው ፍትህን (ጽድቅን) አግኝተው ስለሚረኩ ደስ ይበላቸው እግዚአብሔርን ያያሉ ከግዚአብሔር ጋርም በደስታ ይኖራሉ” እንዳሉ ገለጡ።








All the contents on this site are copyrighted ©.