2016-06-03 16:36:00

በካህናት ኢዮበልዮ ቀን ምክንያት የቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ቃለ አስተንትኖ ለካህናት


በኵላዊት ቤተ ክርስቲያን እየተኖረ ባለው ቅዱስ የምኅረት ዓመት ምክንያት የካህናት ኢዮቤልዮ ቀን ከተለያዩ አህጉራ የተወጣጡ በጠቅላላ ከስድስት ሺሕ በላይ የሚገመቱ ካህናት በተገኙበት ሁኔታ እየተከበረ ሲሆን፡ እነዚህ ሮማ የገቡት በዓለማችን የሚገኙትን ሰበካዎች ካህናትና ገዳማውያንን ለወከሉት ካህናት ቅዱስ አባታን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ በሦስቱ ጳጳሳዊ ባሲሊካዎች ማለትም በቅዱስ ዮሓንስ ዘላተራኖ ከዛም በቅድስት ማርያም ማጆረና በመጨረሻም በቅዱስ ጳውሎስ ባዚሊካ ፉዎሪ ለ ሙራ በመገኘት ሦስት አስተንትኖዎች ማቅረባቸው የቫቲካን ረዲዮ ልኡክ ጋዜጠኛ አለሳንድሮ ጂሶቲ ገለጡ፡

ቀዳሚው ቃለ አስተንትኖ በቅዱስ ዮሓንስ ዘላተራኖ ባዚሊካ

የእግዚአብሔር ምህረት ከተራርቆ መኖር ወደ ባንድ ላይ የመኖር በዓል ከችጋር ወደ ክብር የሚያሸጋግር መሆኑ ያንን በወንጌል የሚተረከው ጠፍቶ የተገኘው ልጅ ምሳሌ በማስደገፍ ተትነው። ምህረት ሁሌ ሠሪና ተቀሳቓሽም ነው። እግዚአብሔር በምኅረት ገናና ነው፡ ገደብ የለሽ ምኅረት፡ ቅዱስ አባታችን ይኽንን ሃሳብ ጠፍቶ ከተገኘው ክብሩን አጥቶ በአሳርና በችጋ ወድቆ የነበረው ልጅ ወደ አባቱ ቤት በመመለስ ከዚያ ከሚጠባበቀው ከመፈለጉ ካልቦዘነው የእግዚአብሔር ምኅረት ጋር ይገናኛል፡ ስለዚህ ይኽ ደግሞ ከተለይቶና ርቅቆ ከመኖር ወደ በዓልነት መሸጋገር ማለት ነው፡ ኃጢአት እንደ የእግዚአብሔር ምኅረት ማከማቻ ማድረግ። እግዚአብሔር መኃሪ ነው፡ ኃጢኣት ለመፈጽም የሚፈቅድ ግን አይደለም፡ የእግዚአብሔር ምኅረት ወሰን የለውም ለማለት ነው። ኃጢአት ተኰራምቶ ሃፍረት ተከናንቦ እራስ ደብቆ ወደ መኖር ይገፋፋል። ሆኖም ልክ ጠፍቶ እንደተገኘው ልጅ እግዚአብሔር ምኅረቱን አይነሳም። በምስጢረ ንስሓ የሚሰጠው አገልግሎትም  እርሱ ነው፡ የሚናዘዘውን በቁጣና በትችት ማዋከብ ሳይሆን ልክ የዚያ ጠፍቶ የተገኘው ልጅ አባት የሚያሳየው መንፈስ መኖር ያስፈልጋል፡ አናዛዥ ካህን ይኸንን መንፈስ የሚኖር የሚመሰክር መሆን ይጠበቅበታል ያሉት ቅዱስ አባታች እክለው በእግዚኣብሔር ምኅረት ከሃፍረት ወደ ክብር  የሚያሸጋግር ነው፡ መማርና የተማረ፡ ምኅረት መስጠትና መቀበል፡ ከእግዚኣብሔር ጋር የሚያዋህደ ከእርሱ የተቀበልነው ምኅረትና እኛም በአራሳችን ለሌላው የምንኖረው ምኅረት ነው፡ ምኅረት የተቀበለ ምኅረትን ይሰጣል። ምኅረት ተግባራዊ ነው፡ ስለዚህ ምኅረት የተቀበለ ስለ ሌላው አሳቢ ይሆናል። ለተቸገረው ለሚሰቃየው ርህራሄ እንዲያደርግ ይገፋፋል። ልክ ጠፍቶ እንደተገኘው ልጅ ያንን ክብሩን በገዛ ፈቃዱ ያጠፋው ውሉዳዊ መብቱ ማጣት ያስከተለበት ሃፍረት ይዞ በእግዚአብሔር ፊት እንደቀረበ ሁሉ ሆኖ መኖር፡ መኃሪነት በነጻነት የሚኖር ተግባር ነው

ምኅረትን መቀበል ወይንም አለ መቀበል ይቻላል፡ ስለዚህ በነጻነት የሚኖር ተግባር ነው፡ ምኅረት የነጻነት ጥያቄ ነው። ስለዚህ ምኅረትን ተቀብሎና አቅቦ መኖር የነጻነት ጉዳይ ነው፡ እግዚአብሔር በምኅረቱ ነጻነቱን ይገልጣል። እኛም እንደ እርሱ። ሙሴ እንደሚለውም፥ እግዚአብሔር ለሚምሩ መኃሪ ነው፡ ምኅረትን ለመስጠት ምኅረትን መቀበል ይጠይቃል እንዳሉ የቫቲካን ረዲዮ ልኡክ ጋዜጠኛ ጂሶቲ ገለጡ፡

የእግዚአብሔር ወደ የውድቀታችን አዘቅት መግባት ትስብእቱ ነው፡ ኢየሱስ ክርስቶስ ፍጹም ምኅረት ነው፡ ምኅረት በሙላት በሌላው ሕይወት መሳተፍ የሚል ነው፡ እግዚአብሔር ለመማራችን በሚወደው በአንዲያ ልጁ አማካኝነት ወዳደፈው እኛነታችን ገባ፡ እኛን መሰለ። ስለዚህ መኃሪነት ምኅረት የሚሰጠውን መምሰልን ይጠይቃል፡ ካለ ኃጢአት በስተቀረ በሁሉም እኛን የመሰለ ምኅረት።

ፈሪሳዊነት የሚያስፈራ ነው፡ ሽክ ያለ ሐዋርያዊ ግብረ ኖልዎ ጥርት ያለ በችጋር ላይ ያለውን ለመምሰል ያማይቃጣው ሐዋርያዊ ግብረ ኖልዎ ማቅረብ ከሚለው ተገሎና እራስን አግሎ መኖር ከሚለው ፈሪሳዊ ክህነት መራቅ። ምኅረት የተስፋ መሰረት ነው፡ ለሌላው ምኅረት ለመስጠት የሚደረገው ጉዞ ለኅሊና ምርመራ ይጋብዛል፡ ለሌላው ይቅር ስትል ገዛ እራስህን ትመለከ ዘንድ ያደርጋል።

ቅዱስ አባታችን የእግዚአብሔር ወሰን አልቦ ምኅረት ለመግለጥ እነዚያ ፈውስ ፈልገው በኢየሱስ ፊት የተገኙትን በወንጌል የተዘረዘሩትን ምሳሌዎች ውስጥ በስጋደዌ የተያዘው እውሩ በርጠለመዎስን የመሳሰሉትን ጠቅሰው እነዚህ ፈውስ የሚፈልጉ ድምጻቸውን ከዚያ የካህናት የግብር ማስከፈያው ድንበር ማዶ ያሰማሉ። አዎ የእግዚአብሔር ምኅረት የተጋነነ ነው፡ ከተገሎ መኖር ወደ ተዋህዶ የመኖር ክብር ያሸጋግራል፡ የምኅረት የሚሰጠው በተራው ምኅረት እንዲሰጥ ነው እንዳሉ ጂሶቲ አስታወቁ።

 

ሁለተኛው ቃለ አስተንትኖ በቅድስተ ማርያም ታልቅዋ ባዚሊካ

የእግዚአብሔር ምኅረት በእውነት ልብን የሚያድስ እንጂ ገበያ አይደለም

ቅዱስ አባታችን በዚህ በቅድስት ማሪያም ታላቋ ባዚሊካ የማርያም አብነት ላይ በማነጣጠር በለገሱት ቃአ አስተትኖ ማርያም የምኅረት ማደሪያና ምንጭ በማለት ገልጠው፡ ካህናት በማርያም ዓይነ እይታ ሕዝብን እንዲመለከቱ ኣሳስበው፡ ምኅረት ልብን የሚያድስ እንጂ የምንነሳው የእኛ ተምሳይ የሆነውን ፎቶ መልሶ የሚሰጥበት ፎቶ ቤት አይደለም፡ ይኽ ደግሞ የአዳም ኃጢአት ሰብአዊ ባኅርያችንን አይነካም የሚል ፐላጃዊነት ጽንሰ ሓሳብ አይደለም፡ ሊታደገንና ሊምረን የማይሰለቸው አምላክ፡ የሚምር ብቻ ሳይሆን ምኅረቱን የምንቀበልበት ማደጎቻችንንም ጭምር የሚያድስ ነው። ምኅረቱን የምንቀበልበት አዲሱን ወይን የምናኖርበት ማደጎቻችንን ጭምር ያድሳል።

ምኅረቱ ዳግም እንድንወለድ ያደርገናል። ስለዚህ ኃጢአተኛ መሆንህ መታመን ያስፈልጋል። ቅዱሳኖች ኃጢተኛ መሆናቸው የሚታመኑ ናቸው፡ ምኅረት የምንቀበልበት ማዶጎአችን ወደ ምንቀበለው ምኅረት ይለወጣል፡ ቅዱስ ጳውሎስ ከሕግ አጥባቂነት ተላቆ ሌሎችን ከሕግ ነጻ ለመውጣት ይንቀሳቀሳል ልኡክ ይሆናል። ሌሎችን ሊረዳና ሊምርም ይጀምራል፡ የጳውሎስ ፈራጅነት በዚያ ቅድመ ሁነት በማይል በእግዚአብሔር ምኅረት ላይ የተመሠረተ ይሆናል ያሉት ቅዱስ አባታን አያይዘ ምኅረትን ለመቀበል  ከእብሪተኝነትና ከትዕቢት መላቀቅ ያስፈልጋ። ይኸንን ነጥብ ከቅዱስ ጴጥሮስ ታሪክ ጋር በማመሳሰልም፥ ጴጥሮስ ብዙውን ጊዜ በኢየሱስ የተገሰጸ የታረመ እንደነበርም አስታውሰው። ቅዱስ የሐንስ፡ ቅዱስ አጎስጢኖስ፡ ቅዱስ ፍራቸስኮስ … ቅዱስ ኢግናዚዮስ ዘለዮላን  በማስታወስ እነዚህ ሁሉ ቅዱሳኖች በእግዚአብሔር መኃሪነት የነበራቸው ትዕቢት ሁሉ ተፈውሷል ብለው በመጨረሻም ቅድስት ድንግል ማርያም ካህን ሕዝብን በፍቅር ለማየት ጥሪው ትእምርት ነች። የምኅረት ኪዳን ለሕዝበ እግዚአብሔር ትሆን ዘንድ የተመረጠች ናት። ስለዚህ ካህን የሚሻው አብነትም እርሷ ነች። የማርያም አይኖች ማህጸናዊ እንጂ ቤተ ፍርዳዊ አይን አይደአም እንዳሉ የቫቲካን ረዲዮ ልኡክ ጋዜጠኛ አለሳንድሮ ጂሶቲ ገለጡ።

ቤተ ክርስቲያን በሮችዋን ለሚያንኳኳ የምትንከባከብ መሆን ይገባታል

ብዙውን ጊዜ ካህናት አቡኖቻቸው ወደ ሌላ ቁምስና ያዛውሯቸው ዘንድ ይጠይቃሉ፡ መፍትሔው ሕዝብ መቀየር ሳይሆን  ገዛ እራስን መለወጥ ነው ስለዚህ አንድ ካህን በገዛ እራስ ከመዘጋት ፈተና ይጠቀቅ። በሮቿ ለሚያንኳኩ ክፍት የሆነች ቤተ ክርስቲያን ብቻ ነች ስለ እግዚአብሔር ለመናገር የምትችለው። ለሕዝብ ልቡ ክፍት ያልሆነ ካህን ለሕዝብ ስለ ቃለ እግዚአብሔር ለመናገር የሚቻለው አይደለም።

የማርያም እይታ ህዝብን እያንዳንዱን ሰው በምሉእነት የሚመለከት ነው። የተቆራረጠ እይታ የላትም። ማርያም በቃና ዘገሊላ እናስታውስ። የኢየሱስ ምላሽ ትማጸናለች። የሚጎድልብንን የምታውቅ እናት ነች። ስለዚህ የጎደለው ይሞላ ዘንድ ጎዶሎነታችንን ይዛ ለልጇ ታቀርባለች።

በማርያም መንጠሊና ሥር እንገኝም ዘንድ እንፍቀድ በማለት ሁለተኛው ቃለ አስተንትኖ ማጠናቀቃቸው ጂሶቲ አስታወቁ።

 

ቅዱስ አባታችን ከሰዓት በኋላ በሮማ ሰዓት አቆጣጠር ልክ 4 ሰዓት ሮማ ወደ ሚገኘው ቅዱስ ጵውሎስ ባዚሊካ በመሄድ በለገሱት ሦስተኛው ቃለ አስተንትኖ፥ ዮሐንስ ወንጌል ምዕ. 2 ከቁጥር 1 እስከ 12 ያለውን ጠቅሰው፥ “እርሱ የሚላችሁን አድርጉ” የሚለው ቃል ማእከል በማድረግ ምኅረቱና ግብረ ተአምሩ ይፈጸም ዘንድ፡ እርሱ የሚለውን ከመፈጸም የማይታክት ሕይወት መኖር ያለው ውሳኝነት ማርያም ታረጋግጥልናለች።

በዚያ ብዙ ሕዝብ በተሰበሰበበት የበርጠለዎስ ጩኸትን የሰማ ያችህ ብዙ ሕዝብ በነበረበት ሥፍራ ቀስ ብላ የልብሱን ጫፍ የነካቸውን ሴት ሁነት  እናስታውስ። በመስቀል ላይ ተሰቅሎ የሰው ልጅ ጥልቅ ስቃይና መከራ ያዳመጠው ኢየሱስን እናስብ። ኢየሱስ ቅብአ ምኅረቱን ይቀባንም ዘንድ የእኛ መሆንን ለበሰ። ምኅረቱ ጸጋ ነውና ምኅረቱን መለመን ያስፈልጋል።

የኵላዊት ቤተ ክርስቲያን ትምህርተ ክርስቶስ በቁጥር 2449 ላይ ስለ ግብረ ሠናይ ሲናገር፥ ኢየሱስ በድኾች ዘንድ እንዳለ የተናገረው እውነት ተመልክቶ እናገኛለን። ድኾችን እንዳንረሳ አደራው የተቀበልን ነን፡ ቤተ ክርስቲያን የምታቀርበው ግብረ ሠናይ ነጻ የሚያወጣ መሆን አለበት፡ ላዘኑት መጽናናን ድምጽ ለሌላቸው ድምጽ ለተጨቆኑት ነጻነት ለምታውጅ ቤተ ክርስትያን አገልጋዮች ነን፡ ይኸንን ለማድረግ ለድኾ ለተናቁት ለተራቡት ፍቅር ሊኖረን ይገባል፡ ይኽ ደግሞ ሕዝበ እግዚአብሔር እግዚአብሔርን ያመሰግንና ይወድስም ዘንድ ያነቃቃዋል፡ ሕዝብ የማይምረው ጉዳይ ቢኖር ያንድ ካህን የገንዘብ ወዳጅ መሆን ነው፡ ገንዘብ ስላለው ሳይሆን ሃብት እግዚአብሔርን የሚያስረሳ በመሆኑ ነው፡ ሃብታሞች እንድንሆን ድኽነታችንን የገዛ እራሱ አደረገ፡ ስንሰጥ የምናገኝ እንጂ ባለ መስጠት የማናገኝ እንዳንሆን እንጠንቀቅ፡ ፍቅርን ይዘን የማንጓዝ ከሆን ክርስቲያኖች እይደለንም፡ ካህናትም አይደለንም።

የአብ መንፈስ የሚኖር ክህነት አሳቢነት የሕዝብ ስቃይና መከራ ለይቶ የሚያወቅ የቤተ ክርስቲያን እናታዊ መንፈስ የሚያጎላ ካህን መሆን ነው፡ አንድ ካህን በሚያሳየው ተግባር አማካኝነት የሕዝብን ስቃይ የሚገነዘብና የሚያስተውል መሆኑ ይመሰክራል፡ ያችን ኢየሱስ የሚኮንንሽ ማንም የለም ደግመሽ ሓጢአት አትስሪ ተነሽ ያላትን አመንዝራ፡ ትወገር አትወገር የተባለባት። እኔም አልፈርድብሽም ነው የተባለቸው፡ ኢየሱስ ጎንበስ ብሎ እግሮቹህ አጥፎ ነው በወደቀችበት ቀርቦ ያናገራት። ኢየሱስ ሲፈውስ ዳግም ሐጢአት እትስራ ነው የሚለው እንጂ አይፈርድም። የሚፈርደው ታዲያ ማን ነው፡ ሊፈርድ የሚቃጣውስ ማን ነው፡ ተነስ ዳግም ሐጢአት ኣትስራ የሚለውን የጌታ ድምጽ እያንዳንዱ በውስጥ ለራሱ እንደተባለ አድርጎ ሊያዳምጠው ይገባዋ፡ በፍቅር ጎዳና መመላለስ ልክ እግዚኣብሔር ከሕዝቡ ጋር እንደሚጓዝ ሁሉ ካህንም ከሕዝብ ጋር የሚጓዝ መሆን አለበት።

ምሥጢረ ንስሐ ነጻ የሚያወጣ እውነት ያለበት ሥፍራ ነው፡ የንስሐ ምሥጢር ወይንም የንስሐ ሊጡርጊያ ያንን የጠፋችውን በጉን ሊፈልግ የሚወጣው የእረኛው መንፈስ የሚኖርበት ሁነት ነው፡ የደጉ ሳምራዊው የጠፋውና  ልንጁ የሚጠባበቅ አባት የሚኖረው ሁነት የሚኖርበት ሥፍራነው።

ካህን የግኑኝነት ምልክትና መሣሪያ ነው፡ ግልጽ የሆነ የማያምታታና የማያሻማ ምልክት ለመሆንም ከጌታ ምኅረት ጋር መገናኘ ይኖርበታል ያሉት ቅዱስ አባታችን በመቀጠል የምኅረት ተግባር ያለው ማኅበራዊ ገጽታውን ተንትነው፤ ግብረ ምኅረት በቅዱሳት ሚሥጥራት በሐዋርያዊ ግብረ ኖልዎ፡ በግብረ ሠናይ በጸሎት የሚኖ እንጂ፡ የማይጨበጥ ሃሳብ አይደለም ብለው የመልካሙን እረኛ ጸጋ እንለምን ብለው የምኅረት ጸሎት ደግመው የለገሱት ቃለ አስተንትኖ እንዳጠቃለሉ ጂሶቲ ገለጡ።








All the contents on this site are copyrighted ©.