2016-06-01 15:38:00

ናይጀሪያ


እ.ኤ.አ. ከ 2006 እስከ 2014 ዓ.ም. ውስጥ በናይጀሪያ የምስልምና ሃማኖት አክራሪው ቦኮ ሐራም አሸባሪው ኃይል በሰነዘረው ጸረ ክርስቲያን ጣቃት ሳቢያ አሥራ አንድ ሺሕ ክርስቲያን ለሞት 1.3 ሚሊዮን የሚገመት ማኅበረ ክርስቲያን ለመፈናቀል እንዲሁም 13 ሺሕ አቢያተ ክርስቲያን መውደማቸው የናይጀሪያ ብሔራዊ የክርስቲያን ማኅበር ካወጣው ሰነዳዊ መግለጫ ለመረዳት ሲቻል፡ ይኸንን ጉዳይ በማስመልከትም በኒው ዮርክ በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት በስፐይን ሲትዘን ጎ የተሰየመው የክርስቲያን ማኅበር ከቅድስት መንበር ጋር በመተባበር ባነቃቁት የሃይማኖት ነጻነት በሚል ርእስ ዙሪያ በመከረው ዓውደ ጉባኤ ከተሳተፉት በናይጀሪያ የካፋንቻን ሰበካ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ጆሰፍ ባጎቢሪ ለጉባኤው ባስደመጡት ንግግር፥

በሰሜናዊ ናይጀሪያ የሚከሰተው ጸረ ክርስቲያንና ጸረ ቤተ ክርስቲያን ጥቃት በናይጀሪያ መንግሥት ብቻ እንዲፈታ መተዉ በእውነት እጅግ አደገኛ ነው፡ ስለዚህ የዓለም አቀፍ ማኅበረሰብ ምላሽ ሊሰጥበት ከሚገባቸው ወቅታዊና አንገብጋቢነት ችግር ነው ። በዚህ ቦኮ ሐራም በሚሰነዝረው ጥቃት ሰለባ የሚሆነው ማኅበረ ክርስቲያን ሲሆን፡ ሌላው ለክርስቲያን ማኅበረሰብ አቢይ ስጋት የሆነውም በእንስሳት ርቢ የሚተዳደረው የፉላን ሙስሊም ማኅበረሰብ የክርስቲያኖችን መሬት በመንጠቅ የሚፈጽሙት ጸረ ማኅበረ ክርስቲያን ተግባር ጠቅሰው፡ ስለዚህ በአገሪቱ የሚታየው ጸረ ክርስቲያን ጥቃት ተጠያቂው ቦኮ ሓራምና እነዚህ የፉላን ጎቻዎች ናቸው እንዳሉ የቫቲካን ረዲዮ ልእክት ጋዜጠኛ ሊዛ ዘንጋሪኒን ካጠናቀሩት ዘገባ ለመረዳ ተችለዋል።

ብፁዕነታቸው በዚህ አጋጣሚም ቦኮ ሓራም የሚያረማምደው በናይጀሪያ የሚታየው ጸረ ክርስቲያን ዘመቻና ጥቃት እልባት እንዲያገኝ የአገሪቱ መንግሥት በዚሁ ጉዳይ አበክሮ እንዲሰራና ማኅበራዊ የሰላሙ ኑሮ ማረጋገጥ ተቀዳሚ ዓላምው እንዲያደርግ በናይጀሪያ የክርስቲያኖችና የኃዳጣን የአገሪቱ የኅብረተሰብ ክፍል መብትና ክብር በማረጋገጡ ረገድ እንዲተጋ በክልሉ እየተስፋፋ በመሄድ ላይ ያለው ጸረ ክርስቲያን ጥቃትና አመለካከት ለማስወገድ የዓለም አቀፍ ማኅበረሰብ ገላጋይ ጣልቃ ገብነት እጅግ እስፈላጊ ነው ብለዋል።

በመጨረሻም ብፁዕ አቡነ ጆሰፍ ባጎቢሪ በዓለም የሚታየው ጸረ ክርስቲያን ተግዳሮችና በማኅበረ ክርስቲያን ላይ የተጋረጠው ስደት በማሰብ የሰው ልጅ በሰላም በነጻነት በውህደትና ስምምነት ብሎም በፍቅር ለመኖር የሚችልበት አዲስ ዓለም አቀፋዊ ሥርዓት እንዲረጋገጥም ለሁሉም የዓለም መንግሥታት ጥሪ በማቅረብ ያስደመጡት ንግግር እንዳጠቃሉ የቫቲካን ረዲዮ ልእክት ጋዜጠኛ ሊዛ ዘንጋሪኒን  ገለጡ።








All the contents on this site are copyrighted ©.