2016-06-01 15:33:00

ብፁዕ ካርዲናል ታግለ፥ ምግብ የማባከን ድርጊት በድኾች ላይ የሚፈጸም ኢፍትኃዊ ተግባር ነው


የተለያዩ የካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን የተራድኦ ማኅበራትን ለሚጠራንፈው ካሪታስ ኢንተናዚዮሊስ ለተሰየመው ማኅበር ሊቀ መንበር በፊሊፒንስ የማኒላ ሊቀ ጳጳሳት ብፁዕ ካርዲናል አንቶኒዮ ታግለ እ.ኤ.አ. ግንቦት 30 ቀን 2016 ዓ.ም. በሮማ የተባበሩት መንግሥታት የምግብና የእርሻ ድርጅት ምክር ቤት “ምግብ የማባከን ተግባር መዋጋት” በሚል ርእሥ ዙሪያ  ባካሄደው ዓውደ ጉባኤ ተገኘው ጥሮና ግሮ እንዲኖር የተጠራው ሰው የሥራው ፍሬ ሳያገኝ እንዳይቀር የፍትኅ ጉዳይ የሚመለከት ጥያቄ ነው የሚል ቅዉም ሃሳብ ላይ ያነጣጠረ ንግግር ማሰማታቸው የቫቲካን ረዲዮ ልእክት ጋዜጠኛ ሮበርታ ጂሶቲ ገለጡ።

በተባበሩ መንግሥታት የቅድስት መንበር ቋሚ ታዛቢ ሊቀ ጳጳሳት ብፁዕ አቡነ ፈርናንዶ ቺካ አረላኖ በበኩላቸውም ባስደመጡት ንግግርም የምግብ ምርት ብክነት በሰው ልጅ ሕይወት እጅግ አገብጋቢ ከሚባሉት ተግዳሮች ውስጥ አቢይ ተግዳሮት ነው፡ ስለዚህ ሰው ምግብ የማግኘ መሠረታዊ ፍላጎቱ ዋስትና መስጠት ግድና የሁሉም ኃላፊነት ነው እንዳሉ ጂሶቲ ይጠቁማሉ።

በዚህ አጋጣሚም ብፁዕ ካርዲናል ታግለ ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ፥ በዓለም የምግብ ምርት አንድ ሦስተኛው ባክኖ የሚቀር ሲሆን ይኽ ደግሞ 1.6 ሚሊያርድ ቶን የሚለካ መሆኑም ገልጠው ምግብ ማባካን በምግብ እጥረ ከሚሰቃየውና ከተራበው የሚነጥቅ ምግብ ነው። የሚባክነው ምግብ በእርሃብ ለሚጠቃው ቢታደል ኖሮ እርሃብተኛ ባልኖረ ነበር ብለዋል።

በበለጸጉት አገሮች የሚባክነው የምግብ ምርት 40 መቶኛው ገና በመመረት ሂደት ላይ እያለ ወይንም በተጠቃሚው ሕዝብ እጅ እየተጣለ የሚባክን ሲሆን፡ ይኽ ደሞግ ሞያዊ ጥያቄ ብቻ ሳይሆን በከፍተኛ ደረጃ ከፍትህ ጋር የተያየዘ ጥያቄ ነው ካሉ በኋላ፥ በምግብ እጥረት የሚሰቃየው ሕዝብና ረሃብተኛው ዜጋ የተጋረጠበት አደጋ ሰብአዊ ቀውስ ነው፡ በመሆኑም ማንኛውም ዓይነት እድገት ለልማት የሚደረገው ሂደት ሁሉ ግብረኣዊነት ላይ የጸና ብቻ ሳይሆን የሰው ልጅና የኅብረተሰብ ምሉእ እድገት የሚደግፍ መሆን አለበት፡ እድገት ግብረአዊ ብቻ ሲሆን ሰብአዊ ልክነት የሌለው ይሆናል። የተፈጥሮው የጋራው ሃብት ሁሉንም የሚያሳትፍ ማድረግና በማንኛውም ዓይነት እድገት መተባበርና መደጋገፍ በተሰኙት እሴቶች ላይ የጸና መሆን አለበት ብለዋል።

ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ በአንድ ወቅት የሚባክነው የምግብ ምርት የሚጣለውም ሁሉ ከድኻው የሚነጠቅ ነው በማለት ገልጠዉታል፡ ስለዚህ የሚጣለው ምግብት ለረሃብተኛው የሚሰጥ ቢሆን በዓለማችን ተራቢ ሕዝብ ባልኖረ፡ጉዳዩ የኅሊና ጥያቄ ነው፡ ይኽ በቅድስት መንበርና በኢራን መንግሥት አነሳሽነት ተከትሎ የተካሄደ አውደ ጉብኤ መሆኑም አስታውሰው። ቅድስት  መንበር ቃለ እግዚአብሔር የምትከተልና የማኅበራዊ የቤተ ክርስቲያን ትምህርት መሠረት በመኖር ሰብአዊነት ማእከል ያደረገ ባህል እንዲስፋፋ ታነቃቃለች፡ ይኽ የምትከተለው ዓላማ መሠረት በማድረግ የምታከናውነው ግኑኝነት የተዋጣለት መሆኑ ለሁሉም የተሰወረ አይደለም፡ ስለዚህ የኢራንና የቅድስት መንበር የጋራው ግኑኝነት በዓለም ለሥነ ከሌአዊ ግኑኝነት እንደ አብነት ሊጠቀስ የሚችልም ነው ካሉ በኋላ፥ ሁሉም የተለያዩ ኃይማኖቶች የምግብ ምርት የማባከኑ ድርጊት እንዲገታ አብረው በመተባበር ከዓለም እርሃብ ለማጥፋት በሚደረገው ጥረትና የመንግሥታት ኅሊና በማነቃቃቱ ረገድ ሊተባበሩ ይገባል በማለት ያካሄዱት ቃለ ምልልስ አጠቃለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.