2016-05-30 16:02:00

የመልአከ እግዚአብሔር ጉባኤ አስተምህሮ


እ.ኤ.አ. ግንቦት 29 ቀን 2016 ዓ.ም. ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍርንቸስኮ በምኅረት ዓመት የዲያቆናት ዕለት ምክንያት በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ መሥዋዕተ ቅዳሴ እሳርገው እንዳበቁ እኩለ ቀን በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባው ከተሰበሰበው ከውጭና ከውስጥ የመጣው በብዙ ሺሕ የሚገመት ምእመን በተገኘበት ጸሎተ መልአከ እግዚአብሔር ከማሳረጋቸው ቀደም በማድረግ ባስደመጡ ቃለ አስተንትኖ፥ ቅድስት ድንግል ማርያም በክራኮቪያ ሊካሄድ በተወሰነው ዓለም አቀፍ የወጣቶች ቀን ለሚሳተትፉት ቤተ ሰቦችና ወጣቶች ትደግፍ ካሉ በኋላ የሶሪያ ወቅታዊ ሁኔታም በማስታወስ፥ እ.ኤ.አ. ሰነ 1 ቀን 2016 ዓ.ም. በኵላዊት ቤተ ክርስቲያን ስለ ሶሪያ የሚጸለይበት ዕለት እንደሚሆን ገልጠው ዕለቱም ዓለም አቀፍ የሕጻናት ቀን የሚከበርበት ጭምር መሆኑ ያስታወሱት ቅዱስ አባታችን በማያያዝም ስለ ሶሪያ በሚደረገው ጸሎት ካቶሊካዊትና ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያን በሁባሬ እንደሚሳተፉ ገልጠው፥ በዚህ ዓለም አቀፍ የሕጻናት ቀን ምክንያት በመላ ዓለም ስለ ሚገኙት ሕጻናት መጸለይ ስለ ሰላም መጸለይ ማለት በመሆኑም የመላ ዓለም ሕጻናት ስለ ሶሪያ ሕጻናት እንጸለይ ጥሪ ያቀርባሉ፡ ጥሪውን ተቀብለንም ስለ እነርሱ በጋራ እንጸልይ አደራ እንዳሉ የቫቲካን ረዲዮ ልኡክ ጋዜጠኛ አመደዮ ሎሞናኮ ገለጡ።

ይኽ በእንዲህ እንዳለም በሶሪያ ሁለት ሚሊዮን ከግማሽ የሚገመቱ ከአምስ ዓመት እድሜ በታች የሆኑት የሶሪያ ሕጻናት ለተመጣጠነ ምግብ እጥረት መጋለጣቸውና ሌሎች ከ ሦስት ሺሕ በላይ  የሚገምቱ ሕጻናት ከነቤተሰቦቻቸው በደማስቆ አቅራቢያ በሚገኘው የክሃን ኢሻይሕ ክልል በተፈናቃዮች መጠለያ ሰፈር የሚገኙት በክልሉ ባለው የከፋው ውጥረት ሳቢያ የሰብአዊ እርዳታ ሊቀርብላቸው ባለ መቻሉ ምክንያት ለከፋ አደጋ ተጋልጠው እንደሚገኙ ያስታወሱት ልኡክ ጋዜጠኛ ሎሞናኮ አያይዘው፥ በአለፖ ክልል አንድ ሚሊዮን ሁለት መቶ ሺሕ ሕጻናት እጅግ ለከፋ አደጋ መጋለጣቸውም ይጠቁማሉ።








All the contents on this site are copyrighted ©.