2016-05-30 17:06:00

በራዲዮ ቫቲካን የአርመንኛ ቋንቋ ስርጭት ጅማሬ 50ኛ ዓመት


እ.ኤ,አ. ግንቦት 29 ቀን 1966 ዓ.ም. በቫቲካን ረዲዮ የአርመንኛ ቋንቋ ስርጭት የተጀመረበት ቀን ምክንያት ይኸው እ.ኤ.አ. ግንቦት 29 ቀን 2016 ዓ.ም. 50ኛውን ዓመቱን ያከበረ ሲሆን። የዚህ ስርጭት  መርሃ ግብር ኃላፊ በመሆን ለ20 ዓመታት ያገለገሉት ቋሚ ዲያቆን ሚሸል ዣንገ ለ50ኛው የስርጭቱ ክብረ በዓል ቅድመ ዝግጅት ከመሩ በኋላ ግንቦት 29 ቀን 2016 ዓ.ም.ማለዳ በድንገት ከዚህ ዓለም በሞት ተለይቷል፡ ዣንግ ቋሚ ዲያቆን በመሆንቸውም ይኸው  ግንቦት 29 ቀን 2016 ዓ.ም. በምኅረት ዓመት የዲያቆናት ዕለት ምክንያት በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ በሚያሳርጉት መሥዋዕት ቅዳሴ ይሳተፋሉ ተብለው ይጠበቁም እንደነበር የገለጡት የቫቲካን ረዲዮ ልኡክ ጋዚጠኛ ቸንቶፋንቲ አክለው፥ ነፍሰ ኄር ዣንግ እ.ኤ.አ. ሐምሌ 13 ቀን 1945 ዓ.ም. የተወለዱ የሁለት ልጆች አባት የዋህ ሁሉንም  አገልጋይ አወንታዊ ባህር ያላቸው እ.ኤ.አ. መስከረም 27 ቀን 2007 ዓ.ም. የቅዱስ ሲልቨስትሪ ቅዱስ ማኅበር ልዩ የክብር ሽልማት ከቅዱስነታቸው ልኂቅ ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ እጅ የተቀበሉ መሆናቸው በማስታወስ ይጠቁማሉ።

ነፍሰ ኄር ዣንግ በሮማ የአርመን ማኅበረሰብ ሊቀ መንበር በመሆን ያገለገሉ አርመን በሶቭየት ኅብረት ግዛት ውስጥ በነበረችበት ወቅት በራዲዮ ቫቲካን አማካኝነት ለዚያ በክርስትና እምነቱም ጭምር ይሰደድ ለነበረው አአርመ ሕዝብ ወንጌል በማቅረብ በቫቲካን ረዲዮ አማካኝነት የኵላዊት ቤተ ክርስቲያን ቅርበት በመመስከር ለዚያ በስውር ራዲዮ ቫቲካን ያዳምጥ ለነበረው አርመናዊ ሁሉ የኵላዊት ቤተ ክርስቲያንና የቅዱስ ጴጥሮስ ተከታይ ድጋፍና ጽናት ያስተጋቡ እንደነበ ቸንቶፋንቲ ገልጠው፥ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ እ.ኤ.አ. ከሰነ 24 ቀን እስከ ሰነ 26 ቀን 2016 ዓ.ም. በሃገረ አርመን ሊያካሂዱት በእቅድ በተያዘው ዓለም አቀፋዊ ሐዋርያዊ ጉብኝት በመገኘትም ቅዱስነታቸው በግዩሚሪ በሚያሳርጉት መሥዋዕተ ቅዳሴ ይሳተፋሉ ከሚባሉት ውስጥ አንዱ እንደሩም አስታውሰው በዚህ አጋጣሚም መላ የቫቲካን ረዲዮ የኢትዮጵያና የኤርትራ ክፍል አባላት ለሟቹ ዣንግ ቤተሰብ ወዳጅ ዘመድ እንዲሁም ለስራ ባልደረቦቻቸው ሁሉ የእግዚአብሔር መጻናናቱን እንመኛለ፡ እግዚአብሔር ነፍሳቸውን ይማር።








All the contents on this site are copyrighted ©.