2016-05-24 12:12:00

ቅዱስነታቸው "ክርስቲያን ያለ እግ/ር ደስታ ልኖር አይችልም" ማለታቸው ተገለጸ።


ቅዱስ አባታችን ፍራንቸስኮ ዘወትር ጥዋት በቅድስት ማርታ የጸሎት ቤት ካህናት፣ ደናግላን እና ምዕመናን በተገኙበት መስዋዕተ ቅዳሴን እንደ ሚያሳርጉ የሚታወቅ ሲሆን በግንቦት 15/2008 ባሳረጉት ስራዓት ቅዳሴ ላይ ባሰሙት ስብከት እንደገለጹት ማንም ክርስቲያን ያለ ደስታ ሊኖር አይችልም ማለታቸው ተገለጸ።

ምንም እንኳን በሕይወት ውስጥ ብዙ መከራ ቢኖርም ክርስቲያኖች በኢየሱስ መታመን እና ተስፋን ማድረግ ግን ያውቁበታል በማለት ስብከተ ወንጌላቸውን የጀመሩት ቅዱስ አባታችን ክርስቲያኖች ወደ ሐዘን ለሚመራቸው ባለ ጠግነት ሕይወታቸውን እንዲቆጣጠረው መፍቀድ አይኖርባቸውም በማለት አሳስበዋል።

ክርስቲያኖች ከሙታን በተነሳው በክርስቶስ ምክንያት በምያስደንቅ ደስታ ውስጥ ይኖራሉ በማለት ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው በእለቱ በተነበበው በመጀመሪያው የሐዋሪያው ጴጥሮስ መልዕክት ከምዕራፍ 1:3-9 በተወሰደው ምንባብ ላይ በመመርኮዝ ባሰሙት ስብከታቸው ምንም እንኳን በፈተናዎች ብንዋጥም “በክርስቶስ ዳግም እንድንወለድ ያደረገንን እና ተስፋ የሰጠንን” እግዚአብሔርን የማወቅ ድስታ ልናጣ ግን በፍጹም አንችልም ብለዋል። 

ቅዱስነታቸው በማስከተል እንደ ገለጹት “አንድ ክርስቲያን ልቡ በደስታ የተሞላ ነው። ደስታ የሌለው ክርስቲያን የለም” በማለት ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው “ደስታ የለንም የሚሉ ክርስቲያኖች አሉ ተብላችሁ ሰምታችሁ ልታውቁ ትችላላችሁ እኔ ግን እነዚህ ክርስቲያኖች አይደሉም ነው የምለው፣ ክርስቲያኖች ነን ይላሉ ነግር ግን በፍጹም አይደሉም ምክንያቱም የሚጎላቸው ነገር ስላለ ነው” ብለዋል።

“ደስታ የአንድ ክርስቲያን የመታወቂያ ወረቀቱ ነው በተለይም በወንጌል የሚገኘው ደስታ፣ በክርስቶስ የመመረጣችን ደስታ፣ በክርስቶስ የመዳናችን ደስታ፣ አንዲስ ሕይወት በክርስቶስ የማግኘታችን ደስታ፣ ክርስቶስ እንደ ሚጠብቀን እና በእዚህ ምድር በሚገጥሙን መስቀሎች እና መከራዎች ወቅት ሁሉ እንደ ሚጠብቀን ተስፋ የምናደርግበት ደስታ በአጠቃላይ በእርግጠኝነት ኢየሱስ ከእኛ ጋር እንደ ሚጓዝ እና ሰላሙን እንደ ሚሰጠን ስናስብ የምናገኘው ደስታ የክርስቲያን መለያ ባሕሪው ነው” ብለዋል።

በማስከተልም ቅዱስነታቸው በእለቱ በተነበበው እና ከማርቆስ ወንጌል ከምዕራፍ 10: 17-27 በተወሰደው ምንባብ ላይ በቀጣይነት ትኩረታቸውን በማድርገ እና ኢየሱስ ከሀብታሙ ሰው ጋር የተገናኘበትን ምሳሌ ዋቢ በማድረግ እንደ ገለጹት “ይህ ሐብታም ሰው ብዙ ሐብት ስለነበረው ልቡን ለደስታ ሳይሆን ለሐዘን መክፈትን መርጡዋል”  ምክንያቱም የነበረው ንብረት እና ሀብት ተብትቦት ይዞት ነበር” ብለው ኢየሱስ  አንድ ሰው ለሁለት ጌታ መታዘዝ እንዳማይችላ አስተንቅቆን ነበር ካሉ ቡኋላ እግዚአብሔርን ወይም ንብረቱን መምረጥ ይገባዋል እንዳለን ጨምረው ገልጸዋል።

ሀብት በእራሱ መጥፎ ነገር አይደለም ነገር ግን ለሀብታችን ባሪያ መሆን ደካማነት ነው በማለት ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው ሀብታሙ ወጣት ሰው ይህንን በሰማበት ወቅት በሀዘን ተሞልቶ ወደ መጣበት ተመልሶ ሄዶዋል ብለው በምንሰራበት ቁምሳና፣ በማኅበርሰብ እና በማዕከላት ውስጥ ክርስቲያን ነኝ ነገር ግን ደስተኛ አይደለሁኝም የሚሉ ሰዎች በምያጋጥሙን ወቅት አንድ የተሳሳተ ነገር በሕይወታቸው እንደተከሰት መገንዘብ እንችላለን ብለዋል። እንዲህ ዓይነቱ ሁኔታ በምያጋጥመን ወቅት እንደነዚህ አይነት ሰዎች ሀዘናቸውን አስወግደው ኢየሱስን ያገኙ ዘንድ እና በወንጌል ላይ መሰረቱን ያደረገ እውነተኛ ደስታ ይጎናጸፉ ዘንድ ልንረዳቸው ያስፈልጋል ብለዋል።

አንድ ክርስቲያን ከእግዚአብሔር ግልጸት እና ፍቅር ጋር በሚገናኝበት ወቅት በመንፈስ ቅዱስ አቀጣጣይነት ወደ “አስገራሚ የሆነ ደስታ” ውስጥ ይገባል ያሉት ቅዱስነታቸው ኢየሱስ ተስፋ በቆረጠ ስሜት ለሐዋሪያቱ ይህ ሐብታም ወጣት ሰው ከሀብቱ ጋር ባለው ቁርኝት ምክንያት ልከተለው እንዳልፈለገ በገለጸበት ወቅት ሐዋሪያቱ “እንዲህ ከሆነ ታዲያ ማን ልድን ይችላል? ብለው በጠየቁት ጊዜ ኢየሱስም “ለሰው የማይቻል ነገር ሁሉ ለእግዚአብሔር ግን ይቻላል” ብሎ መልሶላቸው ነበር ስለእዚህም ክርስቲያን ከዓለማዊ ነግሮች ተላቆ ደስታውን ሊጎናጸፍ የሚችለው በእግዚአብሔር ኋይል እና በመንፈስ ቅዱሱ ጥንካሬን ስያገኝ ብቻ ነው ብለዋል።

በስብከታቸው ማጠቃለያ ላይ ቅዱስነታቸው እንደ ገለጹት ጌታ በፀጋው እንድያስገርመን፣ እንዲሁም በተሰጠን ብዙ መንፈሳዊ ፀጋ ላይ ተመርኩዘን ደስታን እንድንጎናጸፍና በስቸጋር ሁኔታ ውስጥም በምንገኝበት ወቅት ጌታ ልባችንን በደስታ እንዲሞላው እጸልያለሁ ብለው ብዙ ደስታ የሚሰጡ የሚመስሉ ነግር ግን ምንም አይነታ ደስታን ልያጎናጽፉን ከማይችሉ እና ሰላማችንን ከሚነሱን ዓለማዊ ነገሮች ተጠብቀን እንድንኖር እና ክርስቲያን ማለት በጌታ የሚገኘውን ሰላም የተላበሰ እና አስገራሚ ተግባር የሚፈጽም ሰው መሆኑን እንድንረዳ ያስፈልጋል ብለው ስብከታቸውን አጠናቀዋል። 

 








All the contents on this site are copyrighted ©.