2016-05-24 10:33:00

ቅዱስነታቸው በስብከታቸው "እራስን ለማበልጸግ በማሰብ ሠራተኞቻችንን መበዝበዝ ደም እንደ መምጠጥ ይቆጠራል ማለታቸው ተገለጸ"።


ቅዱስ አባታችን ፍራንቸስኮ በግንቦት 11/2008 በቅድስት ማርታ የጸሎት ቤት ካህናት፣ ደናግላን እና ምዕመናን በተገኙበት ባሳረጉት ስርዓተ ቅዳሴ ላይ ባሰሙት የወንጌል ስብከት እራስን ለማበልጸግ በማሰብ ሠራተኞቻችንን መበዝበዝ ደም እንደ መምጠጥ ይቆጠራል ማለታቸው ተገለጸ።

የእለቱ የመጀምሪያ ምንባብ የተወሰደው ከያዕቆብ በልእክት ከምዕራፍ 5:1-6 ሲሆን ሐዋሪያው ያዕቆብ ሕዝብን በመበዝበዝ ሀብት ለምያከማቹ ሀብታም ሰዎች  ጠንከር ያለ ማስጠንቀቂያ የሰተበጥ ምንባብ ላይ በመመርኮዝ ቅዱስነታችው እንዳሳሰቡት “ሀብት በእራሱ ጥሩ ነገር ቢሆንም ነገር ግን ሀብት ጠቃሚ ነገር እንጂ ፍጹም ነገር አይደለም” ብለዋል።

በስብከታቸው ወቅት ቅዱስነታቸው “የብልጽግና ሥነ-መለኮት” ተብሎ የሚጠራውን አመለካከት የተቹ ሲሆን "ጥሩ ሰው በመሆኔ እግዚአብሔር ባለ ጠጋ አድርጎኛል” በሚል ሐስተሳሰብ ተመርተው ሀብትን የሚያሳድዱ ሰዎች የተሳሳቱ ናቸው” ብለዋል። ይህ ትልቅ ችግር የሚመነጨው ከሀብት ጋር ባለን ቁርኝት ምክንያት ነው ብለው ይህም የምያስገነዝበን “እግዚአብሔርን እና ሀብትን በእኩልነት ማገልገል እንደ ማይቻል ነው” ብለዋል። “የብልጽግና ሥነ-መለኮት” የሚለው ጽንሰ ሐሳብ ኢየሱስን በነጻነት እንዳንከተለው ወደ ኋላ ተብትቦ የሚይዘን ሰንሰለት ነው” ብለው አክለውም ሐዋሪያው ያዕቆብ እንደ ጻፈው “ይሁን እንጂ በእርሻችሁ ስያጭዱ ለዋሉ ሠራተኞች ዋጋቸውን ስላልከፈላችሁ እነሆ የተቃውሞ ጩኸታቸው ይሰማል፣ የመከር ሰብሳቢዎቻችሁን ጩኸት ኅያሉ እግዚአብሔር ስምቶታል” (ያዕ. 5:4) በማለት ፍርድን ማጉዋደል እንደ ማይገባ አበክረው ገልጸዋል።

ሕዝብን በመበዝበዝ ሀብትን በምናከማችበት ወቅት ሀብታም ሰዎች ሌሎች ሰዎችይበዘብዛሉ፣ የእነዚህን ድኾች ሰዎች ድካም ተጠቀመው እነዚህን ሰዎች ባሪያ ያደርጋሉ። እዚህም እና ዛሬም ቢሆን ይህ ተግባር በተመሳስይ መልኩ በዓለማችን ሁሉ ላይ እየተከሰተ ይገኛል።እኔ መሥራት እፈልጋለሁስትል እንርሱም " ጥሩ! ከመስከረም እስከ ሰኔ ድረስ ውል መፈረም ትችላለህ" ይሉኋል። ያለ ጡረታ አበል፣ ያለ ምንም የህክምና ዋስትና. . . ወዘተ ከእዚያም  ቡኋላ በሐምሌ እና በነሐሴ ወር ንፋስ ብቻ እንዲበሉ ይገደዳሉ (ከሥራ ያስወጡኋል)። እናም በመስከረም ወር ውስጥ እንደ ገና እነርሱ ላይ ይሳለቃሉ። ይህንን የሚተገብሩ ሁሉ ደም መጣጮች ናቸው፣ በሰው ደም ውስጥ ገብተው ሰዎችን የሥራ ባሪያዎች ስለምያደርጉ።

ቅዱስ አባታችን በስብከታቸው ወቅት አንዲት ሴት ልጅ እንዴት ሥራ እንዳገኘች ከነገረችኝ ታሪክ ላካፍላችሁ ብለው ይህቺ ልጅ ሥራ ካገኘች ቡኋላ በቀን 11 ሰዓት እንደምትሠራ እና በወር 650 ኤውሮ አሰሪዎችዋ እንከፍልሻለን  ካሉዋት ቡኋላ ከተስማማሽ ተቀበይ እና ሥሪ፣ አለበለዚያ ከእዚህ ጥፊ አሉዋት። ምንም ምርጫ አልነበራትም። ብዙ ሰዎች ደግሞ ተሰልፈው ይህንን እድል ለማግኘት ይጠባበቁ ነብር። “እነዚህ ሀብታም ሰዎች” አሉ ቅዱስነታቸው “በሀብታቸው ምክንያት ይሰባሉ” ነግር ግን ሐዋሪያው እንዲ ይላል “በምቾት እና በደስታ በመኖር ሰውነታችሁን ለእርድ እንደ ተዘጋጀ ሰንጋ አደልባችኋል” ““እናንተ በተድላ የኖራችሁበት እና  የመጠጣችሁት የእነዚህ የድኾች ደም ወደ እግዚአብሔር ለፍትህ ይጮኋል፣ ድኾችን መበዝበዝ” አሉ ቅዱስነታቸው “በዛሬው ጊዜ የሚታይ ትክክለኛ የባርነ ሥርዓት ነው” ብለዋል። “ምን አልባት በአሁኑ ወቅት ድኾች የሉም ብለን እናስብ ይሆናል፣ ነገር ግን በእውነትም አሁንም አሉ” ካሉ ቡኋል እንደ እዚህ ቀደም ሰዎች ወደ አፍሪካ በመሄድ ሰዎችን በመያዝ ወደ አሜሪካ መሸጥ እንደ ማይችሉ እሙን ቢሆንም ቅሉ ነገር ግን አሁንም ቢሆን ባርነት በከተሞቻችን ውስጥ ይገኛል ብዙ የሰው አዘዋዋሪዎችም ሰዎችን ላልተገባ ሥራ ሲማግዱ እና ስያስፈራሩ ይታያል ብለዋል። 

ቅዱስነታቸው በስብከታቸው ማጠቃለያ ላይ ጌታ ለሁላችን በተለይም ይህንን ዓይነት ድርጊት ለሚፈጽሙ ሰዎች ማስተዋልን እንዲሰጥ እጸልያለው ብለው በእግዚአብሔር ፊት አንድ ብርጭቆ ውሃ ለተጠማ መስጠት ድኾችን በመበደል ከሚገኝ ሀብት ሁሉ የሚበልጥ በረከት ብለው እግዚአብሔር ይህንን ማስተዋል የምንችልበትን ጸጋ ይስጠን ብለው ስበከታቸውን አጠቃለዋል።

 








All the contents on this site are copyrighted ©.