2016-05-24 14:24:00

ቅዱስነታቸው "ቅድስና ሊገዛ የሚችል ነገር ወይም ደግሞ በሰው ብርታት የሚገኝ ነገር አይደለም” ማለታቸው ተገለጸ።


ቅዱስ አባታችን ፍራንቸስኮ ዘወትር በቅድስት ማርታ የጸሎት ቤት ካህናት፣ ደናግላን እና ምዕመናን በተገኙበት መስዋዕተ ቅዳሴን እንደ ምያሳርጉ የሚታወቅ ሲሆን በዛሬው ቀንም ማለትም በግንቦት 16/2008 ባሰሙት ስብከታቸው “ያለ ነቀፋ በእግዚአብሔር ፊት ተመላለሱ” ብለው  ክርስቲያኖች በሕይወታቸው ወጤታማ መሆንን ከፈለጉ ብርታት፣ ተስፋን ማድረግ፣ ለውይይት እራሳቸውን መክፈት እና እንዲሁም በነጻነት የእግዚአብሔርን ፀጋ መቀበል ይኖርባቸዋል ማለታቸው ተገለጸ።

“ቅድስና ሊገዛ የሚችል ነገር  ወይም ደግሞ  በሰው ብርታት የሚገኝ ነገር አይደለም” በማለት ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው እኛ በእየቀኑ እንድንኖር የተጠራንበት እና ክርስቲያኖች ሁሉ በቀላሉ ሊተገብሩት የሚችሉት ቅድስና የሚገኘው አራት ዋና ዋና ተግባራትን በምንጎናጸፍበት ወቅት መሆኑን ገልጸው እነዚህ አራት ዋና ዋና ተግባራትም ጥንካሬ፣ ተስፋ፣ ፀጋ እና መለወጥ የሚሉ መሆናቸውንም አክለው ገልጸዋል።

በእለቱ በተነበበው የመጀመሪያ ምንባብ የመጀመሪያው የጴጥሮስ መልዕክት ምዕራፍ 1: 10-16 ሲሆን ይህም የምንባብ ክፍል ስለ ቅድስና በሚተነትነው ሀርግ ላይ ተመስርተው ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው ቅድስና ማለት “በእግዚአብሔር ፊት ያለነቀፋ መመላለስ ማለት ነው” ብለዋል።

“ቅድስና መንገድ ነው፣ ቅድስናን ልንሸምት አንችልም፣ ሊሸጥም አይችልም፣ በስጦታ መልክም ልናበረክተውም አንችልም። በአንጻሩም ቅድስና ማንም ሰው በስሜ ሊያደርገው የማይችል ወደ እግዚአብሔር የሚደረግ የግል ጉዞ ነው” ብለዋል። “ሌላ ሰው ቅዱስ ይሆን ዘንድ ልጸልይ እችል ይሆናል ነገር ግን ባሌበቱ እራሱ ነው ወደ ቅድስና መጓዝ ያለበት እንጂ እኔ አይደለሁኝም” ካሉ ቡኋላ “ስለእዚህ ማትረፍ እንድትችሉ በእግዚአብሔር ፊት ተመላለሱ” በማለት ጨምረው ገልጸዋል።

“የዕለት ተዕለት ቅድስና” አሉ ቅዱስነታቸው  "ስም-አልባ" ሊሆን ይችላል ነገር ግን ይህንን ለመጎናጸፍ ብርታት ያስፈልገናል ምክንያቱ “ወደ ቅድስና የሚደረግ ጉዞ ብርታት ያስፈልገዋል” በማለት አክለው ገልጸዋል።

“የኢየሱስ መንግሥት የሚገኘው” አሉ ቅዱስነታቸው በአጽኖት “በብርታት ወደ ፊት ለሚጓዙ ሰዎች ብቻ ነው” ብለው “ይህንን ብርታት ሊፈጠር የሚችለው ሁለተኛ ዋናው ወደ ቅድስና መንገድ እንድናመራ በሚረዳን “በተስፋ” አማካይነት መሆኑን አበክረው ገልጸው ይህ ተስፋ ኢየሱስን እንድንገናኝ ይገፋፋናል ብለዋል።

ሦስተኛው እና ወደ ቅድስና እንድናመራ የሚረዳን ነገር በቅዱስ ሐዋርያው ጴጥሮስ የተጠቀሰው “ተስፋችሁን ሁሉ በጌታ ፀጋ ላይ አድርጉ” የሚለው ቃል ነው ብለው “ቅድስናን በፍጹም ብቻችንን ልንጎናጸፈው የምንችለው ነገር እንዳልሆን ላረጋግጥላችሁ እፈልጋለው ብለው በአንጻሩም “መልካም እንድንሆን፣ ቅዱሳን እንድንሆን እንዲሁም በየቀኑ ቀስ በቀስ በክርስትና ሕይወታችን ወደፊት እንድንራመድ የምያደርገን የእግዚአብሔር ፀጋ በመሆኑ ይህንን ፀጋ ከእግዚአብሔር መጠየቅ ያስፈልጋል ብለዋል። ብርታት ወደ ፊት መጓዝ ማለት ነው፣ አንድ ሰው በብርታት የምያደርገው ጉዞ፣ በተስፋ እና በፋቃደኝነት የእግዚአብሔርን ፀጋ ለመቀበል የሚደርገ ጉዞ ነው፣ ተስፋ የተስፋ ጉዞ ነው” ብለዋል።

ቅዱስነታቸው አጋጣሚወን ተጠቅመው በስርዓተ ቅዳሴ ላይ ለተገኙ ሁሉ በጣም “ግሩም” በማለት ያወደሱትን ወደ ሕብራዊያን የተጻፈውን መልዕክት ከምዕራፍ 11 የተወሰደውን “በመጀመሪያ የቀድሞ አባቶቻችን በእግዚአብሔር ተጠርተው ነበር”። “አባታችን አብራሃም” አሉ ቅዱስነታቸው “ ወዴት እንደሚሄድ ባያውቅም እንኳ በትስፋ ነበር የተጓዘው” የሚለውን ሁሉም እንድያነቡት ጋብዛለው ብለዋል።

ቅዱስነታቸው በማስከተለ ወደ ዋና ፍሬ ሐሳባቸው በመመልስ እና አራተኛውን እና ለቅድስና ይጠቅማል ያሉትን ፍሬ ነገር ከቅዱስ ጴትሮስ በተወሰደው ምንባብ ላይ ተመርኩዘው “በእየ ጊዜው ልብን ለማንጻት የሚደረግ የለውጥ ጉዞ መሆኑን”  ገልጸዋል።

“በተቀኑ የሚደርገ ለውጥ” አሉ ቅዱስነታቸው ስህተትን በሠራን ቁጥር እራሳችንን በሱባዔ መቅጣት ማለት አይደለም” ብለው ነገር ግን በየቀኑ የምናደርጋቸው “ጥቃቅን ተጋድሎዎችን ያካተተ ነገር መፈጸም ማለት ነው” ካሉ ቡኋላ ለምሳሌም “ስለ ሰዎች ክፉ ነግሮችን የማታወራ ከሆንክ ይህ በእራሱ ወደ ቅድስና መንገድ እያመርህ መሆኑን ያሳያል፣ በጣም ቀላል ነገር ነው ይህንን ማድረግ!! ስለ ሰዎች ክፉ ትናገራላችሁ ብዬ አላስብም እውነት ነው አይደል? ይህንን የመሳሰሉ ጥቃቅን ነገሮች . . .ባልጀራን እና አብሮን የሚሠራውን ሰው ከመንቀፍ. . .ትንሽ ምላሳችንን መቅጣት ይጠበቅብናል። ምላሳችን እንድ አንዴ ያብጣል ነገር ግን መንፈሳዊ ጉዞዋችን ግን ከእዚህ በተሻለ ቅዱስ ነው። ትላልቅ የሚባሉ በስዋዕቶችን መክፈል ሳይሆን እነዚህን ጥቃቅን ነገሮች መፈጸም ይጠበቅብናል። ወደ ቅድስና የሚደረግ ጉዞ በጣም ቀላል ነው። ወደ ኋላ አትመለሱ ነገር ግን በጽናት ወደ ፊት ተጓዙ” ብለው የእለቱን ስብከት አጠናቀዋል።   

 








All the contents on this site are copyrighted ©.