2016-05-24 10:58:00

ቅዱስ አባታችን ፍራንቸስኮ ሀገራቸውን በመወከል ለቅድስ መንበር የተሾሙትን የልዑካን ቡድን የሹመት ደብዳቤን ተቀበሉ።


ቅዱስ አባታችን ፍራንቸስኮ በግንቦት 11/2008 ሀገራቸውን በመወከል ለቅድስ መንበር የተሾሙትን የኢስቶኒያ፣ የማላዊ፣ የናሚብያ፣ የሲሼልስ፣ የታንዛኒያ እና የዛንቢያ አባሳደሮችን የሹመት ደብዳቤን በቫቲካን በሚገኘው የክሌሜንት የስብሰባ አዳራሽ በተቀበሉበት ወቅት ባሰሙት ንግግር ይህ የዲፕሎማሲ ግንኙነት ለሰው ዘር በጋራ የምንሰጠው ተጨባጭ አገልግሎት ማሳያ ነው ማለታቸው ተገለጸ።

 “ይህ አገልግሎት” አሉ ቅዱስነታቸው “አሁን በዓለማችን ላይ ለሚታየው ስቃይ፣ ጦርነት፣ ስደት፣ መፈናቀል እና የኢኮኖሚ ችግሮችን በአስቸኳይ መፍትሄ እንድናበጅ ያሳስበናል” ማለታቸውም ተገልጹዋል። ቅዱስነታቸው በማከልም “በእነዚህ ችግሮች ላይ ማሰብ እና መወያየት ብቻ በቂ አይደለም” ብለው “ነገር ግን በአሳሳቢ ሁኔታ ለይ የሚገኙ ወንድሞቻችንን እና እህቶቻችንን ለመርዳት ተጨባጭ እርማጃ መውሰድ ይጠበቅብናል” ብለዋል።

ቅዱስነታቸው በንግግራቸው ወቅት ስለ ሰላም ትኩረት ሰጥተው እንደነበረ የታወቅ ሲሆን በተለይም ሰላምን በየሀገራት ውስጥ እንዴት ማጠናከር እንደ ሚቻል እና የዓለም ሀገራት በተለያዩ ሀገራት ውስጥ በእየጊዜው  የሚፈጠሩትን ውጥረቶች ለማርገብ እና ውጤታማ የሆኑ የግጭት አፈታት ዘዴዎችን እንዲዘይዱ እና መላውን የማኅበረሰብ ክፍሎችን ከሚያጠፋው እና ከቤት ንብረታቸው ከሚያፈናቅላቸው ግጭቶች ልንታደጋቸው ይገባል ብለዋል።

ቅዱስነታቸው በማከልም እንደ ገለጹት “አሁን እኛ እያሳየነው ያለው ለሰላም ተነሳሽነት ሰዎች በቄያቸው በሰላም እንዲኖሩ አስተዋጾ የሚያደርግ ቢሆንም በአሁኑ ወቅት የሚታየው ሁኔታ ስደተኞችን እና እነርሱ እየተንከባከቡ የሚገኙትን ሁሉ መርዳት እንደ ሚኖርብን መገንዘብ እንጂ ጥረታችንን ለሚያዳክም ፍርሃት እና አለመግባባት መንበርከክ የለብንም” ብለው “ይልቅ እኛ የተጠራነው ቀርቦ የመነጋገርን ባሕል ለማዳበር እና የባዕድን ሀገር ማክበር የምያስችል አጋርነትን በመፍጠር ከተለያዩ ባህሎች የተውጣጡ ስደተኞችን እና የተለያዩ የማኅበረሰብ ክፍሎችን በመስማት መኖር የሚችሉበትን ሁኔታ መፍጠር ይኖርብናል ያሉት ቅዱስነታቸው “ይህንን ስናደርግ ብቻ ነው ሰላምን ልናመጣ የምንችለው እና ስደተኞች የተቀበሉዋቸውን ሀገራት ባሕል እንድያከብሩ እና ውህደትን ማምጣት እና የሁለቱንም ባሕል ማዳበር የምንችለው ብለዋል።

ቅዱስነታቸው በማጠቃለያ ንግግራቸው እንዚህን አዳዲስ ተሹዋሚ የልዑካን ቡድንን በድጋሚ ሰላምታን አቅርበው በየሀገራቸው ለሚገኙ መንፈሳዊ መጋቢዎች እና የካቶሊክ ማኅበረሰቦች ሰላምታቸውን እንድያደርሱላቸው ተማጽነው ሁሉም የካቶሊክ ማኅበረሰብ ሰላምን እና ተስፋን ያበስሩ ዘንድ አደራ ካሉ ቡኋላ የእናንተ መሾም የቅድስት መንበርን አገልግሎ የሚያጠናክር ነው ብለው ከየወከላዋቸው  ሀገራት ጋር ግልጽ የሆነና መከባበር ላይ የተመሰረተ ወይይቶችን እንድናደርግ እና ገንቢ የሆነ ትብብሮችን እንድናከናውን በር የሚከፍት አጋጣሚ ነው በማለት ንግግራቸውን አጠናቀዋል። 

 








All the contents on this site are copyrighted ©.