2016-05-19 10:49:00

ቅዱስነታቸው "ክርስቲያኖች የዓለምን እና የሰው ምኞት ያለውን የማታለል ኃይል ማሸነፍ ይኖርባቸዋል" ማለታቸው ተገለጸ።


በግንቦት 9/2008 በቅድስት ማርታ የጸሎት ቤት ካህናት፣ ደናግላን እና ምዕመናን በተገኙበት ቅዱስ አባታችን ፍራንቸስኮ ባሳረጉት ስርዓተ ቅዳሴ ላይ ባሰሙት ስብከት እንደ ገለጹት ክርስቲያኖች የዓለምን እና የሰው ምኞት ያለውን የማታለል ኃይል በማሸነፍ እና እንዲሁም ሌሎችን ወይም አቅመ ደካማ የሆኑ ሰዎችን በማጥፋት እና በመበደል እራሳቸውን  ከፍ ያለ ቦታ ለማድረስ ከመፈለግ  እንዲቆጠቡ አሳስበዋል።

በእለቱ  ከማርቆስ ወንጌል ከምዕራፍ 9:30-37 በተነበበው እና ሐዋሪያት ከሁላችን የሚበልጥ ማን ነው? ብለው እርስ በእርሳቸው ይወያዩ እንደ ነበር በሚያወሳው ታሪክ ላይ ተመስርተው ቅዱስነታቸው ባደረጉት ስብከት ስልጣን ወይም የበላይ ለመሆን መፈለግ በጣም አደገኛ ነገር መሆኑን ገልጸው የእነዚህ ነገሮች ሁሉ ምንጭ የሆኑት ገንዘብ፣ ሥልጣን እና ሕብሪት መሆናቸውን በአጽኖት ገልጸዋል።

በመቀጠልም ኢየሱስ ለሐዋሪያቱ እንደ ገለጸው እና ወደ እዚህ ምድር የመጣበት ዋነኛው ዓላማ እራሱን በማዋረድ፣ ሞቶ እኛን ለማዳን ነበር ያሉት ቅዱስነታቸው በአንጻሩም የሐዋሪያቱ ጭንቀት ከሁላችንም የሚበልጥ ማነው? የሚል  ዓለማዊ እና ከንቱ ሐሳብ እንደ ነበረ ጨምረው ገልጸዋል።

በመቀጠልም ቅዱስነታቸው ሐዋሪያቱ ከሁላችን ማን ይበልጣል? ብለው ላቀረቡት ጥያቄ ኢየሱስ ሐዋርያቱን በማስጠንቀቅ የመለሰላቸው “መጀመሪያ መሆን የሚፈልግ ማንኛውም ሰው የሁሉም መጨረሻና የሁሉም አገልጋይ መሆን አለበት” ብሎ መልሶ ነበር ብለዋል። ኢየሱስ እንድንጓዝበት የሚያሳየን መንገድ ዋናውና መሰረታዊ መርህ ‘አገልግሎት ነው’” በማለት ስብከታቸውን የቀጠሉ ቅዱስነታቸው “ከሁሉም የሚበልጠው አብዝቶ ሌሎችን የምያገለግል ሰው ነው እንጂ ስልጣን ፈላጊ፣ ገንዘብ የምያካብት፣ እብሪተኛ እንዲሁም የሚኩራራ ሰው አይደለም፣ እንደ እነዚህ አይነት ሰዎች በፍፁም ትልቅ ሊባሉ አይችሉም” ብለዋል።

“ይህ እውነታ በሐዋሪያቱ፣ እንዲሁም በዩሐንስ እና በያዕቆብ እናት ላይ ተንጸባርቆ ነበር “ ብለው “ በተጨማሪም በየቀኑ በቤተክርስቲያናችን ውስጥ እና በማሕበረስብ ውስጥም ይህ በሕሪ እንደሚታይ” ገልጸዋል። “ነገር ግን ማንኛችን ነን ትልቅ? ማነው ኋላፊ? ሁልጊዜም ቢሆን በማሕበረሰብ ውስጥ፣ በቤተክርስቲያን እና በማዕከላት ውስጥ ከሁሉም የበላይ ለመሆን እና ስላጣን እንዲኖረን እንቋምጣለን” ብለዋል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ  በስብከታቸው ልያስጨብጡን የፈለጉት እውነታ አገልግሎት በዛሬው ጊዜም ቢሆን የቤተክርስቲያን ዋነኛው መልእክት መሆኑን ሲሆን ዓለም ከሁሉም የሚበልጥ ማን ነው? ብሎ በሚደሰኩርበት ወቅት ኢየሱስ ግን እኔ የመጣሁት “ለማገልገል” እንጂ “ልገለገል አይደለም” የሚለውን ጽንሰ ሐሳብ ልይስጨብጡን ስለፈለጉ ነው።

“ሕብሪት፣ ስልጣን . . .ወዘተ” አሉ ቅዱስነታቸው “ለማገልገል ሳይሆን ለመገልገል  መቼ እና እንዴት የእዚህን ዓለም ስልጣን እጨብጣለው? ምን ዓይነት ጥረት ባደርግስ ነው እዚያ ደረጃ ላይ የምደርሰው? በሃሜት ስለሌሎች ክፉ ነግሮችን በመናገር. . . ወዘተ ወይስ እዴት ነው? በምቀኝነት እና በቅናት ? እነዚህ መንገዶች ሁሉ የጥፍት መንገዶች መሆናቸውን ሁላችንም እናውቃለን” ብለዋል። “እነዚህ እውነታዎች በእየለቱ በቤተክርስቲያን ተቋማት፣ በቁምስናዎች፣ በሀገረ ስብከቶች እና በአጠቃላይ በተለያዩ ማዕከላት ውስጥ ይንጸባረቃሉ” ያሉት ቅዱስነታቸው “ሁል ጊዜም ቢሆን ሀብትን ለማግኘት፣ ሕብሪት እና ኩራት ለእነዚህ ዓለማዊ ፍላጎቶች ምኞታችንን እናሳያለን” ብለዋል።

“ኢየሱስ ለማገልገል ነው የመጣው” በሚለው አረፍተ ነገር ላይ ተመስርተው ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው  ክርስቶስ እውነተኛውን የክርስትና መንገድን አሳይቶናል ይሄውም አገልግሎት እና ትሕትና መሆኑን ገልጸው ታላላቅ የሚባሉ ቅዱስና እንኳን ‘እኔ ኋጥያተኛ ሰው ነኝ’ ይሉ የነበረበት  ዋነኛው ምክንያት እነዚህ ዓለማዊ ፍላጎቶች እና ፈተናዎች በሕይወታቸው ይታዩ ስለነበር መሆኑን ገልጸው ማንም ሰው ቢሆን አሉ ቅዱስነታቸው በአጽኖት “እኔ ቅዱስ እና ንጹህ ሰው ነኝ” ሊል አይችልም ብለዋል።

ቅዱስነታቸው በስብከታቸው ማጠቃለያ ላይ እንደ ገለጹት “ሁላችንም ብንሆን በእነዚህ ነገሮች እንፈተናለን፣ ሌሎችን አጥፍተን እና እነርሱን ተንተርሰን ትልቅ ቦታ መድረስን እንመኛለን” ብለው “ይህም ዓለማዊ አስተሳሰብ የሚከፋፍል እና ቤተክርስቲያንን የሚያፈርስ ተግባር ነው” ብለዋል።

“ነገር ግን ይህ የኢየሱስ ፍላጎት እና ሐሳብ እንዳልነበር ሐዋሪያቱም ተረድተውት ይህንን ጉዳይ በተመለከተ ሌላ ጥያቄ ማቅረብ እንኳን አልደፈሩም ነበር” ብለው “እኛም ብንሆን ብዙን ጊዜ ይህንን ዓይነት ጥያቄ ኢየሱስን ጠይቀነው ሊሆን ይችላል” ካሉ ቡኋላ ትክክለኛውን መንገድ ጌታ ያሳየን ዘንድ ልንጠይቀው እንደ ሚገባ እና በተለይም የእዚህ ዓለም ፍቅር ማለት ዓለማዊነት ማለት መሆኑን ተገንዝበን ይህም ዓለማዊነት ከእግዚአብሔር ጋር የሚያቃርን መሆኑን በማወቅ ከእዚህ ዓይነት መንፈሶች መላቀቅ እንድንችል ይረዳን ዘንድ ጌታን ልንለምነው ያስፈልጋል ብለው ስብከተ ወንጌላቸውን አጠናቀዋል።

 

 

 

 

 








All the contents on this site are copyrighted ©.