2016-05-17 10:43:00

ቅ. አ. ፍራንቸስኮ ከሰኔ 17-19/2008 የሦስት ቀን ጉብኝት ለማድረግ ወደ አርሜንያ እንደ ሚሄዱ ተገለጸ።


ቅዱስ አባታችን ፍራንቸስኮ ከሰኔ 17-19/2008 የሦስት ቀን ጉብኝት ለማድረግ ወደ አርሜንያ እንደ ሚሄዱ ተገለጸ። በሬዲዮ ቫቲካን ይፋ የሆነው ኦፊሴላዊ የጉብኝታቸው መረሃ ግብር እንደ ምያሳየው በሮም ሰዓት አቆጣጠር ከጥዋቱ 9:00 AM ከሮም አለማቀፍ አየር ማረፊያ ፉሚችኖ ተነስተው በተመሳስይ ቀን የስድስት ሰዓት በረራን ካደረጉ ቡኋላ የአርሜንያ ዋና ከተማ የረቫን በመድረስ በእዚያው አቀባበል ይደረግላቸዋል።

በአርሜንያ የሰዓት አቆጣጠር ከሰዓት ቡኋላ 3: 35 PM ላይ በየረቫን የካቶሊክ ካቴድራል በመገኘት የአጠቃላይ የአርሜንያ የካቶሊክ አብያተ ክርስቲያናት መሪ ከሆኑ ፓትርያርክ ካሬኪን 2ኛ ጋር ተገናኝተው ሰላምታን ይለዋወጣሉ።

በሀገሩ የሰዓት አቆጣጠር 6:00 PM ላይ በሀገሪቱ ቤተ መንግሥት በመገኘት ከሀገሪቱ ፕሬዚዴንት ጋር ይገናኛሉ።

በሀገሩ የሰዓት አቆጣጠር 6:30 PM ላይ ከሀገሪቷ ባለስልጣናት ጋር እና ከተለያዩ ሀገራት ከተውጣጡ የዲፕሎማሲ አካላት ጋር ቅዱስነታቸው ተገኝተው  በእዚያው ንግግር ያደርጋሉ።

ከምሽቱ 7:30 PM ላይ የአርሜንያ የካቶሊክ አብያተ ክርስቲያናት መሪ ከሆኑ ፓትርያርክ ካሬኪን 2ኛ ጋር ተገናኝተው የግል ውይይት ያደርጋሉ።

ቅዳሜ ማለትም በሰኔ 18/2008 ጋይመሪ በምትባል የአርሜንያ ከተማ አደባባይ በመገኘት ስርዓተ ቅዳሴን የአርሜንያ የካቶሊክ አብያተ ክርስቲያናት መሪ ከሆኑ ፓትርያርክ ካሬኪን 2ኛ ጋር እንደ ሚያሳርጉ የታወቀ ሲሆን በእለቱም ቅዱስነታቸው ስብከተ ወንጌልን ስያደርጉ የአርሜንያ የካቶሊክ አብያተ ክርስቲያናት መሪ የሆኑ ፓትርያርክ ካሬኪን 2ኛ ደግሞ የመግብያ ንግግር ያደርጋሉ።

ከሰዓት ቡኋላ 4:45 PM ላይ በጋይመር በሚገኘው ካቴድራል በመገኘት በእዚያ ያረፈውን የአርሜንያ ቅዱሳን ሰማዕት አጽም ከጎበኙ ቡኋላ  ማምሻውን ወደ ዋና ከተማይቱ የረቫን ከተመለሱ ቡኋላ ከምሽቱ 7:00 PM ላይ በየረቫን አደባባይ በመገኘት ከተለያዩ አብያተ ክርስቲያን ከተውጣጡ የአብያተ ክርስቲያን ሕብረት አባላት ጋር ተገናኝተው ለሰላም ጸሎት ያሳርጋሉ።

እሁድ እለት ማለትም በሰኔ 19/2008 ላይ ከጥዋቱ 9: 15 AM ላይ በአርሜንያ ከሚገኙ የካቶሊክ ጳጳሳት ጋር ተገኝተው ከተወያዩ ቡኋላ በ10:00 AM ላይ የእለቱን ስራዓተ ቅዳሴን ያሳርጋሉ። ቅዱስነታቸው ስብከተ ወንጌልን ስያደርጉ የአርሜንያ የካቶሊክ አብያተ ክርስቲያናት መሪ የሆኑ ፓትርያርክ ካሬኪን 2ኛ ደግሞ የመግብያ ንግግር ያደርጋሉ።

ስርዓተ ቅዳሴ ካበቃ ቡኋላ የካቶሊክ አብያተ ክርስቲያናት መሪ በሆኑት ፓትርያርክ ካሬኪን 2ኛ መኖሪያ ቤት በመገኘት ከጳጳሳት ጋር ሆነው ምሳ ከተቋደሱ ቡኋላ የጋራ መግለጫን በማውጣት እና የአሸኛኘት ስነ ስርዓት ከተደርገላቸው ቡኋላ ከምሽቱ 6:30 PM ወደ ሮም እንደ ሚመለሱ ለቫቲካን ሬድዮ ከደረሰው የጉብኝታቸው መርሃ ግብር ለመረዳት ተችሉዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.