2016-05-14 11:39:00

የግንቦት ወር ለየት ባለ ሁኔታ ለእናታችን ቅድስት ድንግል ማሪያም ፀሎታችንን የምናቀርብበት ወር ነው።


ይህ የያዝነው የግንቦት ወር ለእናታችን ለቅድስት ማሪያም ለየት ባለ ሁኔታ ጸሎት የምናቀርብበት ወር እንደሆነ ሚታወቅ ሲሆን በተለይም እንደ አውሮፓዊያን የቀን አቆጣጠር ግንቦት 5,2008 በፖርቹጋል ሀገር ፋጢማ በሚባል መንደር የዛሬ አንድ መቶ ዓመት ገደማ የመቁጠሪያዋ እናታችን ቅድስት ድንግል ማሪያም እንደ አውሮፓዊያን የቀን አቆጣጠር በ1917 ለሦስት እረኛ ልጆች የተገለጠችበት ቀን ይታወሳል።

በወቅቱ ፖርቹጋል እና የተቀረው ዓለም በጦርነት ውስጥ በነበሩበት ወቅት የመቁጠሪያዋ እናታችን ቅድስት ድንግል ማሪያም ለእነዚህ ሦስት እረኛ ሕጻናት በመገለጸ ሁሉም የዓለም ሕዝቦች ንስሐን በመግባት እና የመቁጠርያን ጸሎት አዘውትረው በመጸለይ ለዓለ ሰላም እንዲመጣ መጣር እንዳለባቸው ቅድስት ድንግል ማሪያም ባሳሰበችሁ መሰረት ዛሬም ቢሆን በሚልዮን የሚቆጠሩ ነጋዲያን በፖርቹጋል ሀገር ፋጢማ በሚባለው ስፍራ በመገኘት ለግል እና ለዓለም ሰላም ይመጣ ዘንድ በእናታችን ቅድስት ድንግል ማሪያም አማላጅነት ጸሎታቸውን ወደ እግዚኣብሔር እያሳረጉ ይገኛሉ።

ከእነዚህም ነጋዲያን መካከል ግናባር ቀደም ሊባል በሚችል መልኩ ብዙን ጊዜ ወደ ፋጢማ ንግደት በማድረግ የሚታወቁት ቅዱስ ዩሐንስ ጳውሎስ ሁለተኛ ይገኙበታል። ቅዱስ የሐንስ ጳውሎስ ሁለተኛ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት በነበሩበት ወቅት ለሳምንታዊው የጠቅላላ አስተምህሮ ምዕመናን እና የሀገር ጎብኚዎች በተገኙበት በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ በሚዘዋወሩበት ወቅት መሐመድ አሊ በተባለ ቱርካዊ እንደ አውሮፓዊያን የቀን አቆጣጠር በግንቦት 13,1981 አራት ጊዜ በጥይት ተመተው የወደቁበት ቀነ፣ የመቁጠሪያዋ ማሪያም ለእነዚህ ሦስት ሕጻናት እረኞች ከተገለጠችበት ቀን ጋር በመገጣጠሙ ከእዚህ ክፉ አደጋ ከሞት የተረፍኩት በፋጢማዋ ቅድስት ድንግል ማሪያም አማላጅነት ነው ብለው አምነው እስከ ሕይወታቸው ፍጻሜ ድረስ ከፍተኛ የሆነ አክብሮት እና ፍቅር ለቅድስት ድንግላ ማሪያም በማሳየት ይህንንም እምነታቸውን የመቁጠሪያን ጸሎት አዘውትረው በመጸልይ ተግብረውታል።

እንደ አውሮፓዊያን የቀን አቆጣጠር በግንቦት 13,2000 ቅዱስ ዩሐንስ ጳውሎስ ሁለተኛ ለመጨረሻ ጊዜ ቅድስት እናታችን ማሪያም የተገለጠችበትን የፋጢማን ቅዱስ የንግደት ስፍራ መጎብኘታቸው እና እናታችን ቅድስት ድንግል ማሪያም በሕይወታቸው ላደረገችላቸው ጥበቃ እና አማላጅነት ምስጋናን አቅርበው እንደ ነበር ይታወቃል። በእዚህ የመጨርሻ ጉብኚታቸው ወቅት እንደ አውሮፓዊያን የቀን አቆጣጠር በ1917 ቅድስት ድንግል ማሪያም ከተገለጸችላቸው ሦስት ሕጻናት እረኞች መካከል ብቸኛዋ በሕይወት የነበረችሁ ሉቺያ በእለቱ እንደ ነበርች እና ከእዚያም ከጥቂት ዓመታት ቡኋላ ማረፏም ታልቅ ምስክርነትን ጥሎ ያለፈ ወቅት እንደነበር ይታወሳል።








All the contents on this site are copyrighted ©.