2016-05-13 16:22:00

የቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ቃለ ምዕዳ ለዓለም አቀፍ የደናግል ማኅበራት ጠቅላይ አለቆች ጉባኤ


እ.ኤ.አ. ግንቦት 12 ቀን 2016 ዓ.ም. ቅዱስ ኣባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ የመላ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን የደናግሎ ች ማኅበር ጠቅላይ አለቆች ጉባኤ በአገረ ቫቲካን በሚገኘው ጳውሎስ ስድተኛ የጉባኤ አዳራሽ ተቀብለው መሪ ቃል መለገሳቸው የቫቲካን ረዲዮ ልኡክ ጋዜጠኛ አለሳንድሮ ደ ካሮሊስ ገለጡ፡

ቅዱስ አባታችን መሪ ቃሉን የለገሱት የደናግሎች ማኅበራ ጠቅላይ አለቆች ጉባኤ አባላት በቀጥታ ባቀረቡላቸው ጥያቄዎች ላይ የተመረኰዘ ሲሆን። ቅዱስ አባታችን ደናግሎች ሴተኝነት ከሚለው ልቅ እርሱም የእኩልነት መብት ከሚለው የሰብአዊ መብትና ክብር ላይ ከሚጸናው የእኩልነት ጥያቄ ጋር  ምንም ዓይነት ግኑኝነት ከሌለው ያክራሪነት መንፈስ ሴት የበላይነት ከሚለውና በተቃራኒውም ተገዢነት ከሚለው አመልካከት ነጻ ሊሆኑ ይገባቸዋ እንዳሉና ቤተ ክርስቲያን የአንስት ፆታ ብልህነት ልባምነት በሥልጣናዊ ትምህርቷ ሥር አቢይ ግምት አየሰጠችበት መምጣቷን የሚታይ እውነት ሲሆን ቅዱስ አባታችን ህያው ምስክር ናቸው።

የቤተ ክርስቲያን አንስታዊ እይታ

ሴቶች በቤተ ክርስቲያን የበላይ ወሳኝ አካል አባል ማድረግ። በተለያዩ የቤተ ክርስቲያን ተቋማትና አበይት መዋቅሮች ሴቶች በኃላፊነት ሊቀመጡ እንደሚችሉ ነው፡ ይኸንን ሃሳብ ቅዱስነታቸውም የሚደገፉት መሆናቸው ሲገልጡ። ነገር ግን ይኽ ሃሳብ ማዕርገ ክህነት ጋር ምንም የሚያገናኘው  ነገር የለም። በአቢይ ኃላፊነት መቀመጥና ማዕርገ ክህነት መቀበል ግዳዊ ትስስር እንደሌለውም አብራተው ፡ የአንዲት ሴት መንፍሳዊ ስነ አእምሮአዊ ወዘተ ያላት አመለካከ ከወንድ አመለካከት የተለየ ነው የተለየ ሲባል የበታች ማለት አይደለም፡ ስለዚህ የሴቶች እይታ ለቤተ ክርስቲያን አቢይ አስተዋጽኦ እንዳለውም ጠቅሰው፡  ይኽ እይታ ቤተ ክርስቲያን በአበይት ውሳኔዎችዋና በሥራ አስፈጻሚ ጉዳይ ሥር ሊሆን እንደሚችል ነው እንዳሉ ደ ካሮሊስ አመለከቱ።

ለሴቶች ቋሚ ማዕርገ ድቁና የሚለው ጥያቄ የሚያጠና ልዩ ድርገት ያለው አስፈላጊነት

ደናግሎች በቤተ ክርስቲያን በግብረ ሠናይ ኅሙማንን በማገልገል በትምህር ተክርስቶስ አስተማሪነት በተለያዩ የቤተ ክርስቲያን ያገግሎት ዘርፍ ተሰማርተው አቢይ አስተዋጽኦ እየሰጡ መሆናቸው ያስታወሱት ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ከዚሁጋር በማያያዝ ብዙውን ጊዜ ደናግሎች የሚያቀርቡት ጥያቄና በተካሄደው ግኑኝነት የቀረበላቸው ጥያቄ ተንተርሰው ቋሚ ማዕርገ ድቁና በቤተ ክርስቲያን የመጀመሪያ ዓመታት ማለትም በጥንቱ ሴቶች ዲያቆናት በመሆን ያገለግሉ እንደነበር የቤተ ክርስትያን ታሪክና አንዳንድ የቅዱስ ጳውሎስ መልእክቶች ያረጋግጡልናል። ስለዚህ ቋሚ ማዕርገ ድቁና ለሴቶች በቤተ ክርስቲያን የተፈቀደ ይሁን ለሚለው ጥያቄ ተገቢ ውሳኔ ለመስጠት እንዲቻል ይኽንን ጉዳይ የሚያጠና ልዩ የአጥኚዎች ድርገት ማቆም ያስፈልጋል እንዳሉ ደ ካሮሊስ ገልጠዋል።

ሴቶችና በቅድሴ ሥነ ስርዓት ሰባኪነት

ዓለም አቀፍ የደናግሎች ማኅበር ጠቅላይ አለቆች ጉባኤ አባላት፥ በቅዳሴ ሥነ ስርዓት ደናግሎች እንዲሰብኩ ለምን አይፈቀድላቸውም በማለት ላቀረቡት ጥያቄ ቅዱስ አባታችን ሲመልሱ፥ ጥያቄውን ለሁለት በመከፋፈል፡ በቃለ እግዚአብሔር ሊጡርጊያ አለ ምንም ችግር ድንግልም ትሁን ዓለማዊ ምእመን ሴት ሌላው ተባዕት ምእመን ሰብከት ልታቀርብ ሊያቀርብ ትችላለች ይችላል። ነገር ግን በቅዳሴ ሥነ ሥርዓት ሰባኪነት ወይንና እንጀራውን ወደ የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሥጋና ደም ለሚለውጠት ካህን የሚመለከት አገልግሎት ነው ብለው፥ ደናግሎቹ ከሴተኝነት አመለካከት አክራሪነት መጠንቀቅ ያስፈልጋል። በቤተ ክርስቲያን የምትኖር ሴት ያላት ክብር እንደ ሁሉም በቤተ ክርስቲያን እንደሚኖር ተባዕት ከጸጋ ጥምቀት የመነጨ ክብር ነው፡ በማያያዝም ክህነተኝነት ማእከል በማድረግ አንድ ካህን ለብቻው የቁምስና መሪ በማድረግ ሌሎችን በማግለል የሚደረገው አሠራር መወገድ ይኖርበታል፡ ዓለማውያን ምእመናንም ኣንዲመቻቸው ብለው በክህነተኝነት አመለካከት እይዳመሩ አደራ፡ ስለዚህ በቤተ ክርስቲያን ትብብርና መተባበር ሊኖር ያስፈልጋል እንዳሉ ደ ካሮሊስ አስታወቁ።

ውሳኔ በሚሰጥበት ኅላፊነት የሴቶች ኅልውነት

ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በቤተ ክርስቲያን ሕይወት የደናግሎች ሱታፌ ከተመለከተው ርእስ ጋር አዛምደው፡ የእነርሱ ማለትም የደናግሎች በቤተ ክርስትያን ውሳኔ በሚሰጥበት ኃልፊነት ዙሪያ ኅልዋን እንዲሆኑና በዚህ ብቻ ሳይታጠር የተለያዩ ውሳኔዎች በሚሰጡባቸውና ውሳኔ ለማስተላለፍ ውይይት በሚካሄድባቸው የቤተ ክርስቲያን የበላይ መዋቅሮች ግባኤ ውስጥ ቦታ ሊኖራቸው ይገባል እንዳሉ የገለጡት የቫቲክን ረዲዮ ልኡክ ጋዜጠኛ ደ ካሮሊስ አክለው፥

አገልጋዮች እንጂ ባሮች አይደላችሁም

ቅዱስ አባታችን ደናግሎችና የውፉያን ማኅበር አባላት ሴቶች የሚኖሩት የእናትነት ባህርይ በቤተ ክርስቲያን እርሱም ድኾች የተገለሉትን የተገፉትን ለመንከባከብ በሚሰጡት አገልግሎት የሚገልጡት መሆን እንደሚገባው አብራርተው ሆኖም የሚሰጡት አገልግሎት በተንከባካቢነት ግብረ ሠናይ ብቻ አጥሮ ማስቀረቱ ወይንም በመናብርተ ጳጳሳት ውስጥ የሚሰጡት አገልግሎት የባርነት ግልጋሎት አተደርጎ መታየት የለበትም።

ለመላ ሕይወት የሚኖር ጥሪ

በርግጥ በአሁኑ ሰዓት በወጣነት እድሜ እያለ ለመላ ሕይወት ለሚኖር ጥሪ ታማኝ ሆኖ ለመኖር እጅግ እየከበደ መጥቷል ይኸንን ሃሳብ የፍቅር ሓሴት በሚል ርእስ ሥር በደረሱት ድኅረ ሲኖዶሳዊ ምዕዳን ዘንድ የመለየት ወይንም የማስተዋል ጥያቄ ጋር በማዘበድ እንዳብራሩት አስታውሰው። ከዚህ ጋር በማያያዝ ቅዱስ ቪንቸንሶ ደ ፓውሊ አለ ምክንያት አልነበረም ጊዚያዊ ማሕላ የመረጠው።

መንፈሳውያን ማህበራትና ገዳማውያን የሚኖሩት ሕይወት የድኽነት ሕይወት ነው። ስለዚህ የድኽነት እሴት አቃቢያን መሆን ይጠበቅባቸዋል። ምንም’ኳ የማኅበር ንብረት በሚገባ ማስተዳደር የሚያስፈግል ቢሆንም ቅሉ ይኽ ጉዳይ ለሃብታመኛ ኑሮ የሚከጅል መሆን የለበትም እንዳውም ድኽነት ያለው የላቀው እሴት ለመመስከርን በድኽነት የተጠቃውን በሚገባ ለማገልገል የሚደገፍ መሆን አለበት እንዳሉ ደ ካሮሊስ ያመለክታሉ።

ሰቂለ ህሊናዊ ጸላይ ሕይወት፡ ሬሳ መሆን ማለት አይደለም

ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ በቤተ ክርስቲያንና በመንፈሳዊ ማኅበራት ዘንድ የሚኖረው ንቁ ማኅበራዊነት ጠቅሰው ብዙ የውይፉ ሕይወት አባላት በድኽነት ጫንቃ ሥር ለተጠቃው ዜጋ በማገልገል የሚኖሩት ሕይወት ተገቢ ነው አስፈላጊም ብቻ ሳይሆን በተጨባጭ ኢየሱስን የሚመስከር ሕይወት ነው ነገር ግን በጸሎት ተግባርና በሰቂለ ኅሊና ጸሎት የማይሸኝ መሆን የለበትም። ነገር ግን የሰቂለ ኅሊና ሕይወት ማለት ሬሳዊ ሕይወት ወይን ሙት ሕይወት ማለት እይደለም፡

ሲደክማችሁ ማረፉን እወቁበት

ቅዱስ አባታችን የለገሱት ምዕዳን፥ የውይፉይ ሕይወት አባላትና ገዳማውያን ደናግሎች ለማረፍ በቂ ጊዜ ያላቸው ሊሆኑ ይገባል፡ አረጋውያን ደናግሎችን በእድሜ የገፉትን የታመሙትን ደናግሎች መንከባከብ  ያስፈልጋል። በእድሜ የገፉት ደናግሎች ለደናግሎች ማኅበራት በተመክሮአቸውና በጥበባቸው ተዘክሮ ናቸው በማለት እንዳጠቃለሉ ደ ካሮሊስ ገለጡ። 








All the contents on this site are copyrighted ©.