2016-05-13 16:28:00

የቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ መልእክት ወደ የአዛኞች አጽናኝ ቅድስት ድንግል ማርያም መንፈሳውያን ነጋዲያን


በዚህ በቅዱስ የምኅረት ዓመት እ.ኤ.አ.2016 ዓ.ም. ቅድስት ድንግል ማርያም የአዛኞች አጽንኝ በሚል ቅዱስ ቅጽል ሥያሜ የሉሰምበርግ ጠባቂ ቅድስት ተብላ የታወጀችበት ዝክረ 350ኛው ዓመት ምክንያት ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ባስተላለፉት መልእክት፥ ዝክረ በዓሉ ከዓመተ ምኅረት ጋር መገናኘቱም የእግዚአብሔር አሳቢነት የሚያረጋግጥ ነው ብለው፡ ይኽ ደግሞ የምኅረት ዓመት የድህነትና የጸጋ ተሳታፍያን እንድንሆን በተስፋ የሚሞላን መሆኑ ያረጋግጥልና እንዳሉ ሲር የዜና አገልግሎት አስታወቀ።

የአዛኖች አጽናኝ ቅድስት ድንግል ማርያም ቅዱስ ሐወልት

የአዛኞች አጽናኝ ቅድስት ድንግል ማርያም የሉሰምበርግ ጠባቂ ቅድስት ተባላ የታወጀችው እ.ኤ.አ. ጥቅምት 16 ቀን 1666 ዓ.ም. መሆኑ ያስታወሰው ሲር የዜና አገልግሎት አያይዞ፥ በየዓመቱም ምእመናን ወደዚያ የአዛኞች አጽናኝ ቅድስት ድንግል ማርያም ቅዱስ ሐወልት ወደ ተኖረበት የማርያም ካቴድራል ተብሎ ወደ ሚጠራው ቤተ መቅደስ መንፈስዊ ንገድ በመፈጸም መጀመራቸው ገልጦ፡ እግዚአብሔር ለሰው ልጅ የሰጠው ተስፋ ኅያው እንዲሆን  የእግዚአብሔር እናት አጽናኝነቷንና አማላጅነቷን ለመማጠን በ 14ኛው ክፍለ ዘመን የተባረከው የአዛኖች አጽናኝ ቅድስት ማርያም ቅዱስ ሐወልት ፊት ጸሎት ለማሳረግ የሚፈጸመው ንግደት ብሔራዊ መልክ ብቻ ያለው ሳይሆን ዓለም አቀፋዊ መልክ ንዳለውም ያብራራል።

የሉሰምበርግ ሊቀ ጳጳሳ ብፁዕ አቡነ ዣን ክላውደ ሆለሪክ የአዛኞ አጽናኝ ቅድስት ድንግል ማርያም ዝክረ 350ኛውን ዓመት ምክንያት ባስተላለፉት መልእክት በዚህ የምህረ ዓመት ወደ የአዛኞች አጽናኝ ቅድስት ድንግል ማርያም ንግደት መፈጸም በአሁኑ ሰዓት ለስደትና ለመፈናቀል አደጋ ለተዳረጉትና ለሚዳረጉት ሁሉ ቅርብ እንድትሆን የሚማጠን ተግባር ይሁን እንዳሉና ሁሉም መልካም ፈቃድ ያለው ዜጋ ወደ ካቴድራሉ በመሄድ በአጽናኚቱ ቅድስት ድንግል ማርያም አማላጅነት ስለ ስደተኞችና ተፈናቃዮች እንዲጸልይ አደራ እንዳሉ የገለጠው ሲር የዜና አገልግሎት አክሎ ይኽ እ.ኤ.አ. ጥቅምት ወር 2016 ዓ.ም. የሚጠናቀቀው ማርያማዊ ጸሎትና መንፈሳዊው ንግደት ግንቦት 8 ቀን 2016 ዓ.ም. መጀመሩንም ይጠቁማል።








All the contents on this site are copyrighted ©.