2016-05-12 11:57:00

የኮፕቲክ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን እና የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን የዛሬ 43 ዓመት በይፋ ወዳጅነትን መመስረታቸው ታወቀ።


ሁለቱ ታላላቅ አብያተ ክርስቲያናት ማለትም የእስክንድሪያ የኮፕቲክ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን እና የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን የዛሬ 43 ዓመት ገደማ በወቅቱ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት የነበሩት ጳውሎስ ስድስተኛ እና ፓትርያርክ ሼኖዳ 3ኛ  ለመጀመሪያ ጊዜ ፊት ለፊት ተገናኝተው በሁለቱ አብያተ ክርስቲያናት መካከል መልካም ግንኙነት ይፈጠር ዘንድ መምከራቸውን ለመዘከር፣ በእየዓመቱ በሁለቱ ታላላቅ አብያተ ክርስቲያናት መካከል በይፋ ወዳጅነት የተጀመረበትን ቀን ምክንያት በማድረግ የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን የጹሑፍ መልዕክት የምታስተላልፍ እንደሆነ የሚታወቅ ሲሆን ይህንንም መሰረት በማድረግ ቅዱስ አባታችን ፍራንቸስኮ  በግንቦት 2, 2008 የእስክንድሪያ ርዕስ ሊቃነ ጳጳሳት እና የቅዱስ ማርቆስ ቅዱስ መንብር ፓትርያርክ  ለሆኑ ቴውድሮስ 2ኛ እለቱን የሚዘክር የጹሑፍ መልዕክት ማስተላለፋቸው ተገለጸ።

በግብጽ ለሚገኙት የኮፕቲክ ቤተ ክርስቲያን መሪ ቅዱስ አባታችን ፍራንቸስኮ ባስተላለፉት መልዕክታቸው ወዳጅነቱ በመጀመሩ ደስታቸውን የገለጹ ሲሆን “በሁለት አብያተ ክርስቲያናት መኋከል ያለውን ጥብቅ መንፈሳዊ ግንኙነት በማውሳት “ይህንን ጥብቅ መንፈሳዊ ግንኙነትን እውን ለማድረግ በጋራ የተወሰደው እርምጃ ወደ እርቅ እና ወዳጅነት መንገድ የሚመራ በመሆን እግዚኣብሔርን አመስግናለው ማለታቸው ታውቁዋል።

ቅዱስነታቸው ጨምረው እንደገለጹት “ምንም እንኳን አሁንም   የጌታን ማዕድ በጋራ  ወደ ምንቋደስበት ቀን እየተጓዝን ቢሆንም ያለነው፣ አሁንም ቢሆን ሊታይ የሚችል ተጨባጭ አንድ የምያደርገን ሕብርት በእኛ መካከል እየተንጸባረቀ ይገኛል” ብለዋል።

ቅዱስነታቸው በመቀጠልም የኮፕቲክ ክርስቲያኖች እና ኮቶሊኮች አሁን በዓለማችን ለሚታዩት ተግዳሮቶች “በወንጌል ላይ የተመሰረተ የጋራ ምላሽ” ምስጠት ይገባቸዋል ብለው በተለይም ደግሞ በመካከለኛው ምስራቅ በክርስቲያኖች ላይ በእየእለቱ እየደረሰባቸው የሚገኘውን ስደት መላሽ ሊሰጡ ይገባል ብለዋል።

“ምድራዊ ንግደታችንን ማድረግ በቀጠልን መጠን፣ እርስ በእርሳችን አንዱ ለእንዱ ሸክም አለመሆኑን በምንማርበት ጊዜ እና በተቃራኒው እያንዳዳችን የወረስነው ቱባ መንፈሳዊ ባሕሎች እንዳሉን በተገነዘብንበት ወቅት፣ ከምያለያዩን ነገሮች ይልቅ አንድ የምያደርጉን ነገሮች እንደ ሚበዙ መረዳት እንችላለን” ብለው የጹሑፍ መልዕክታቸውን አጠቃለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.