2016-05-12 12:34:00

ቅዱስነታቸው በቅ. ጴጥሮስ አደባባይ ያደረጉት የጠቅላላ አስተምህሮ ትኩረቱን ጠፍቶ የተገኘው ልጅ ላይ ያደረገ ነበር።


ቅዱስ አባታችን ፍራንቸስኮ በትላንትናው እለት ማለትም በግንቦት 3,2008 በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ለጠቅላላ ሳምንታዊ አስተምህሮ ለተገኙ ምዕመናን እና የሀገር ጎብኚዎች ያደረጉት አስተምህሮ ትኩረቱን ጠፍቶ በተገኘው ልጅ ላይ ያደርገ ሲሆን ከእዚህ ጠፍቶ ከተገኘ ልጅ ምሳሌ የምንረዳው “አስቸጋሪ በሆነ ወቅት እንኳን እግዚአብሔር ሁላችንንም ፍፁም በሆነ ፍቅር እንደ ሚቀበለን ያሳያል” ማለታቸው ተገለጸ።

ቅዱስነታቸው በማስከተልም እንደ ገለጹት ይህ ምሳሌ ስለ ጠፋው ልጅ ብቻ ሳይሆን የሚያወሳው የአባትነትን ይቅርባይነት መማር እና መቀበል ስላለበት ታላቅ ወንድሙ ጭምር እንደ ሆነ ለታዳሚዎች አስረድተው ሁለቱም ማለትም ቅጣት ይገባው የነበረው ታናሽ ወንድም እና  መልካም ባህሪን በማሳየቱ ሽልማትን ይጠብቅ የነበረው ታላቅ ወንድሙ፣ ሁለቱም የወሰዱት እርምጃ የአምላክ ፍቅር መሠረት ያላደረገ እንደ ነበር እና ሽልማት ወይም ቅጣት ከምያሰጥ እውነታ የራቁ እንደ ነበር አስረድተዋል። ቅዱስነታቸው አጽኖት ሰጥተው እንደ ገለጹት የእነዚህ የሁለት ወንድማማቾች  አባት ታልቁ ደስታ የነበረው ግን እነዚህ ተራርቀው የነበሩ ሁለት ልጆች ተመልሰው መገናኘታቸው እና እንደ አዲስ ወንድማማቾች መሆናቸውን መቀበላቸው እንደ ነበረም ገልጸዋል።

በመጨረሻም ቅዱስነታቸው እንደ ገለጹት ይህ ምሳሌ የተጠናቀቀው ታናሽ ወንድሙ ከጠፋበት በመመለሱ ምክንያት አባቱ ባዘጋጀው ግብዣ ላይ ታላቅ ወንድሙ ለቀረበለት ግብዣ የሰጠው ምላሽ ምን መሆኑን ሳይገልጽ ነው ብለው ኢየሱስ እያንዳንዳችንን የሚገፋፋን ለእግዚኣብሔር ጥሪ እንዴት መልስ መስጠት እንዳለብን እና ልባችንን ለእርቅ በፍቅር እንድንከፍት እና እንደ አባት መኋሪ እንድንሆን ነው ካሉ ቡኋላ የሰማይ ንግሥት ሆይ የሚለውን ጸሎት ከምዕመናን ጋር ካሳረጉ ቡኋላ ቡራኬን ሰጥተው የእለቱን አስተምህሮ አጠናቀዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.