2016-05-11 16:12:00

የቅድስና አዋጅ


የንጽሕት ድንግል ማርያም ልጆች ማኅበር መሥራች ብፁዕ ሉዶቪኮ ፓቮኒና የክርስቲያን ትምህርት ቤቶች ወንድሞች ማኅበር አባል ብፁዕ ሳሎሞነ ለክረክ በሰባት ሞቶዎች መጨረሻዎች ዓመታት የደም ሰማዕትነ የተቀበለው ቤተ ክርስቲያን ቅድስና እንዲታውጅላቸው የቫቲካን ረዲዮ ልኡክ ጋዜጠኛ አለሳንድሮ ጂሶቲ ገለጡ።

 ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ የቅድስና ጉዳይ የሚከታተለው  ቅዱስ ማኅበር ኅየንተ ብፁዕ ካርዲናል አንጀሎ አማቶ ያቀረቡት በሁለቱ ብፁዓን አማላጅነት እግዚአብሔር የጸገወው ፈውስ የተኖረበት የቅድስና አዋጅ ሰነድ ማጽደቃቸው የገለጡት የቫቲካን ረዲዮ ልኡክ ጋዜጠኛ ጂሶት አያይዘው፥

አባ ሉዶቪኮ ፓቮኒ እ.ኤ.አ. በኢጣሊያ ብረሺያ ክፍለ ሃገር እ.ኤ.አ. በ 1807 ዓ.ም. የክህነት ማዕርግ የተቀበሉ በዚያ ሰበካ ጳጳስ የሚደነቁ ጥልቅ መንፈሳዊነት የተካኑ  በተለያዩ ሐዋርያዊ ኃላፊት ሰበካውን በማገልገል በተለይ ደግሞ ድኾችና ወላጅ አልባ የሆኑትና በወላጆቸው የተተዉትን ወጣቶች በመንከባከብና ምሉእ ሰብአዊ ሕንጸት በመሰጠት ያገለገሉ መሆናቸው የቤተ ክርስቲያን የቅዱሳኖች የታሪክ ማኅደር ጠቀሰው ያመለክታሉ።

የሥነ ትምህርት አሰጣጥ ሊቅ

አባ ሉዶቪኮ በሠላሳ ዓመት እድሜያቸው የተግባረ እድ የሕንጸት ሥልት ቀድመው በዚያ በነበሩበት ዘመን በመለየት ለወቅታዊ የሥነ ተግባረ ዕድ ሥልጠናና ሕንጸ አብነት ለመሆን የበቁና የንጽሕት ቅድስት ድንግል ማርያም ልጆች “ላባደር ወንድሞች”በሚል መጠሪያ የሚታወቅ ገዳማዊ ማኅበር የመሠረቱ መሆናቸው የታሪክ ማኅደራቸው የጠቀሱት የቫቲካን ረዲዮ ልኡክ ጋዚጠኛ ጂሶቶ ብፅዕ ሉደቪኮ በ 65 ዓመት ዕድሜያቸው እ.ኤ.አ. በ 1849 ዓ.ም.  በሰማያዊ ቤት መወለዳቸው ይጠቁማሉ።

በፈረንሳይ አብዮት የደም ሰማዕትነት የተቀበለው ወንድም ለክረክ

ብፁዕ ሳሎሞነ ለክረክ  በ700 ዎች ዓመታት ሁለተኛ አጋማሽ በሕይወት የነበሩ በፈረንሳይ አቢዮት ወቅት ተነሣስቶ በነበረው ጸረ ካህናትና ምእመናን ባጠቃላይ ጸረ ቤተ ክርስቲያን ጽንሰ ሐሳብ በሚከተለው ሥርዓት ለስቃይ የተዳረጉ የክርስቲያን ትምህርት ቤቶች ወድማች ማኅበር በላሳል የሚታወቁት የወንድሞች ማኅበር ኣባል እንደነበሩና በዚያኑ ዘመን የነበረው የፈረንሳይ ሕግ ማንኛውም ዓይነት የቤተ ክርስቲያን ተቋምም ሆነ የገዳማውያንና ልኡካነ ወንጌል ጥሪ እውቅና የማይሰጥ እንደነበር የሚታወቅ ሲሆን። ገዳማውያን ጥሪያውቸውን በመካድ እንዲኖሩ የሚያስገድድ የፈረንሳይ አብዮት አመጣሽ ሥርዓት በመቃወምን ጥሪውን እልክድም ያለው ወንድም ለክለርክ መንግሥት ፓሪስ የሚገኘው የቀርመሎሳውያን ካህናት ገዳም ወደ ወኅኔ ቤት በለወጠው እስር ቤት ታጉረው ከቆዩ በኋላ በ 46 ዓመት ዕድሚያቸው የደም ሰማዕትነ የተቀበሉ የመጀመሪያ የላሳል ወንድሞ ማኅበር ሰማዕት መሆናቸውም የቤተ ክርስቲያን የታሪክ ማኅደር የጠቀሱት የቫቲካን ረዲዮ ጋዜጠኛ ደ ካሮሊስ አስታውቀዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.