2016-05-09 16:20:00

አባ ቪጋኖ፥ ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ የመገናኛ ብዙኃን አገልጋዮች የምኅረት ቋንቋ የሚናገሩ እንዲሆኑ ይሻሉ


እ.ኤ.አ. ግንቦት 8 ቀን 2016 ዓ.ም 50ኛው ዓለም አቀፍ የመገናኛ ብዙኃን ቀን ታስቦ መዋሉ ሲገለጥ። ቀኑን ምክንያት በማድረግ ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ቃለ ምልልስ ያካሄዱት የቫቲካን የመገናኛ ብዙኃን ጉዳይ ኅየንተ የኔታ አባ አንድረያ ኤድዋርዶ ቪጋኖ  ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸሶ ቀኑን ምክንያት በማድረግ ቀድመው ጥር 24 ቀን 2016 ያስተላለፉት መልእክት በማስታወስ  50ኛው ዓለም አቀፍ የመገናኛ ብዙኃን ቀን መርሆ “የመገናኛ ብዙኃንና ምኅረት፡ ላንድ ፍርያማ ግኑኝነት” የሚል መሆኑም ጠቅሰው፡ ቅዱስ አባታችን ቀኑን ምክንያት በማድረግ ባስተላለፉት መልእክት ምኅረት መኃሪነት ያንን በአንዲት ቤተሰብ ባንድ ማኅበረሰብ በጠቅላላ በአንድ ኅብረተሰብ ውስጥ የደማው የእርስ በእርስ ግኑኝነት የመጠገን ሰላም ስምምነት የማስጨበጥ እምቅ ኃይል አለው። በተባበሩት የአመሪካ መንግሥታት ሐዋርያዊ ጉብኝት ባካሄዱበት ወቅትም አንድ ቋንቋ የተበቃይ ግትር ቃል መግለጫ ሳይሆን አቀባበል መከባበር በተለያየ ችግር ምክንያት የተነጠለው እንዲስተናገድ እንዲደገፍ የሚያሳስብ መሆን አለበት ያሉትን ቃል አስታውሰው፡ ይኽ ሓሳብ የተገባው የምኅረት ቅዱስ ዓመትና ዓለም አቀፍ የመገናኝ ብዙኃ ቀን መካከል ያለው ግኑኝነት ያበክራል ብለዋል።

ሁለተኛው የቫቲካን ጉባኤ ዝክረ 50ኛው ዓመት በተለያየ ዘርፍ እየታስበ ነው፡ የዚያ ቅዱስ ጉባኤ 50ኛው ዓመትና ዘንድሮ የሚከበረው ዓለም አቀፍ የመገናኛ ብዙኃን ቀን ዝክረ 50ኛው ዓመት ብዙ ግኑኝነት አለው። ዓለም አቀፍ የመገናኛ ብዙኃን ቀን እንዲከበር የሚል ውሳኔ የሁለተኛው የቫቲካን ጉባኤ ሃሳብ ነው። ይኽ ደግሞ በቤተ ክርስቲያንና በዓለም መካከል ያለው ግኑኝነት ምን ተምሰሎው የሚገልጥ አንድ የታሪክ ምዕራፍ ነው። በመገናኘት የጋራ የሆነውን ሁሉ መገንባትና የጋራ ጥቅም አብሮ መሻት ማለት ነው፡ ስለዚህ ምንም’ኳ ልዩነት ቢኖር ይኸንን ልዩነት እርስ በእርስ በመገናኘት ቦግ ብሎ ልዩነት ለመለያየት ሳይሆን ልዩነቱ ለእርስ በእርስ መተዋወቅ የሚገፋፋ ፍላጎት ሆኖ እንዲኖር የሚደግፍ ነው።

የቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ መልእክት ቃል ቋንቋ የመገናኛ ብዙኅን ዓላም ለማጋጨት ጦርነት ለመጫር ለመቃቃር ሳይሆን መደማመጥ መግባባት መቀራረብ የሚል ነው፡ የኃሜትና ያሉባልታ መሣሪያ ሳይሆን የእውነት መሣሪያ ነው፡ ስለዚህ ለመገናኘት ከገዛ እራሳ መወጣት እንደሚያስፈልግ የሚያሳስብ ነው። በኦሪት ዘጸዓት ፥ ጫማህን አውልቅ የቆምክበት ሥፍራ ቅዱስና የተባረከ ነው ካንተ የተለየው ያለበት ሥፍራ ነው፡ ይኽ የተለየው ተብል የሚገለጠውም እግዚአብሔር ነው፡ ሰው ከእግዚአብሔር ጋር ለመገናኘት ምን ማድረግ አለበት ለሚለው ጥያቄ መልስ ከዚህ የመሓፍ ቅዱስ ቃል እናገኛለን። የመገናኛ ብዙኃን የግኑኝነት ሥፍራ መሆን አለበት።

በአሁኑ ወቅት ዓለም የሚከተለው የግኑኝነት ተግባር ወደ ምናባዊ እያደላ ነው። በተራቀቀ የሥነ አኃዝ ምርምር የተካነ እየሆነ እውነተኛ ግኑኝነት ከመሆን ይልቅ አኃዛዊ ግኑኝነት እየሆነ። እኔ ይኽ ያክል በዚህ በዚያ ድረ ገጽ ማኅበራዊ ገጹ ዘንድ ብዙ ጓደኞች አሉኝ ብዙ ተከታይ አለኝ ይባላል። ይኽ ግኑኝነት ምናባዊ ነው፡ በአሁኑ ሰዓት ዓለም የተጠማው እውነተኛ ግኑኝነት ነው፡ ስለዚህ ግኑኝነት መስመር ላይ  ወይንም ከመስመር ውጭ በመሆን የሚገለጥ አይደለም። የመገናኛ ብዙኃን ሰብአዊነት ማላበስ ያስፈልጋል።

ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ በሚያካሂድት ግኑኝነቶች በሚያስደምጡት ንግግሮችና በሚያስተላልፉት መልእክት አማካኝነት የግኑኝነት ጥልቅ ትርጉሙ ይመሰክራሉ። መገናኘት ልብ ለልብ። እርሱም የሌላው ችግር የሌላው ጭንቀት ፍርሃት የሰው ልጅ ወቅታዊ ሁኔታ የሚያዳምጡ መሆናቸውና አዳምጠውም የሚገባ ምልሽ እንዲያገኝ ችግሩናን ስቃዩን ፍርሃቱን ተስፋው ሁሉ ቃል በማድረግ ያስደምጡታል። ይኽ ደግሞ ድምጽ ለሌለው ድምጽ መሆን ማለት ነው፡ በሰዎች መካከል መሆን። የዚህ ፍጹም አብነትም ኢየሱስ ነው በማለት ያካሄዱት ቃለ ምልልስ አጠቃለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.