2016-05-09 16:22:00

ብፁዕ ካርዲናል ፓሮሊን፤ የመስቀል ኮረብታው የተስፋና የመቋቋም ኃይል ሥፍራ ነው


የቅድስት መንበር ዋና ጸሓፊ ብፁዕ ካርዲናል ፒየትሮ ፓሮሊን እ.ኤ.አ. ግንቦት 13 ቀን 2016 ዓ.ም. የሚጠናቀቀው  በሊቷንያ ኤስቶኒያና ለቶኒያ የሚያካሂዱት ዓለም አቀፋዊ ሐዋርያዊ ጉብኝታቸው እ.ኤ.አ. ግንቦት 7 ቀን 2016 ዓ.ም. ሊትዋኒያ በመግባት የጀመሩ ሲሆን፡ ብፁዕነታቸው ሊቱዋንያ ርእሰ ከተማ ቪልንዩስ በመግባት እዛው ከአገሪቱ መራሔ መንግሥት አልጂርዳስ ጋር የተገንኙ ሲሆን። ከግኑኝነቱ በኋላ ወደ ሲያኡሊያይ ክልል ወደ ሚገኘው የመስቀል ኮረብታ ተብሎ ወደ ሚጠራዊ አራት መቶ ሺሕ የመስቀል ምልክት ወደ ተኖረበት የአገሪቱ ህዝብ ሊትዋኒያ በቀድሞ በሶቪየት ኅብረት ሥር በነበረችበት ወቅት ብሔራዊ ማንነቱን ለማቀብ ላካሄደው ትግል ትእምርት ወደ ሆነው ሥፍራ በመሄድ  መሥዋዕተ ቅዳሴ ማሳረጋቸው የገለጠው የቅድስት መንበር መግለጫ አክሎ ያ ክልል በቅዱስ ዮሓንስ ጳውሎስ ዳግማዊ እ.ኤ.አ. መስከረም 7 ቀን 1993 ዓ.ም. መጎብኘቱንም ያመለክታል።

ብፁዕ ካርዲናል ፓሮሊን መሥዋዕተ ቅዳሴ አሳርገው ባሰሙት ስብከት፥ ያንን የመስቀል ኮረብታ የተስፋና የመቋቋም ምልክትና ያንን አገሪቱ ለራስ ክብር የከፈለችው መስዋዕትነት የሚመስከር ነው በማለት ዮሐንስ ጳውሎስ ዳግማዊ ብለዉት የነበረው ቃል ደግመው በማስተጋባት የአገሪቱ ሕዝብ በጽሞና በእምነት ጸንቶ የከፈለው መሥዋዕትነት ያንን ክርስቶስ የሰውን ልጅ ለማዳን የከፈለው መሥዋዕትነት በሱታፌ የኖረ የሊትዋንያ ሕዝብ የከፈለው የሰማዕትነት ደም ትእምርት ነው እንዳሉ የገለጠው የቅድስት መንበር መግለጫ አያይዞም ብፁዕ ካርዲናል ፓሮሊን እ.ኤ.አ. ግንቦት 9 ቀን የሊትዋንያ ጉብኝታቸውን አጠናቅው ኤስቶኒያ የገቡም ሲሆን እ.ኤ.አ. ግንቦት 11 ቀን 2016 ዓ.ም. የለቶኒያ ጉብኝታቸው እንደሚጀምሩም ያመለክታል። 








All the contents on this site are copyrighted ©.