2016-05-07 16:24:00

በሚያዝያ 28,2008 ቅ. አ. ፍራንቸስኮ ዓለማቀፋዊ የሻርልማኝ ሽልማት በቫቲካን በተካሄደ ስነ-ስርዓት ላይ ተሸላሚ ሆኑ።


በትላንትናው እለት ማለትም በሚያዝያ 28,2008 ቅዱስ አባታችን ፍራንቸስኮ ዓለማቀፋዊ የሻርልማኝ (International Charlemagne Prize) ሽልማትን በቫቲካን በተካሄደው ስነ-ስርዓት ላይ መሸለማቸው ታውቋዋል። ይህ የሻርልማኝ ሽልማት በየዓመቱ ስመጥር ለሆኑ ግለሰቦች ወይም ተቋማት ለአውሮፓ ውህደት ለሚያበረክቱት ከፍተኛ አስተዋጾ የሚሰጥ ሽልማት ሲሆን ሽላማቱም በእየዓመቱ የጄርመን ከተማ ከሆነችው አሄ’ን (Aachen ) ይህን ሽልማት የተቋቋመበትን ዓላማ እና መስፈርት ለሚያሙዋሉ ግለሰቦች ወይም ተቋማት የሚበረከት ሽልማት ነው።

ቅዱስ አባታችን ፍራንቸስኮ በሽልማቱ ወቅት በአጽኖት እንደ ገለጹት ይህንን ሽልማት የተቀበሉበት ምክንያት ሲገልጹ ለአውሮፓ ማስገንዘብ ወይም ማበርከት የፈለጉት ሐሳብ ስለነበራቸው መሆኑን ገልጸው ይህንም ሐሳብ በእለቱ “የእኛ ትኩረት ይህ የሽልማት ስነ ስርዓት ሳይሆን አጋጣሚውን ተጠቅመን፣ ይህ ተወዳጅ አህጉር በወኔ የተሞላ አዲስ እርምጃ እንደ ሚወስድ ያለንን የጋራ ተስፋ ለመግለጽ ነው” በማለት ገልጸዋል።

የአሄ’ን ከንቲባ የሆኑት ማርቲን ፊሊፕ ካደረጉት ንግግር በመቀጠል ንግግር ያደረጉት የአውሮፓ ፓርላማ ፕሬዝዴንት ማርቲን ሹልዝ (Shulz) እንደ ገለጹት “አውሮፓ በአሁኑ ወቅት በአስቸጋሪ ጊዜ ውስጥ እና ሕብረቱ ወሳኝ የሚባል ፈተና ላይ ነው” ማለታቸው እና ከእርሳቸው በመቀጠል የተናገሩት የአውሮፓ ካውንስል ፕሬዝዴንት እና እንዲሁም የአውሮፓ ኮሚሽን ፕሬዝዴንት ተመሳሳይ ሐሳቦችን ማቅረባቸውም ታውቁዋል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ አውሮፓ በአንድ ሆና እንድትቀጥል ባሳሰቡበት የተማጽኖ ንግግራቸው “ማፈግፈግ እና መድከም የአውሮፓ እሴቶች አለመሆናቸውን እርገጠኛ ነኝ። ችግሮቻችን ለሕብረታችን ጠንካራ ኋይል ሊሆኑ ይችላሉ” ማለታቸውም ታውቁዋል።

እንደ አውሮፓዊያን የቀን አቆጣጠር 2014 ለአውሮፓ ፓርላማ ያደረጉትን ንግግር በማስታወስ አውሮፓን በጣም ካረጁ እና ከደከሙ አያት ጋር እንዳነጻጸሩዋት አስታውሰው የአውሮፓን ማሕበረሰብ መጠየቅ የምፈልገው “የአውሮፓ ሰባዊ አመለካከት፣ በግንባር ቀደምትነት ስታከብሩት የነበረው የሰብዓዊ መብት፣ ዲሞክራሲ እና ነጻነት  አሁን የት ገባ? የባለቅኔዎች፣ የፈላስፎች፣ የአርቲስቶች፣ የሙዚቀኞች፣ የወንድ እና የሴት ጻሐፊዎች ቤት የነበርችው አውሮፓ አሁን ምን ነካችሁ? የሕዝቦች እና የሀገራት እናት፣ የብዙ ወንዶችና ሴቶች ልጆች ደጋፊ እናት እና እንዲሁም ለወንድሞችና ለእህቶች ክብር ሲሉ ሕይወታቸውን የሰው ሰዎች የሚገኙበት አውሮፓ አሁን ምን ነካችሁ?” ብለው በስፍራው ለነበሩ እንግዶች ጥያቄን ማቅረባቸው ተወስቱኋል።

አውሮፓ በሦስት ዓይነት አቅም ላይ ተመስርታ አዲስ የሰባዊነት አስተሳሰብን መውለድ ትችላለች እነዚህም የመቀናጀት አቅም፣ የውይይት አቅምን ማዳበር እና ችሎታን የማመንጨት አቅም መሆናቸውን ገልጸው አውሮፓ ምዕተ ዓመታትን ያስቆጠር በርካታ እና የተለያዩ ባህላትን የማዋሃድ የማይለወጥ እና ጠንካራ የሆነ ስር መሰረት እናዳላትም ጨምረው ገልጸዋል። በማከልም የመነጋገር ባሕል “በትምህርት ቤቶቻችን ውስጥ እንደ ዋና ክፍል ተደርጎ በተቀናጄ መልኩ መሰጠት አለበት” ይህም ወጣት ዜጎች ግጭቶችን ለየት ባለ መልኩ ለመፍታት እንዲችሉ ግባት ይሆናቸዋል በማለት ገልጸዋል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳስት ፍራንቸስኮ በአጽኖት እንደ ገለጹት ሁሉም ሀገራት ትልቅም ይሁኑ ትንሽ፣ የተቀናጄ እና ሰላማዊ ኅብረተሰብ ለመፍጠር የሚጫወቱት ንቁ ሚና እንዳለቸው ገልጸዋል። በተለይም ደግሞ ወጣቱ የሚጫወተው ሚና በጣም አስፈላጊ መሆኑን ገልጸው “ወጣቶች የወደ ፊቱ የእኛ ተስፋ የሚጣልባቸው ሰዎች ሳይሆኑ ወቅታዊ” ጠቀመታ እንዳለቸውም አበክረው ገልጸዋል። በቦታው የተገኙ የበዓሉ ተሳታፊዎችን “ የሥራ እድል በቀነሰበት እና በብዙ ሚልዮን የሚቆጠሩ ወጣቶች ሥራ ባጡበት እና በአጠቃላይ ሥራ አጥነት በአውሮፓ እየተስፋፋ  ባለበት በአሁኑ ሁኔታ ወጣቶችን ግንባር ቀደም የሆነ ሚና አላችሁ  ልንላቸው እንዴት እንችላለን? በየሀገራቸው እድልን እና እሴቶችን ባለማግኘታቸው ህልማቸውን እውን ለማድረግ በተለያዩ ስፍራዎች የሚኳትኑትን እና የአለኝታነትን ስሜት ያጡትን ወጣቶቻችንን እንዴት ነው መታደግ የምንችለው?” በማለት የአውሮፓን ወቅታዊ ችግር የሚያንጸባርቁ ሁኔታዎችን ከግምት ያስገባ ጥያቄዎችን ማንሳታቸውም ተወስቱዋል።

 ቅዱስነታቸው በማስከተል እንደገለጹት የተከበረ እና ጥሩ ክፍያ ያለው የሥራ ዕድል በተለይም ለወጣቶች ለመፍጠር አሁን ካለው የካሽ ገንዘብ ላይ ትኩረቱን ካደርገው እና ትርፍን ማጋበስን ብቻ መሰረት ካደርገው “liquid economy” ወደ ሁሉን አቀፍ እና ለሁሉም የማሕበርሰብ ክፍል የሥራ እድል በመክፈት ሁሉንም ተጠቃሚ ወደ ሚያደርገው የማሕበረሰብ ኢኮኖሚ (social economy) መሸጋገር አስፈላጊ መሆኑን አሳስበዋል።

ቅዱስ አባታችን ፍራንቸስኮ ንግግራቸውን ለአውሮፓ አለኝ ባሉ ሕልም ያጠናቀቁ ሲሆን አውሮፓ ልክ ሕይወት እንዳላት እናት የሆነች ቦታ እንድትሆን እፈልጋለው ምክንያቱም ክብር እና ሕይወት ለሌሎች መስጠት እንድትችል፣ ለታመሙት እና ለአረጋዊያን ቦታ የምትሰጥ ስፍራ እንድትሆን እመኛለው፣ “በሐቀኝነት የተሞላ ንጹህ አየር” የምትተነፍስ አውሮፓ እንድትሆን እፈልጋለው በማለት ንግግራቸውን አጠናቀዋል። 

 








All the contents on this site are copyrighted ©.