2016-05-06 17:03:00

ደቡብ ሱዳን ብፁዓ ጳጳሳት ምክር ቤት ዜጎች ተፈጥሮና ፍጥረት ለመንከባከብ እንዲተጉ ጥሪ አቀረቡ


ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራቸውስኮ ይሴባሕ በሚል ርእስ ሥር የደረሱት ዓዋዲ መልእክት ዙሪያ የሱዳን ብፁዓ ጳጳሳት ምክር ቤት በጁባ ያዘጋጁትና በጠቅላላ 500 ተጋባእያን ያሳተፈ ዓውደ ጥናት መካሄዱ  የአገሪቱ ብፁዓን ጳጳት ምክር ቤት የሰጠው መግለጫ የጠቀሰው ፊደስ የዜና አገልግሎ አስታወቀ።

የደቡብ ሱዳን ምኅዳር አሳሳቢነት

የሱዳን ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት አገራቸው ከእርስ በእርስ ግጭት ለመውጣት ጥረት በማድረግ ላይ በምትገኝበት በአሁኑ ወቅት ዜጎች ከዚያ ሞትና ውድመት ከሚያስፋፋው ጸረ ሰብአዊ ተግባር ለመላቀቅ በሰላም ጎዳና በሚያደርጉት ጉዞ ተስፋ ሳይቆርጡ እንዲቀጥሉበት በማሳሰብ በአገሪቱ የምትገኘው ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ከሁሉም መልካም ፈቃድ ካላቸው ሰዎች ጋር በመተባበር፡ የጊዜ ምልክቶችን በማንበብ የዓለም ኵላዊ ጥሪ እርሱም መከባበር መቀባበልና መደጋገፍ የሚለው እሴት መሠረት ያደረገ ያኗኗር ስልት እንዲሳፋና በዚህ ስልት አማካኝነት የሰው ልጅ ጤናና የተፈጥሮ ጤና እንዲንከባከብ የተጠራ መሆኑ ታንጻለች እንዳሉ የገልጠው ፊደስ የዜና አገልግሎት አክሎ፥ በሱዳን የሚታየው የውህ ብከላ የመሬትና ያካባቢ አየር ብከላ እጅግ አሳሳቢ ከመሆኑም ባሻገር የተፈጥሮ የደን ሃብት ምንጠራ የተፈጥሮ ማእድን ላገልግሎት ለማዋል እግብር ላይ እየዋለ ያለው እደ ጥበብ አገሪቱን ለከፋና ለተወሳሰበ ችግር እያጋለጣት መሆኑ አብራርተው፡ ሁሉም ተፈጥሮ ለመከባከና በሚገባ ለመጠቀም የተጥራው መሆኑ እንዲያስተውል አደራ እንዳሉ አስታወቀ።

ፍትህ በተፈጥሮና በሰብአዊ ፍጥረት ፊት ብበዙውን ጊዜ ጦርነት አመጽና ግጭት በሚታይበት ክልል የሚኖር ሰው የአግዚአብሔር አርአያና አምሳያ መሆኑ የሚያሰጠው ሰብአዊ ክብሩን ጠብቆ ከመኖር ይልቅ ወንድሙ አቤልን እንደ ገደለው ቃኤል ለመሆን ይቃጣዋል፡ በዓለም ቃኤልነት እየተስፋፋ ነው። እግዚአብሔርም ወንድማችን የት እንዳለ እየጠየቀን ነው፡ በሰዎች መካከል ያለው ግኑኝነት ከእዚአብሔር ጋር የሚኖረው ግኑኝነት ውንድማችንንና ተፈጥሮን ጭምር በመንከባከ የሚገለጥ ነው፡ እግዚአብሔር ለሰው ልጅ ተፈጥሮን ግዛ ብሎ ኃላፊነት ሲሰጠው ተፈጥሮን ባርያ እንዲያደርግ ሳይሆን በሚገባ እንዲያስተዳዳር ብሎ ነው፡ ኃላፊነት የሚል ሆኖ እያለ የሰው ልጅ ተፈጥሮን ላደጋ እያጋለጠ የገዛ እራሱንና የጋራ ማደሪያ የሆነችውን መሬት ለከፋ አደጋ እያጋለጠ ነው፡ ስለዚህ በተፈጥሮና በሰው ዘር ፊት በፍትሃዊነት ተግባር መቅረብ እንደሚያስፈልግ የደቡብ ሱዳን ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት ማብራራታቸው ፊደስ የዜና አገልግሎት ይጠቁማል።

ቤተ ክርስቲያን ምእመናን ውሉደ ክህነት ነቢያው ድምጽ በመሆን የጊዜ ምልክት በማነበብ ሰብአዊ ማእከል ያደረገ ባህል በማስፋፋት ረገድ አቢይ ሚና እንዲጫወቱ ብፁዓን ጳጳሳቱ በማሳሰብ የፖለቲካው ዓለም ማንኛውም ዜጋ ፍትህ ሰላም ተፈጥሮ ለመንከባከብና ለእርቅ የቆመ እንዲሆን ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ በይሴባሕ ዓዋዲ መልእክታቸው አማካኝነት የሰጡት ሥልጣናዊ ትምህርት እግብር ላይ እናውል በማለት ባቀረቡት ጥሪ ያስተላለፉት መልእክት እንዳጠቃለሉ ፊሰስ የዜና አገልግሎት ያመለክታል። 








All the contents on this site are copyrighted ©.