2016-05-05 11:32:00

ቅ.አ. ፍራንቸስኮ የግንቦት ወር የቤተ ክርስቲያን የጸሎት ሐሳብ እንዲሆን የመረጡት ሴቶች በማሕበረሰብ ውስጥ እያበረከቱት ያለውን ተግባር እውቅና ይሰጠው ዘንድ መሆኑን አስታወቁ።


ቅዱስ አባታችን ፍራንቸስኮ በሚያዝያ 26,2008፣ እንደ አውሮፓዊያን የቀን አቆጣጠር አሁን በያዝነው የግንቦት ወር ዓለማቀፋዊው የቤተ ክርስቲያን የጸሎት ሐሳብ እንዲሆን የመረጡት እና ትኩረቱም ሴቶችን መዕከል ያደረገ እና በተለይም “በመላው ዓለም የሚገኙ ሴቶች በማህበርሰብ ውስጥ እያበረከቱ ስለሚገኘው፣ ሊተካ የማይችል እና ከፍተኛ አስተዋጾ ክብር እና እውቅና እንዲሰጠው” በሚል አርዕስት ላይ እንደሚሆን በአስተላለፉት የቪዲዮ መልዕክታቸው መግለጻቸውን ዜናውን ያዘጋጀው የቫቲካን ሬድዩ ባልደረባ ሮበርቶ ፒየርማሪኖ አስታወቀ።

“ሴቶች በማንኛውም ሁኔታ ለሰው ልጆች እያበረከቱ ያለው አስተዋጾ ሊካድ አይገባውም” ያሉት ቅዱስነታቸው “ከቤተሰብ ጀምሮ የሚያደርጉት አስተዋጾ ከፈተኛ መሆኑንም” ጨምረው ገልጸዋል። “ይህ ሴቶች እያከናወኑ ለሚገኙት ተግባር እውቅናን መስጠት ብቻ ይበቃል ወይ?” ብለው ጥያቄን በማንሳት መልዕክታቸውን የቀጠሉት ቅዱስ አባታችን በእዚህ ረገድ ገና ብዙ ሰፊ ሥራ እንዳልተሰራ ገልጸው “በአስቸጋሪ ሁኔታ የሚኖሩ፣ ተስፋ የቆረጡ፣ የተገለሉ እና እንዲሁም እንደ ባሪያ እየተቆጠሩ የሚገኙ ሴቶች አሁንም እንደ ሚገኙ እና በተጨማሪም፣ በሴቶች ላይ በሚፈጸመው የወሲብ ጥቃት ምክንያት የሚሰቃዩ ሴቶች” በርካታ እንደሆኑ ጠቅሰው፣ “ይህንን ዓይነት ተግባራትን ማውገዝ እና እንዲሁም ሴቶች በማሕበራዊ፣ በፖሌቲካዊ እና በኢኮኖሚያዊ ተግባራት ውስጥ መሉ በሙሉ እንዳይሳተፉ የሚያደርጉዋቸውን መሰናክሎች ማስወገድ እና ማውገዝ ይጠበቅብናል” ብለዋል።

በመጨረሻም ሴቶች በማሕበራዊ ሥራ ውስጥ ሊኖራቸው ሰለ ሚገባው ድርሻ ለመግለጽ በማሰብ “ሴቶች የሚሠሩት ማንኛውም ሥራ ከወንድ እኩል ዋጋ ሊሰጠው ይገባል። በምንም ዓይነት ሁኔታ ሴቶች የባርነት እና  የጥቃት ሰላባዎች እንዲሁም እነዚህን በመሳሰሉ ጥቃቶች ሰላባ መሆን የለባቸውም። በሴቶች ላይ የሚደርገው የሥራ አድሎ ይብቃ ምክንያቱም ሁላችንም ወንድም ሆንን ሴት የአንዱ የእግዚአብሔር ልጆች ነን” በማለት የቪድዮ መልዕክታቸውን አጠናቀዋል።

 








All the contents on this site are copyrighted ©.