2016-05-02 15:49:00

ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ.፥ ሥራ ሰብአዊ ተግባር ነው


ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ እ.ኤ.አ. ግንቦት አንድ ቀን ዓለም አቀፍ የሠራተኞች ቀን እንዲሁም ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ዮሴፍ አስባ የምትውልበ ግንቦት አንድ ቀን ምክንያት በማድረግ ሥራ ሰብአዊ ተግባር  መሆኑ የሚያበክር መልእክት ማስተላለፋቸው ሲገለጥ፡ ያ በእግዚአብሔር አርአያና አምሳያ የተፈጠረው ሰው  ክብሩን የሚገልጥበት ተግባር ሲሆን የሰው ልጅ በዚህ ምድር ዕለታዊ ሕይወቱን ለማስተዳዳር የሚያስችለው ተግባር ሲሆን ከዚህ አንጻር ሲታይም ሥራ የሰው ልጅ ሰብአዊ መብትና ክብር መሆኑ ማብራራታቸው የቫቲካን ረዲዮ ልኡክ ጋዜጠኛ አለሳንድሮ ጓራሺ አስታወቁ።

በአሁኑ ሰዓት ተከስቶ ባለው የኤኮኖሚ ቀውስ ምክንያት በዓለማችን እየተስፋፋ ያለው የሥራ አጥነት ጉዳይ በማስመልከትም የኢጣሊያ የክርስቲያን ሠራተኛ ማኅበር ጠቅላይ ዋና ጸሓፊ ሰርጆ ሲልቫኒ ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ፥ በኢጣሊያ ባለው የሥራ አጥነት ችግር ምክንያት የአገሪቱ ምርጥ ምርጥ ምሁራንና ተመራማሪዎች ወደ ተለያዩ አገሮች  እንዲሰደዱ እያስገደደ ነው። እጅግ አሳሳቢ እየሆነ የመጣውም የወጣቶች ሥራ አጥ ብዛት ከፍ እያለ መምጣቱ  ነው፡ መንግሥት ለምርምርና ለአዲስ የምርምር ግኝቶች ድጋፍ መዋዕለ ንዋይ ማቅረብ ይኖበታል። ካልሆነ በአሁኑ ሰዓት እንደሚታየው አንዲት አገር ያፈራቻቸው በተለያየ የትምህትር ዘርፍ የሰለጠነው የሰው ኃይል ግሽበት በከፍተና ደረጃ እንዲያጋጥማት ከማድረግ እልፎም ልትጨብጠው የሞገባት እድገት ከወዲሁ ገና ሳይጀመር እንዲገታ ያደርጋል ብለዋል።

የኢጣሊያ ክርስቲያን የኢንዳስትሪ ባለ ሃብቶች ማኀበር ሊቀ መንበር ዲየጎ ባርባቶ በበኩላቸውም ባካሄዱ ቃለ ምልልስ፥ በሥራ ቦታ እያሉ የሞት አደጋ የሚያጥማቸው ሠራተኞ ቁጥር ብዛት ከፍ እያለ መሆኑ አስታውሰው፡ የሠራተኛ ደህንነት ለማረጋገጥ እንዲቻል ሕጋዊ ሥራ ማስፋፋት የሰው ልጅ መብትና ክብር የሚያከብር የሥራ ሰዓት ሥራና ተመታጣኝ የደሞዝ ክፍያ የመሳሰሉት መመሪያዎች ግብራው ማድረግ ያስፈልጋል፡ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮ እንዳሉትም ሥራ የሰው ልጅ ክብር መግለጫ ነው በማለት ያካሄዱት ቃለ ምልልስ ደምድመዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.