2016-04-30 10:47:00

አሞሪስ ላኤቲቲአ በቅዱስ አባታች ፍራንቸስኮ ተጽፎ በመጋቢት 30,2008 ለንባብ የበቃው ሐዋሪያዊ ቃለ ምዕዳን።


የፍቅር ሐሴት
አሞሪስ ላኤቲቲአ (Amoris Laetitia)
በቅዱስ አባታች ፍራንቸስኮ ተጽፎ በመጋቢት 30,2008 ለንባብ የበቃው ሐዋሪያዊ ቃለ ምዕዳን
የአሞሪስ ላኤቲቲአ መዋቅር እና ትርጉም በአጭሩ በቫቲካን ሬድዮ እንደ ተዘጋጀው
ፍቅር በቤተሰብ ውስጥ
“የፍቅር ሐሴት” ወይም በላቲን “አሞሪስ ላኤቲቲአ” የተሰኘው እና ትኩረቱን ፍቅር በቤተሰብ ውስጥ ስላለው
ሚና ላይ በማድረግ የምያወሳው ድሕረ ሲኖዶስ ሐዋሪያዊ ቃለ ምዕዳን በመጋቢት 19, 2016 በቅዱስ ዮሴፍ
የንግሥ በዓል ዕለት በቅዱስ አባታችን ተፈርሞ ለንባብ እንዲበቃ መታዘዙ በአጋጣሚ የተፈጠር ጉዳይ
አልነበረም።
ይህ ሐዋሪያዊ ቃለ ምዕዳን ከእዝህ በፊት በቅዱስ አባታችን አነሳሽነት፣ በቤተስብ ጉዳይ ላይ ትኩረትን
በማድረግ በ2014 በተዘጋጀው ልዩ የጳጳሳት ሲኖዶስ እና በመቀጠልም በጥቅምት ወር 2015 ከ190 በላይ
ከዓለም ዙሪያ የተውጣጡ ጳጳሳት የተሳተፉበት መደበኛው የጳጳሳት ሲኖዶስ ድምር ውጤት ነው።
አሞሪስ ላኤቲቲአ (የፍቅር ሐሴት) የተሰኘው ሐዋሪያዊ ቃለ ምዕዳን ቀደም ብለው ከተካሄዱት ሁለት
ሲኖዶሶች ባሻገር ከእዝህ በፊት የነበሩት የቤተክርስቲያን ሰነዶችን፣ ከቅዱስ አባትችን ፍራንቸስኮ በፊት የነበሩ
ጳጳሳት አስተምሮዎችን እንዲሁም በቤተሰብ ዙሪያ እርሳቸው እራሳቸው የሰጡትን አስተምሮ አጠቃሎ የያዘ
ሐዋሪያዊ ቃለ ሞዳን ነው።
እንደ ተጨማሪ ግብኋትም በዓለም ዙሪያ ለምሳሌም በኬንያ፣ በአውስትራሊያ፣ በአርጄንቲና . . . ወዘተ
ከተካሄዱትን ጳጳሳዊ ጉባሄዎች የማጠናከሪያ ሐሳብ የወሰደ ሲሆን በተጨማሪም የጥቁሮች መብት ተሟጋች
የነበረው እና “I have adream” (ሕልም አለኝ) በሚለው አባባሉ የሚታወቀው አሜርካዊው የሰዎች መብት
ተሟጋች የነበረው ማርቲን ሉተር ኪንግ እና የማሕበርሰብ ስነ-ልቦና አጥኝ የነበረው ጀርመናዊው ኤንሪክ
ፍሮም ጉልህ ሊባል በሚችል መልኩ የተጠቀሱበት እና “ባቤትስ ፊስት” (Babette’s Feast) የተሰኘው እና
በ1987 ለመጀመሪያ ጊዜ በዴንማርክ ለእይታ የቀረበ ድራማ ላይ በተጠቀሰው እና ትኩረቱን በ19ኛ ክፍለ
ዘመን መጨረሻ ላይ በዴንማርክ ፓስተር ከነበረው አባታቸው ጋር ጭምት የሆነ ሕይወት ይኖሩ ስለ ነበር
ሁለት እህተማማቾች የምተርከው ዋና ጽንሰ ሐሳብም በሐውሪያዊው ቃለ ምዕዳን ውስጥ ተጠቅሱኋል።
መግቢያ (ከአንቀጽ 1-7)
ከምዕራፍ አንድ እስከ ሰባት በሐዋሪያዊው ቃለ ምዕዳን ውስጥ የተጠቀሰው በመቀጠል በዝርዝር ለሚቀርቡት
ሐሳቦች እንደ መንደርደሪያ የሚሆኑ ሐሳቦችን የያዘ ነው። ይህ 325 አንቀጾች ያሉት ሐዋሪያዊ ቃለ ምዕዳን
በዘጠኝ ምዕራፎች የተከፈለ ነው። የመጀምሪያዎቹ ሰባት የመግቢያ አንቀጾች የሐዋሪያዊውን ቃለ ምዕዳን
አርዕስት ውስብስብነት በግልጽ በማስቀመጥ በቀጣይነትም አስቸኳይ እና ጥልቅ የሆነ ጥናት እንዲደርግበት
የምያሳስብ ነው።
በተጨማሪም ቀደም ብለው በተካሄዱት ሁለት ሲኖዶሶች ላይ ቅዱሳን አባቶች መልክ እንዲይዝ ያሳሰቡት
የነፍሳት ዕንቁ “multifaceted gem” (አ.ላ. ቁ. 4) የተሰኘው እና ወድ የሆኑ የሰው ልጅች የማንነት እሴቶች
ተጠብቀው እንዲቀጥሉ የሚጋብዝ ሐሳቦችም ተጠቅሰውበታል። ነገር ግን ቅዱስነታቸው ጥንቃቄ በተሞላው
እና ውዝግብ በማይፈጥር መልኩ “ቀኖናዊ ጉዳዮችን የተመለከቱ ፣ የስነ- ምግባር ጉድለቶች ወይም ሐዋሪያዊ
ተግዳሮቶች፣ ቤተ ክርስቲያን በተሰጣት ስልጣን በምትሰጠው ኦፊሴልያዊ አስተምሮ ወይም (magisterium)
ብቻ መፈታት የለባቸውም” የሚል ሐሳብ አንጸባርቀኋል።
በእርግጥም “ለአንድ አንድ ለሚነሱ አንገብጋቢ ጥያቄዎች እየ አንድ አንዱ ሀግር ወይም ክልል. . . ወዘተ፣
ባህሉን እና ወጉን በጠበቀ መልኩ እና የማሕበረሰቡን ጥቅም ከግንዛቤ ባስገባ መልኩ አንገብጋቢ ለሆኑ
ችግሮቻቸው መፍትሄን መስጠት ይችላሉ። ‘ባህሎች አንዱ ከአንዱ የተለዩ በመሆናቸው አጠቃላይ ወይም
ዓለማቀፋዊ የሆኑ መርዕዎች እንዲከበሩ እና ተጋብራዊ እንዲደረጉ ከተፈለገ እንደ የባህሉ ሁኔታ መወሰድ
ይኖርባቸኋል’” (አ.ላ. ቁ. 4)። “እነዝህ ዓለማቀፋዊ የሆኑ መርዕዎችን ‘በባህል ውስጥ ማስረጸ’ የሚለው
መርዕ ሐሳብ የሚተገበረው የችግሮችን መንስሄ በማጥናት፣ እንዲሁም ምፍትሄን በመንደፍ፣ በተጨማሪም
የቤተክርስቲያን ቀኖናን እና ቤተ ክርስቲያን በተሰጣት መንፈሳዊ ስልጣን የምታስተምራቸውን አስተምሮዎችን
ተመርኩዞ ለአንገብጋቢ ችግሮች ተገቢ በሆነ መልኩ ምልስ ሊሰጥ ይገባል። ነገር ግን በእዝህ ዓይነቱ ዘዴ
የተፈታ ማንኛውም ዓይነት አንገብጋቢ ችግር ይዘቱ ‘ዓለማቀፋዊ’ ሊሆን አይችልም”።
በ2015 በተካሄደው ሲኖድ ላይ ቅዱስነታቸው በግልጽ እንዳስቀመጡት “ለአንድ አቡን ጤናማ ጉዳይ ሆኖ
የሚታየው ጉዳይ፣ በሌላ አሀጉር ወይም ሀገር ለሚኖር አቡን ግን እንደ እንግዳ እና አሳፋሪ ነገር ተደርጎ ሊቆጠር
ይችል። በአንዱ አቡን ማሕበርሰብ ውስጥ እንደ የሰው ልጆች የመብት ጥሰት ተደርጎ የሚቆጠር ተግባር በሌላ
አሀጉር ወይም ሀገር ውስጥ ለሚኖር አቡን ግን እንደ ግልጽ እና የማይጣሱ ትክክለኛ የሰው ልጆች መብትን
የምያስከብር ደንብ ተደርጎ ሊወሰድ ይችላል። በአንዱ ማሕበረሰብ ውስጥ እንደ ሕሊና ነፃነት የሚቆጠሩ
ተግባሮች በሌላው ማሕበርሰብ ውስጥ ግን እንደ ግራ መጋባት ይቆጠራሉ” ማለታቸው ይታውሳል።
ቅዱስነታቸው በቃለ ምዕዳናቸው “በመገናኛ ብዙኃን የሚደርጉ ክርክሮች፣ አንድ አንድ አሳታሚዎች አልፎ
ተርፎም በቤተ ክርስቲያን አገልጋዮች መካከል ጉዳዩን በጥልቀት ሳይመረምሩ እና አንድ አቋም ላይ ሳይደርሱ
ተመጣጣኝ ያልሆነ አጠቃላይ ለውጥ እንዲመጣ መፈለጋቸው እና ሁሉንም ዓይነት ጉዳዮች አጠቃላይ
ደንቦችን ተግባራዊ በማድረግ ለመፍታት ዝንባሌ ማሳየታቸው እንዲሁም መለኮታዊ የሆኑ አስተምሮዎችን
ከግምት በማስገባት ወደ አልተፈለገ ድምዳሜ ማምራት” (አ.ላ. ቁ. 2) ቅዱስነታቸው በግልጽ እንዳስቀመጡት
የለውጥ ጥያቄዎችን እና ውስብስብ የሆኑ ሕግጋትን አጠቅላይ ተግባራት ጎን ለጎን አስቀምጠን በግልጽ
ከመፈርጅ መቆጠብ እንደ ሚገባ ገልጸኋል።
ምዕራፍ አንድ “በብርሃነ ቃሉ” (ከአንቀጽ 8-30)
የመግብያ ንግግራቸውን ተከትሎ ቅዱስነታቸው ሐሳባቸውን በመጻሐፍ ቅዱስ ላይ መሰረት በማድረግ
የመጀመሪያ የቃለ ምዕዳናቸውን ምዕራፍ የጀመሩት በመዝሙር 128 ላይ አስተንትኖ በማድረግ ነው።
መጽሐፍ ቅዱስ “በቤተሰብ፣ በልደት፣ በፍቅር ታሪኮች እና የቤተሰብ ቀውስ የተሞላ ነው" (አ.ላ. ቁ. 8)። “ይህ
እውነታ እንድናጤን የሚገፋፋን የቤተሰብ ጉዳይ ውስብስብ አለመሆኑን እና ነገር ግን ዕለታዊ፣ ተጨባጭ እና
ነባራዊ ተግባር መሆኑን ሲሆን (አ.ላ. 16) እንዲሁም በርኅራኄ የምተገበር (አ.ላ. 28) ነግር ግን ከጥንት
ጀምሮ እንደ ሚታየው፣ በፍቅር ላይ የተመሰረት ግንኙነት በሚለወጥበት ጊዜ እና አንዱ ሌላውን በሚጫንበት
ወቅት ኋያት የሚጋረጥበት ሕይወት ነው (አ.ላ. ቁ. 19)።
ስለዚህ የእግዚኣብሔር ቃል ‘በተወሳሰቡ ሐሳቦች የተሞላ ሳይሆን ነገር ግን በችግር ወይም በመከራ ውስጥ
የሚገኙ ቤተሰቦችን የምያግዝ እና የመጽናናት ሁሉ ምንጭ ነው ምክንያቱም ወደ የሕይወታቸው ግብ ስለ
ሚመራቸው” (አ.ላ. 22) በማለት በቤተሰብ ውስጥ ስለሚታዩ በጣም ብዙ ሊባሉ ስለሚችሉ መልካም ነገሮች
እና ተግዳሮቶች በማውሳት ለችግሮቻቸው በእግዚአብሔር ቃል ላይ ተመርኩዘው መፍትሄን እንድያበጁ
ያሳሰቡበት ምዕራፍ ነው።
ምዕራፍ ሁለት “የቤተሰብ ተመኩሮዎች እና ተግዳሮቶች” (ከአንቀጽ 31-57)
በሁለተኛው ምዕራፍ ላይ ቅዱስነታቸው መጽሐፍ ቅዱሳዊ መሠረት ላይ በመመርኮዝ አሁን ባለንበት ዘመን
ያለውን የቤተሰብ ሁኔታ ያብራራሉ። “ነባራዊ እውነታ ላይ በመመርኮዝ”(አ.ላ. 6) የቤተሰብ ተሞክሮን
የገመገመ እና በተለይም ከዝህ በፊት ተካሄደው የነበሩ ሁለቱ ሲኖዶሶች ጠቅላላ ሪፖርት ላይ መሰረቱን ያደረገ
ነው።
ከሰዎች ፍልሰት አንስቶ እስከ በጾታዎች መካከል ስላለው ልዩነት የምያወሳው “ስነ-ጾታዊ ርዮተ ዓለም” (አ.ላ
56)፣ እንዲሁም አዲስ ከሆነ ባሕል እስከ ውልጃን የሚከለክል አስተሳሰብ (ማስወረድ፣ abortion) እንዲሁም
በእርግዝና ወቅት አሁን እየታየ ያለው የባዮቴክኖሎጂ ተጽዕኖ፣ ከመኖሪያ ቤት እጥረት እስከ የብልግና ሥራ ላይ
እስከ ተሰማሩ ሰዎች የሚያወሳ፣ ለአካለ መጠን ያልደርሱ ልጆች ላይ እየደረሰ ያለውን አካላዊ እና ሞራላዊ
ጥቃቶችን የሚዳስስ፣ የአካል ጉዳተኛ የሆኑ ሰዎች ትኩረት መንፈጋቸውን የሚገልጽ፣ መእድሜ የገፉ ሰዎችን
ክብር መነፍጋቸውን የምያብራራ፣ ቤተሰብን ሕጋዊ በሆነ መልኩ ማለያየት እና በሴቶች ላይ በሚደርሰውን
ጥቃት ምክንያት ቤተሰብ ብዙ ተግዳሮቶች እየ ደረሰበት መሆኑን ይተነትናል። ቅዱስነታቸው በሐዋሪያዊ ቃለ
ምዕዳናቸው ትኩረታቸውን ያደረጉት ተጨባጭ በሆኑ እውነታዎች ላይ ነው።
ለተቀባይነት እና ለነባርዊ እውነታ ትርጉሜን በሚሰጠው “ንድፈ ሐሳብ” እና አጣራጣሪ በሆነው “ርዕዮተ
ዓለም” መካከል ያለውን ልዩነት ጉልህ በሆነ መልኩ መለየት የሚቻለው በሕይወት ውስጥ የሚታዩትን
ተጨባጭ እና እውነተኛውን የሕይወት ተሞክሮዎች እንዲሁም ዕለት ተዕለ በሕይወት ውስጥ የሚታዩትን
ፈታንዎች መገንዘብ ስቻል ብቻ ነው።
“Familiaris consortio” ከተሰኘው እና በቅዱስ ዩሐንስ ጳውሎስ ሁለተኛ ከተጻፈው ሐዋሪያዊ ቃለ ምዕዳን
በመጥቀስ “የመንፈስ ቅዱስ ጥሪ እና ፍላጎት ‘በታሪክ ክስተቶች ውስጥ ስለ ምያስተጋባ’ ተጨባጭ የሆኑ
እውነታዎች ላይ ማትኮር አለብን’ ይህም ደግሞ ‘ቤተ ክርስቲያንን ይበልጥ ጥልቅ ወደ ሆነ የማይነጥፍ የጋብቻ
ምሥጢርን እና ስለ ቤተሰብ ግንዛቤ እንዲኖራት ይረዳል’” (አ.ላ. 31) የሚለው ሀርግ በሰፋት ይተነተንበታል።
በሌላ በኩል እውነታን መረዳት ካልቻልን አሁን ያለውን ፍላጎት ወይም የመንፍስ ቅዱስን እንቅስቃሴ መረዳት
አንችልም ማለት ነው። ቅዱስነታቸው ስያብራሩም “አንድ ሰው እራሱን ለሌላ አሳልፎ እንዳይሰጥ በአሁኑ ጊዜ
እየተሰፋፋ ያለው ግለሰባዊነት (Egoism) ሁኔታዎችን አስቸጋሪ እንደ ምያደርግም” (አ.ላ. 33)
አስገንዝበኋል። አስገራሚው ነገር አሉ ቅዱስነታቸው በቃለ ምዕዳናቸው “ብቸኝነትን መፍራት፣ መረጋጋትን
መፈለግ እና ታማኝነትን ለማግኘት ፍላጎትን ማሳየት ጋር አብሮ ጎን ለጎን የሚጓዝው እነዝህ ነግሮች አንድ ሰው
የግል ግቦችን ለማሳካት የምያደርገውን ጥረት የምያሰናክል ወጥመድ ተደርጎ መወሰዱ ነው” (አ.ላ. 34)
በማለት የግለሰባዊ አስተሳሰብ የፈጠርውን ውስብስብነት ገልጸዋል።
እውነታን የተከተለ ትህትና እና “ከተጨባጭ እውነታ የራቀ ጋብቻን የተመልከተ በጣም ረቂቅ፣ ሰው ሠራሽ
ሥነ-መለኮታዊ ሐሳብ፣ እውነተኛ እና በቤተሰብ ውስጥ ተጋባርዊ ሊሆኑ የማይችሉ ሐሳቦችን” (አ.ላ. 36)
እንድናስወግድ ይረዳናል። ሀሳባዊነት በእራሱ ትዳርን በቅጡ እንድንረዳ አያደርገንም። ያም ማለት “የሰው ልጅ
ግላዊ እድገት ተለዋዋጭ መንገድን የተከተለ ነው” መሆኑን መረዳት ያስፈልጋል። ይህም “የእግዚአብሔርን
ጸጋ በግልጽ እንዲ ቀበሉ ሳናበረታታ ዶክትሪንን፣ የስነ-ሕይወት እና የስነ-ምግባር ጉዳዮችን” (አ.ላ. 37)
ቤተሰብን ይደግፋሉ ብሎ ማሰብ የማይመስል እና ከእውነት እና ከተጨባጭ ሁኔታ የራቀ ሐሳብ ነው።
የጋብቻን እና የቤተሰብ ተሞክሮን ያላማከለ “ትችት” እና በቂ ያልሆነ አቀራረብ እንዲኖር የምያደረግ ተግባር
ተወግዶ በአንጻሩም ቅዱስነታቸው በቃል ሞዳናቸው እንዳሳሰቡት ምዕመናን ሕሊናቸውን እንዲጠቀሙ እድል
መስጠት አስፈላጊ መሆኑን አስረግጠው አሳስበው “የተጠራነው ሕሊናን ለማነጽ እንጂ ሕሊናን ለመቀየር
አይደለም”
(አ.ላ. 37) በማለት ትችትን እና ችኩል የሆነ ውሳኔን ከመውሰድ መታቀብ እንዳለብን አሳስበኋል።
ኢየሱስ የሚጠይቀን ገንቢ የሆኑ ሐሳቦችን እንድንከተል ነው እንጂ “ልክ ስታመነዝር እነደ ተያዘችው ሳምራዊት
ሴት ያሉ ግለሰቦችን መቼም ቢሆን ምሕረቱን እና አለኝታነቱን ፍትሐዊ በሆነ መልኩ ነፍጎ አያውቅም” (አ.ላ.
38) በማለት ፍርደ ገምድል መሆን እንደ ሌለብን እና ሁኔታዎችን አንድ በአንድ መመርመር እንደ ሚገባን
አሳስበኋል ።
ምዕራፍ ሦስት “የቤተሰብ ጥሪ ኢየሱስን መፈለግ ነው” (ከአንቀጽ 58-88)
ሥስተኛው ምዕራፍ ትኩረቱን ያደረገው ጋብቻን እና የቤተሰብ ጉዳይን የተመለከቱ የቤተ ክርስቲያን
አስተምሮዎች ላይ ነው። ይህ 30 አንቀጾች ያሉት ምዕራፍ በጣም አስፈላጊ እና ወቅታዊ ሊባል የምችል ምዕራፍ
ነው። ምክንያቱም የቤተሰብ ጥሪ በወንጌል ላይ ተመስርቶ እና ቤተ ክርስቲያን በጊዜ ሂደት ያረጋገጠችው እና
ምን መሆን እንዳለበት የምናገር እና የምያሳይ በመሆኑ ነው።
ከሁሉም በላይ ትዳር እስከ ሕይወት ፍጻሜ የምጸና መሆኑን የተሰመረበት ሲሆን፣ የትዳር ሚስጢራዊ የተፈጥሮ
ገጽታ እና ሕይወትን ቀጣይ እንዲሆን የማድረግ ተግባሩ እንዲሁም ለሕጻናት ስለሚሰጠው መሰራታዊ
ትምሕርት አስፈላጊነትን ይገልጻል። “Gaudium et Spes” (ደስታ እና ተስፋ) ከተሰኘው የሁለተኛው
የቫቲካን ጉባሄ፣ “Humanae Vitae” (የሰው ሕይወት) ከተሰኘው የጳውሎስ ስድስተኛ አወዲ መልዕክት
እና “Familiaris Consortio” (ቤተሰብ ባለንበት ዘመን) ከተሰኘው የቅዱስ ዩሐንስ ጳውሎስ ሁለተኛ
ሐዋሪያዊ ቃለ ምዕዳን በሰፊው የተጠቀሱበት ምዕራፍ ነው።
ይህ ምዕራፍ “ፍፁም ያልሆኑ ሁኔታዎችን” በሰፊው የምመለከት እና የምዳስስ ምዕራፍ ጭምር ነው።
“በሌሎች ባሕሎች ውስጥ ‘ፍሬማ የሆኑ ዘሮች’” (Ad Gentes 11 በአማሪኛ ለሕዝብ) መኖራቸው የተገለጸ
ሲሆን ይህም ደግሞ ከጋብቻ እና ከቤተስብ ነባራዊ እውነታ ጋር በማጣመር መገለጹ በእዝህ ምዕራፍ ውስጥ
መመልከት ይቻላል።
“ተፈጥሮአዊ እና እውነተኛ ከሆነው ጋብቻ በተጨማሪም አንድ አንድ ጊዜ ድንግዝግዝ ሆኖ ቢታይም አዎንታዊ
የሆኑ ግንቢ ነግሮች በሐይማኖታዊ ወግ የተፈጸመ ጋብቻ ውስጥ ይገኛሉ” (አ.ላ. 77)። “በስቃይ ውስጥ
የሚገኙ ቤተሰቦች” በማለት ቅዱስነታቸው በ2015 በተካሄደው ሲኖድስ የማጠቃለያ ሪፖርት ላይ እንደ
ገለጹት እና በትዳር ሕይወት ውስጥ በገጠማቸው ችግር የምሰቃዩ ሰዎችን ሁኔታን የሚዘረዝር ሐሳብ በእዝህ
ምዕራፍ በሰፊው የተዳሰሰ ሲሆን “’እረኞች ማወቅ ያለባቸው ነገር ውሳኔ ከመወሰናቸው በፊት ስለ እውነት
ሲባል በጥንቃቄ ሁኔታዎችን የመመርመር ግዴታ እንዳለባቸው የምያስገድዳቸውን አጠቃላይ መርዕ ማስታወስ
ምንጊዜም አስፈላጊ ነው” (Familiaris Consortio. 84) በማለት በውሳኔ አሰጣጥ ወቅት ጥንቃቄ መደረግ
እንዳለበት አሳስበኋል። “ኋላፊነትን መሰረት ያደርጉ ውሳኔዎች በሁሉም ሁኔታዎች ውስጥ ተመሳሳይነት ባለው
መልኩ ሊተገበር እንደ ማይገባ እና በአንድ አንድ ሁኔታዎች የሚደረጉ ውሳኔዎችን የመገደብ አጋጣሚ
ልያስከስቱ ይችላሉ። ስለ እዝህ የቤተ ክርስቲያንን አስተምሮ በግልጽ መተግበር አስፈላጊ ቢሆንም መጋቢው
ወይም እረኛው የነባሪዊ እውነታውን ውስብስብነት ሳያጤን፣ በትኩረት ሳይመልከት፣ ሰዎች ተመኩሮ እና
በችግራቸው ምክንያት እያሳለፉ ያለውን ስቃይ ሳያገናዝብ ውሳኔ ከመውሰን ልቆጠብ ይገባኋል”
(አ.ላ.79)በማለት አሳስበኋል።
ምዕራፍ አራት “ፍቅር በቤተሰብ ውስጥ” (ከአንቀጽ 89-164)
አራተኛው ምዕራፍ ትኩረቱን ያደረገው ቅዱስ ሐዋሪያው ጳውሎስ ወደ ቆሮንጦስ ሰዎች በጻሐፈው የመጀመሪያ
መልዕክቱ በምዕራፍ 13,4-7 ላይ መሰረቱን በማድረግ ፍቅር በትዳር ውስት ያለውን ሚና ይገመግማል።
የእዝህ ምዕራፍ የመክፈቻ ክፍል በእርግጥም እጅግ አድካሚ ሊባል የሚችል ሥራ ወይም ተግባራት የታየበት
እና በቅዱስ ጳውሎስ መልዕክት አነሳሽነት የተጻሐፈ እንዲሁም ትኩረቱንም በእዝሁ መልዕክት ላይ ያደረገ
ነው።
ይህም በጥንቃቄ የተጻሐፈ እና ተጨባጭ በሆነ መልኩ በሰው ልጆች መኋል ሊኖር ስለ ሚገባ ፍቅር የምገልጽ፣
ይህንንም የምያረጋግጥ እና ለይቶ የምያሳውቅ ስነ-ልቦናዊ ሐሳቦችን በመመርኮዝ ተገቢውን ምላሽ የምሰጥ
ነው። እነዝህ ስነ-ልቦናዊ ማብራሪያዎች በትዳር ዓለም ውስጥ በመግባት የምታዩትን አዎንታዊ እና አሉታዊ
ሁኔታዎች በመዳሰስ፣ ስሜት ቀስቃሽ የሆኑትን የፍቅር እሴቶችን በሚገባ ይዳስሳል። ይህም በክርስትና ደንብ
ጋብቻ ለፈጸሙ ሰዎች ሁሉ ትዳርን በተመለከተ ቱባ እና ጠቃሚ የሆነ አስተዋጾ በማድረግ ረገድ ይህ ሐዋሪያዊ
ቃለ ምዕዳን ቀደም ሲል የነበሩ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ከጻፉኋቸው ሐዋሪያዊ መልዕክቶች ሁሉ ለየት እንዲል
ያደርገኋል።
በተጨማሪም ይህ ክፍል ሰፊ እና ውስብስብ የሆነውን የትዳር ሕይወትን አጭር በሆነ መልኩ ዕለት በዕለት
የሚከናወኑ ነባራዊ ጉዳዮች ላይ ትኩረቱን አድርጎ እና በጋብቻ ውስጥ ያለውን የፍቅር ተመኩሮ በመውሰድ
በሚታዩት ነባራዊ ሁኔታዎች ላይ ተንተርሶ፣ መስፈርቶችን ተጠቅሞ ፍርድ ከመስጠት ቅዱስነታቸው ተቆጥበው
“ፍጹም በሆነ በክርስቶስ እና በቤተክርስቲያን መካከል ባለው አንድነት ላይ ተመርኩዞ ሁለት ውስን የሆኑ
ሰዎች ላይ ከፍተኛ ጫና መጫን አስፈላጊ አይደለም ምክንያቱም ጋብቻ በተፈጥሮው ተለዋዋጭ ሂደትን
የምያስተናግድ በመሆኑ፣ እነዝህ ሰዎች ቀስ በቀስ ከእግዚአብሔር ስጦታ ጋር ይዋሀዱ ዘንድ ማገዝ ያስፈልጋል”
(አ.ላ. 112) በማለት አጠቃላይ የሆኑ መስፈርቶችን ተጠቅሞ ከመፍረድ በመቆጠብ የሰው ልጆችን ውስንነት
ከግምት ያስገባ ጠንቃቃ ውስኔ ማድረግ አንደ ሚገባ አስምረውበታል።
በሌላ በኩል ደግሞ ቅዱስነታቸው በጣም ጠበቅ ባለ ሁኔታ “ሊታወቅ እና ሊከበር የሚገባው ሀቅ በትዳር
ሕይወት ውስጥ ያለው ፍቅር በተፈጥሮ የምያስረዳን ይህ ፍቅር ተጠብቆ ዘላቂ አንድነት እንዲኖር መሆኑ
መረሳተ እንደ ሌለበት” (አ.ላ. 123) በአጽኖት ገልጸው በአጭሩም በትዳር ውስጥ “ደስታ እና ትግል፣
ውጥረት እና እረፍት፣ ጭንቀት እና እፎይታ፣ ህመም እና ፈውስ፣ እርካታ እና ምኞት፣ ንዴት እና ተድላ” (አ.ላ.
126) . . . ወዘተ የመሳሰሉትን ተነጻጻሪ ተግባርት እንዲሁም የችግሮች እና የደስታ ቅልቅል ውጤት መሆኑን
ማወቅ አስፈላጊ መሆኑን ያስረዱናል።
አራተኛው የአሞሪስ ላኤቲቲአ (የፍቅር ሐሴት) ምዕራፍ መደምደምያውን የምያደርገው “የፍቅር ለውጥ”
በሚለው አርዕስት ላይ ተመርኩዞ በጣም አስፈላጊ ሊባል የምችሉ ሐሳቦችን በመሰንዘር ሲሆን “በአሁኑ ወቅት
ረዘም ያለ እድሜ ማለት የቅርብ እና ለየት ያለ ምን አልባትም የአራት እና የአምስት ወይም የስድስት አስርተ
አመታት ግንኙነት ማለት ሊሆን ይችላል፣ በዝህም ምክንያት የመጀመሪያው ውሳኔ በተደጋጋሚ መታደስ
አለበት” (አ.ላ. 163) በማለት ፍቅር ተደጋጋሚ የሆነ እድሳት እንደ ምያስፈልገው ያትታል። አካላዊ ቁመናችን
እንደ ምያሳስበን እያደግን በመጣን ቁጥር ፍቅራዊ መሳሳብ እየቀንሰ የሚመጣ ነገር ሳይሆን በአንጻሩም ከጊዜ
ወደ ጊዜ የሩካቤ ሥጋ ፍላጎታችን በማደስ አብሮነታችሁን እንድታጠብቁ እና በጋራ በጉጉት መኖር እንድትችሉ
ያደርጋል፣ በሕይወት ዘመናችን ሁሉ አንድ አይነት የሆነ ስሜት ሊሰማን ይገባል የሚል ምንም ዓይነት ዋስትና
የለም። ሆኖም አንድ ባልና ሚስት የሚጋሩት አንድ የጋራ እና ዘላቂ ሕይወት ውጥን ካለቸው እርስ በእርስ
ልዋደዱ ይችላሉ እስከ ሕይወት ፍጻሜኋቸው ድረስም አንድ ሆነው ይኖራሉ የጠበቀ እንድነታቸውንም
ያበለጽጋሉ” (አ.ላ. 163) በማለት ከሁሉም በላይ በትዳር ውስጥ የጋራ የሆነ የሕይወት ውጥን አስፈላጊነት
አስረግጠው የገለጹበት ምዕራፍ ነው።
ምዕራፍ አምስት “ፍቅር ፍሬያማ ያደርጋል” (ከአንቀጽ 165-198)
የአሞሪስ ላኤቲቲአ አምስተኛ ምዕራፍ ሙሉ በሙሉ ትኩረቱን ያደረገው ፍቅር የምያስገኘውን ፍርሬ እና ስነ-
ውልደት ላይ ትኩረቱን ያደረገ ነው። መንፈስዊ እና ስነ ልቦናዊ በሆነ መልኩ አዲስ እርግዝናን ስለ መቀበል፣
በእርግዝና ወቅት ስለ ሚታየው የውልደት ቀን ጥበቃ፣ እንዲሁም ስለ እናት እና አባት ፍቅር በጥልቀት
ይዳስሳል።
በተጨማሪም ፍሬያማ ስለሆነ ጉድፈቻ፣ “የአብሮነትን ባሕል” እና የቤተሰባዊ ኑሮን ሰፋ ባለ መልኩ ማለትም
አክስትን፣ አጎትን፣ የአክስት እና የአጎት ልጆችን፣ ዘመዳ ዘመዶችን እንዲሁም ጓደኝነትን ለምያበረታቱ እና
ለእዝህም አስተዋጾ የምያደርጉትን ቤተሰቦችን በተገቢው መልኩ ያወድሳል። አሞሪስ ላኤቲቲአ ወይም የፍቅር
ሐሴት ቃለ ምዕዳን ቤተሰብን የሚረዳው በጣምስ ሰፋ ባለ መልኩ በመሆኑ ምክንያት “በቅርብ የቤተሰብ
አባላት ብቻ” ወይም በእንግሊዜኛው (nuclear family) ማለትም (እናት፣ አባት፣ ወንድም፣ እህት፣ አያት
የመሳሰሉ የቅርብ ጸመዶች) ትኩረቱን አላደረገም። “በቤተ ክርስቲያን ሚስጢራት የታነጸ ጋብቻ ማሕበራዊ
ገጽታ አለው” (አ.ላ.187)። ከእዝህ ማሕበራዊ ገጽታ በመነሳት ቅዱስነታቸው ለየት ባለ ሁኔታ ማጉላት
የፈለጉት በወጣቶች እና በአረጋዊያን መኋከል የሚፈጠርውን ግንኙነት በማሕበርሰቡ ውስጥ የተለየ ሚን እንደ
ምጫወት እና እንዲሁም በወንድም እና እህት መካከል ያለው ጥብቅ ግንኙነት ደግሞ ከሌሎች ጋር በቀጣይነት
ለሚደረጉ ግንኙነቶች እንደ መለማመጃ ሜዳ መሆኑንም በተጨባጭ የገለጹበት ምዕራፍ ነው።
ምዕራፍ ስድስት “ሐዋሪያዊ አመለካከቶች” ከአንቀጽ (199-258)
በስድስተኛው ምዕራፍ ቅዱስነታቸው ተጨባጭ በሆነ መልኩ እና በእግዚአብሔር እቅድ ላይ የተመሰረተ
ፍሬያማ የሆነ ቤተሰብ ለመመስረት አስተዋጾ የምያደርጉትን በዛ ያሉ ሐዋሪያዊ ተግባራትን የዳሰሱበት ምዕራፍ
ነው። ይህ ምዕራፍ በተጨማሪም በቤተሰብ ዙሪያ የመከርውን የመጀመሪያ እና የሁለተኛው ሲኖዶስ አጠቃላይ
ሪፖርት የያዘ ሲሆን፣ ቅዱስነታቸው በተለያዩ አጋጣሚዎች ያስተላለፉኋቸውን የቤተ ክርስቲያን አስተምዕሮችን
እንዲሁም ከቅዱስ ዩሐንስ ጳውሎስ አስተምሮዎችም የተውጣጡ ሐሳቦች ይገኙበታል። ቤተሰብ ሁል ጊዜ
መሰብክ የለበትም ቤተሰብ አንድ አንዴ ልሰብከን ይገባል ብለኋል በእዝህ ምዕራፍ። ቅዱስነታቸው “ካህናት
ብዙን ጊዜ ቤተሰብ እየተጋፈጠ ያለውን የተወሳሰቡ ችግሮችን የመፍታት ችሎታ አለማዳበራቸውን” (አ.ላ.
202) ጸጸት በተሞላው መልኩ ገልጸኋል። በሌላም በኩል ደግሞ የዘርሃ ክህነት ተማሪዎች ስነ ግንኙነትን
የተመለከተ አስተምዕሮ መሻሻል እንደ ሚገባው እና በዘርሃ ክህነት በሚሰጠው የሕንጸት ትምሕርት ቤተሰብ
ልሳተፍ ይገባል (አ.ላ. 203) ብለው በሌላም በኩል “ የምስራቃዊ አብያተ ክርስቲያናት አባላት የሆኑ ያገቡ
ካህናት ልምዳቸውን እንድያካፍሉ ሊጋበዙ ይገባል” (አ.ላ. 202) የሚልም ሐሳብ የተንጸባረቀበት ነው።
በመቀጠልም ቅዱስነታቸው የዳሰሱት ለጋብቻ ዝግጅት ስለ ምሰጠው አስተምህሮ ሲሆን፣ በተለይም ደግሞ
ተጋቢዎች በመጀመሪያው ዓመት የጋብቻ ሕይወታቸው ስለ ሚደርገግላቸው መንፈስዊ ድጋፍ በማውሳት
ሀላፊነት የምሰማቸው ወላጆች እንዲሆኑ፣ ውስብስብ በሆኑ ሁኔታዎች እና በመከራ ወቅት ሁሉ “እየ አንድ
አንዱ መከራ አስተምሮ የምያልፈው ትምሕርት መኖሩን እና በልቦናችን የምያስተላልፍልንን ትምሕርት
በማዳመጥ” (አ.ላ. 232) እና የችግሮች ሁሉ መነሻ በጥልቀት ከተጠና ቡኋላ የችግሮችን መንስሄ ስይዘገዩ
በአጭሩ መቅጨት (አ.ላ. 239) መልመድ ይኖርብናል የሚል ሐሳብ የተንጸባረቀበት ነው።
በተጨማሪም የተረሱ፣ የተለያዩ እና የተፋቱ ቤተሰቦች መንፈስዊ ድጋፍ እነደ ምያስፈልጋቸው ያሳስባል። ይህ
ሐዋሪያዊ ቃለ ምዕዳን እየተሻሻለ ያለውን እና ሁኔታዎች በሚገባ ከተጠኑ ቡኋላ አስፈላጊ ሆኖ ከተገኘ
ሚስጢረ ተክሊልን እንዳልነበረ (anulation) የማድረግ ሥልጣን ያለውን እና በመርቀቅ ላይ የሚገኘውን
ሕግ አስፈላጊነትን ያጠናክራል። በተጨማሪም በግጭት ምክንያት እየተሰቃዩ የሚገኙ ሕፃናትን ሁኔታ በስፋት
በመዳስስ “ፍቺ ክፉ ነገር ነው። ስለ ዝህም የእኛ ሐዋሪያዊ ሥራ ዋና ተግባር መሆን ያለበት በቤተሰብ ውስጥ
ፍቅር እንዲጠናከር መርዳት ነው” (አ.ላ. 246) በማለት ፍቺ የምያስከትለውን ማሕበራዊ እና ቤተሰባዊ
ቀውስን ይዘረዝራል። በመቀጠልም በአንድ የካቶሊክ አማኝ እና በሌላ የክርስትና እመነት ተከታይ መካከል ስለ
ሚፈጸመው ጋብቻ (mixed marrige) እንዲሁም በአንድ የካቶሊክ እምነት ተከታይ እና የክርስትና መሰረት
በሌለው እምነት ተከታይ በሆኑ ሰዎች መካከል የምፈጸመው ጋብቻ (የአምልኮ አለመመጣጠን የምታይበት)
መካከል ስለ ሚፈጸመው ጋብቻ ያትታል።
ምዕራፍ ሰባት “የልጆች የተሻለ የትምህርት አቅጣጫን” (ከንቀጽ 259-290)
የአሞሪስ ላይቲቲአ ሐዋሪያዊ ቃለ ምዕዳን ሰባተኛው ሞራፍ ለልጆች የሚሰጠውን መሰረታዊ ትምሕርት
በሰፊው በመዳሰስ፣ ስነ ምግባራዊ ሕነጻን፣ ስነ ስርዓት ይማሩ ዘንድ ቅጣትን ያካተተ ተግሣስ መስጠትን፣
በትዕግሥት እውነታን ማስተማርን፣ የስነ ፃታ ትምሕርት መስጠትን፣ እምነትን ማስተላለፍ ወይም ማውረስን፣
በአጠቃላይ የቤተሰብ ሕይወትን መሰረት ያደርገ አስተምዕሮ መስጠት እንደ ሚገባ ያሳስባል። በእዝህ ምዕራፍ
ውስጥ የሚታየው ጥበባዊ አገላለጽ ትኩረትን ልስብ የምችል ሐሳቦች የተጠቀሱበት ሲሆን በተለይም ደግሞ
እርጋታን የተሞላ ሂደት የተከተለና መከተል ያለብንን መንገድ “በሚገባ፣ ተቀባይነት እና ተደናቂነትን”
(አ.ላ.271) በተላበሰ መልኩ ለሰዎች በምያጎናጽፍ መልኩ በዝርዝር ተቀምጡኋል።
በእዝህ ምዕራፍ ውስጥ በጣም ማራኪ እና ሳይንሳዊ የማስተማር ዘዴን የተከተሉ መሰረታዊ አሳቦች
የተጠቀሱበት አንቀጾች የሚገኙ ሲሆን በተለይም ደግሞ ቅዱስነታቸው ግልጽ በሆነ መልኩ “ውትወታ
ትምሕርት ሊሆን አይችልም፣ ልጆች ሊያጋጥማቸው የሚችለውን እየ አንድ አንዱን ሁኔታ መቆጣጠር
አንችልም. . .ቤተሰብ ልጆቻቸው የምያከናውኑትን እየ አንድ አንዱን ተግባር ለማወቅ በምያሳዩት ከፍተኛ
ጉጉት እና እየ አንድ አንዱን እንቅስቃሴ ለመቆጣጠር የምያደርጉት ጥረት ሁኔታዎች ላይ ጫና ይፈጥራል። ነገር
ግን ይህ ተግባር ልጆቻቸው ለውደፊት የምገጥሙኋቸውን ፈተናዎች ለመቋቋም እንዲችሉ ለማዘጋጀት እና
ጠንካራ እንዲሆኑ ለማስተማር የሚበጅ መንገድ አይደለም። በጣም አስፈላጊው ነገር በፍቅር እና በነፃነት
እንዲሁም በብስለት እንድያድጉ መርዳት፣ አጠቃላይ በስነ ሥረዓት እና እርሳቸውን በመግዛት” (አ.ላ. 260)
እንድያድጉ ማድረግ ያስፈልጋል የሚል አሳብ የተንጸባረቀበት ነው።
ምዕራፍ ስምንት “መምራት፣ መወሰን እና ድክመትን ማቀናጀት” (ከአንቀጽ 291-312)
ስምንተኛው ምዕራፍ ወደ ምሕረት የምጋብዝ እና ከጌታ ሐሳብ ጋር ሙሉ በሙሉ የማይስማሙ ወይም
የማይዛመዱ ሁኔታዎችን በማስተዋል ሐዋሪያዊ ሥራን ማከናወን እንደ ሚገባ የምያሳስብ ነው። ቅዱስነታቸው
በእዝህ ምዕራፍ መምራት፣ ማስተዋል እና ማቀናጀት ወይ ማዛመድ የሚሉ ሦስት መሰረታዊ የሆኑ ግሦችን
በመጠቀም በቀላሉ ለአደጋ ሊጋለጡ የምችሉ፣ ውስብስብ ጉዳዮችን እና ያልተለመዱ ሁኔታዎችን ለመፍታት
መጠቀም አስፈላጊ መሆናቸውን የገለጹበት ምዕራፍ ነው።
በተጨማሪም ሐዋሪያዊ ተግባራት ርህራሄን በተሞላው መልኩ መፈጸም እንደ ሚገባቸው የምያሳስብ ክፍል
የተካተተበት ሲሆን በተለይም ደግሞ ማስተዋል አስፈላጊ እንደ ሆነ፣ ደንቦችን የማቅለያ ሁኔታዎች በሐዋሪያዊ
ሥራ ውስጥ በማስተዋል እንዲተገበሩ የምመክር ሲሆን በመጨረሻም ቅዱስነታቸው “በማስተዋል ጥበብ
የተሞላ ሐዋርያዊ ምሕረት” ማድረግ እንደ ሚገባ የምተነትን ጭምር ነው።
ምዕራፍ ስምንት በጣም አጉዋጊ ምዕራፍ ነው። ምክንያቱም አንድ ሰው ይህንን ምዕራፍ በምያነብበት ወቅት
“የቤተ ክርስትያን ተግባር ልክ እንደ አንድ ሆስፒታል ተግባር” (አ.ላ. 219) መሆኑን ከግንዛቤ በማስገባት
እንድያነብ የሚጋብዝ በመሆኑ ነው። ቅዱስ አባታችን ቀደም ሲል በተካሄዱት ሲኖዶሶች ላይ በተነሱ አከራካሪ
የሆኑ ጉዳዮች እና የተወሰኑ ውሳኔዎች ላይ የታገሉበትን ፍሬ ሐሳብ ይተነትናል። ክርስቲያናዊ ጋብቻን
የሚመለከት እና ቤተ ክርስቲያን በማንኛውም ሆኔታ “ስለ ጋብቻ ያላት ግንቢ እና ዋና ዋና አስተምሮዎችን
እየተጋፉ ያሉትን እና ለወደፊቱ የምከሰቱትን ጋብቻን የተመለከቱ ከአስተምሮዋ ጋር የማይዛመዱ አስተሳሰቦችን
በንቀት ልትመለከት አይገባም” (አ.ላ. 292) የሚል ማሳሰብያ ያዘለ ነው።
ልማዳዊ ያልሆኑ ሁኔታዎች በምያጋጥሙበት ወቅት ልደርግ ስለ ሚገባው ማስተዋል ቅዱስነታቸው ሲጠቅሱ
“የሁኔታውን ውስብስብነት በቅጡ ስያጤኑ እና ሰዎች በችግራቸው ምክንያት እየኖሩት ያለውን የጭንቀት
ሕይወት በትኩረት ሳይመለከቱ ማንኛውንም ዓይነት ውሳኔ ካማስተላለፍ እንዲቆጠቡ” (አ.ላ. 296) የቤተ
ክርስቲያን መሪዎችን ያሳስባሉ። በመቀጠልም “እገዛ የምያስፈለጋቸውን ሰዎች በቤተ ክርስቲያን ማሕበርሰብ
ውስጥ ተሳታፊ እንዲሆኑ እና ‘ያለ አንዳች ቅድመ ሁኔታ ለማይገባውም እንኳን በነጻ በሚሰጥ ምሕረት ይዳሰሱ
ዘንድ ሁሉም የክርስቲያን ማሕበርሰብ አጥጋቢ በሆነ መልኩ የእራሳቸውን አስተዋጾ ማድረግ እንደ
ሚጠበቅባቸው’” (አ.ላ. 297) የምጋብዝ ምዕራፍ ጭምር ነው።
“መጀመሪያ መስርተወት ከነበረው ትዳር በመፋታት አዲስ የሆን ግንኙነት የጀመሩ ሰዎች ለምሳሌም፣ በተለያየ
ዓይነት ሁኔታዎች ውስጥ የሚገኙ ሰዎችን እና ጥብቅ ከሆነ የቤተ ክርስቲያን አስተምሮ እና ሐዋሪያዊ ተግባር
ጋር አብሮ የማይሄዱ ተግባሮችን የሚፈጽሙ ሰዎችን በተመለከተ ማስተዋልን የተላበሰ ሐዋሪያዊ ተግባራትን
ማከናወን ያስፈልጋል (አ.ላ. 298) በማለት ያትታል።
ይህንን በተመለከተ ቀደም ሲል በተደርገው ሲኖዶስ ለተሳተፉ ጳጳሳት ቅዱስነታቸው “ፍቺ የፈጸሙ እና
በማዘጋጃ ሌላ አዲስ ትዳር የመሰረቱ ክርስቲያኖች በክርስቲያን መሕበርሰብ ውስጥ ለሌሎች እንቅፋት
በማይሆን መልኩ ሙሉ በሙል ተሳታፊ እንዲሆኑ ማድረግ እንደ ሚገባ” ማሳሰባቸው ይምታወስ ነው። “እንደ
እነዚህ አይነት ሰዎች ምንም ዓይነት በቤተ ክርስቲያን እንደ ተወገዙ እንዲሰማቸው የምያደርገውን ተግባር
በማስወገድ በምትኩም የቤተ ክርስቲያን ቋሚ አባል

 








All the contents on this site are copyrighted ©.