2016-04-25 15:11:00

ዓለም ኣቀፍ የመሬት ቀን


ሁሌ  በየዓመቱ ሚያዝያ 22 ቀን የሚከበረው ዓለም አቀፍ የመሬት ቀን ምክንያት በሮማ የኢጣሊያ የመሬት ቀን ማኅበር ከአፍቅሮተ ዘቤት ካቲሊካዊ እንቅስቃሴ ጋር በመተባበር ሮማ በሚገኘው ቪላ  ቦርገዜ ተብሎ በሚጠራው የመናፈሻ ሥፍራ  ባተዘጋጀው ሥነ ስርዓት ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ተገኝተው ባስደመጡት ንግግር፥ ምድረ በዳ ወደ ልምላሜ የደን ሃብት ሥፍራ ለመቀየር የሚታገለግሉ ናችሁና እናመሰግናችኋለን እንዳሉ የቫቲካን ረዲዮ ልኡክ ጋዜጠኛ አለሳንድሮ ደ ካሮሊስ አስታወቁ።

በዚህ  በሮማ ከተማ እምብርት በሆነው ክልል በሚገኘው የመናፈሻ ሥፍራ ለአራት ቀን በተዘጋጅነው ሥነ ስርዓት ምክንያት ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ እ.ኤ.አ. ሚያዝያ 24 ቀን 2016 ዓ.ም. በሮማ ሰዓት አቆጣጠር ከሰዓት በኋላ ልክ 5 ሰዓት እንደደረሱም በአፍቅሮተ ዘቤት ካቶሊካዊ እንቅስቃሴ ሊቀ መንበር ማሪያ ቮቸና ተባባሪ ሊቀ መንበር ኸሱስ ሞራን አቀባበል ተደርጎላቸው እዚያው ለተሰበሰቡት 3 ሺሕ 5 መቶ ሰዎች ሰላምታ አቅርበው፥ ምድረ በዳው ወደ ለመለመ የአረጓንዴ ሃብት ለመቀየር የምትጥሩ ናችሁና ደስ ይበላችሁ። በአሁኑ ሰዓት ሰዎችን ለአደጋ የሚያጋልጡ ሰብአዊ ልማዶች ሁሉ እንዲቀረፉ፡ በሕዝቦችና በባህሎች እንዲሁም በተለያዩ ሃይማኖቶች መካከል መተዋወቅ መግባባት እንዲኖር የምታከናውኑት የውይይትና የግኑኝነት መርሃ ግብር በእውነት የሚመሰገንና አብነትም ነው እንዳሉ የገለጡት የቫቲካን ረዲዮ ልኡክ ጋዜጠኛ ደ ካሮሊስ አያይዘው፥ ቅዱስ አባታችን  ባሰሙት ንግግር ግጭት ወይንም ቀውስ የሚለው ቃል በቻይናኛ ቋንቋ በሁለት ምልክት የሚገለጥ ሲሆን የመጀመሪያው ስጋት ወይንም አደጋ የሚል ሲሆን ሁለተኛው ምልክት ደግሞ አጋጣሚ የሚል ትርጉም ያለው መሆኑ አብራርተው፡ ስለዚህ ለመተዋወቅ ለመቀራረብ አለ ምንም ፍርሃት ስጋቱን መጋፈጥ አለብን፡ ጀርባ ሰጥቶ እየተያዩ እንዳልተያዩ ተኵኖ መተላለፍ አደራ ይወገድ። ካልከፈልክ አትኖርም የሚለው በማኅበራዊ ኑሮ ማእከል የሆነው ገበያነት የሚል ፖለቲካዊ ኤኮኖሚያዊ አስተሳሰብ በእውነቱ ዓለም የገንዘብ ሃብት የሚያመልክ መሆኑ የሚያረጋግጥ  ነው፡ ገንዘብ እንደ ጣዖት በማምለክ ጎዳና ሲራመድ ለዚህ ጣዖት የማምለኩ ምርጫም ብዙ ሕዝብ በእርሃብ በሽታ እንዲጠቃና ለተለያዩ የጭቆናና የብዝበዛ አደጋ እንዲጋለጥ እያደረገ ነው ብለው እየተኖረ ያለው የምኅረት ቅዱስ ዓመት በማሰብ ቂም በቀልተኝነት ቂም ይዞ መኖር የመሳሰሉት ሁሉ ወደ ጎን በመተው ምኅረት በማስቀደምና እርስ በእርስ በመማማር ሁላችን ይቅርታ የምንጠይቅበት ግድፈት ያለን መሆናችን አውቀን፡ በጋራ በመከባበር እንኑር። እንዲህ ያለ ኅብረተስብ ስናቆም በእውነቱ ምድረ በዳነት ወደ የለመለመ ሥፍራ ሲለወጥ እናያለን። ምድረ በዳነት በተፈጥሮ ላይ በሰው ልብ ውስጥ በማኅበራዊና ስብአዊ ዘርፍ ሁሉ የሚከሰት፡ በጥጋ ጥጉ የከተሞቻችንና የህልውና ሥፍራ ሁሉ ያለ ሁነት ነው። በከተሞቻችን መንገዶች በገዛ እራሱ የተዘጋ ከፊት ፈገግታ የተነጠለው ርህራሄ ማኅበራዊ ወዳጅነት የማያመለክት ፊት እናያለን ማኅበራዊ ወዳጅነት በሌለበት ሥፍራ ጥላቻ ጦርነት አለ፡ ይኽ ደግሞ በአሁኑ ወቅት እየተኖረ ያለው በተፈራረቅ የሚታየው ሦስተኛው የዓለም ጦርነት ይመሰክረዋል። ማኅበራዊ ወዳጅነት በነጻ ሌላውን ለመቀበል ዝግጁ በመሆን የሚከወን ሲሆን። ይኽ ደግሞ በስፖርት በስነ ጥበብ በተለያየ ሁነት  የሚገለጥ በጋራ መሆን ደስ እንደሚያሰኝ የሚመሰክር ነው። በዚህ ጠቅላላው የመሆን ጉዳይ በገበያ የሚገለጥና በገዥና አቅራቢ ግኑኝነት አይነት በሚኖርበት ዓለም በእውነቱ በነጻ መስጠት እንዲዘነጋ እያደረገ ነው። እንዲህ ያለ ሁነት በሚኖርበት ዓለም በምድረ በዳነት የተጠቃው ወዳጅነት መቀራረብ ማኅበራዊ ወዳጅነት ለመገንባት እርሱም ምድረ በዳነቱን ወደ ልምላሜ ለመለወጥ የሚተጉ ሁሉ የተመሰገኑ ናቸው እንዳሉ የቫቲካን ሬዲዮ ልኡክ ጋዜጠኛ ደ ካሮሊስ ገለጡ።

ቅዱስ አባታችን የለገሱት ምእዳን ሲያጠቃልሉ፡ ሁላችን የአንድ አባት ልጆች መሆናችን አውቀን ጌታ ሆይ ልጆችህ በመሆናችን ወንድማማቾች ነን። እያንዳንዱ የምንኖርበት ዓለም የበለጠ እንዲሆን  ሁሉም በእኩልነት በወንድማማችነት በመተሳሰብ የሚኖርበት እንዲሆን በማድረግ ዓላማ ተልእኮ ያለው ነው። ተፈጥሮና ፍጥረት ለመከላከል ሰው ሁሉ ተከብሮና ተከባብሮ የሚኖርበት ሰብአዊ ክብሩ የሚጠበቅበት ሥራ አግኝቶ ገዛ እራሱን ረድቶ ሌላውን በመርዳት የሚኖርበት ዓለም በመገንባቱ ሂደት ጌታ ሆይ ደግፈን። እኛ ልጆችህን ትባርክም ዘንድ እንለምንሃለን በሚል ጸሎት ማጠቃለላቸው ደ ካሮሊስ ገለጡ።








All the contents on this site are copyrighted ©.