2016-04-22 16:23:00

የቅ.አ.ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ መልእክት ለድራዊ ግኑኝነት ተማሪዎች ማኅበር


የአርጀንቲና የድራዊ ግኑኝነት ወጣቶች ማኅበር ያንን ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ይሴባሕ በሚል ርእስ ሥር የደረሱት የሁላችን የጋራ ቤት የሆነውን ተፈጥሮ መንከባከብ ያለው አስፈላጊነት የሚያብራራውን ዓዋዲ መልእክት መርህ በማድረግ የአርጀቲና የአቢያተ ትምርት ድራዊ ግኑኝነት ወጣቶች ማኅበር አባላት ወደ ሰሜን ዋልታ ክልል የሰላም ምልክት የሆነውን የወይራ ዝንጣፊ በመያዝ በዓለማችን ክልል እየተከስተ ያለው የተፈጥሮ ብከላና በተፈጥሮ ላይ የሰው ልጅ ያኗኗር ስልት እንዲያጋጥም እያደረገው ያለው ለውጥ በተፈጥሮና በፍጥረት ላይ እያስክሰተለው ያለው አደጋ እንዲወገድ ያኗኗር ስልት መቀየር ያለው አስፈላጊነት ለማስተጋባትና ለሰው ልጅ ደህንነት የብሔር አቢይ ጥረት ለማነቃቃት  በሚል ዓላማ በላቲን አመሪካ በዓይነቱ ለመጀመሪያ ጊዜ የአርጀንቲና ወጣቶችን በመወከል አንዳንድ የአቢያተ ትምህርት ድራዊ ግኑኝነት ማኅበር አባላት ወደ ሰሜናዊ ዋልታ ክልል መላካቸው የአርጀንቲና ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት ያሰራጨው መግለጫ ይጠቁማል።

ይኽ የካርተሪያ ማኅበር ያዘጋጀው በዓለማችን ተፈጥሮና ፍጥረትን ለመንከባከብ ይሴባሕ ዓዋዲ መልእክት መርህ በማድረግ የሁሉም ኃላፊነት ለማነቃቃት በሚል ዓላማ ወደ ሰሜናዊ ዋልታ ክልል የተላኩት ወጣቶች የዚያ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ገና የቦኖስ አይረስ ሊቀ ጳጳሳት እያሉ የመሠረቱት ዓለም ዓቀፍ የአቢያተ ትምህርት ድራዊ ግኑኝነት ማኅበር አባላት  ሲሆኑ በዚህ የምኅዳር ጥበቃ ዘመቻ ወደ ሰሜናዊ ዋልታ መላኩ ምክንያት ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ለልኡካኑ ወጣቶች መልእክት ማስተላለፋቸው የቅድስት መንበር መግለጫ ይጠቁማል።

የተፈጥሮ ብከላ አደገኛነት

ቅዱስ አባታችን ባስተላለፉት መልእክት የተፈጥሮ ብከላ አደገኛነቱ ላይ ያተኰረ ሲሆን፡ የሰው ልጅ በሚከተለው የልማት ሥልት በተፈጥሮና በፍጥረት ላይ እያስከተለው ያለው አሳሳቢ  ጉዳት የልማቱ ሥልት ተቀባይነት ያለው አለ መሆኑ እንደሚያስገነዝብ በማብራራት ፍትህ ለተፈጥሮ ፍትህ ለፍጥረት ፍትኃዊነት ለበስ የተፈጥሮ ሃብት በእኩል ማዳረስ በሚል ዓላማ የሚመራ የልማት እቅድ ወሳኝ ነው እንዳሉ የገለጠው የቅድስት መንበር መግለጫ አክሎ፥

የኅብረት ሥራ ለያዩን የግንብ አጥር ወደ አገናኝ ድልድይ እንዲለወጥ ያደርጋል

እናንተ የዚህ ዘመቻ ተሳታፊ ወጣቶች የምትገልጡት ፍቅር ታታሪነትና  የኅብረት  ተግባር ለያዩን አጥር ወደ አገናኝ ድልድይ መለወጥ እንደሚቻል የሚያረጋግጥ  ነው ያሉት ቅዱስ አባታችን  መልእክቱን፡ ወጣቶቹ ለሚያካሂዱት እንቅስቃሴ በማመስገን በዚህ ዘመቻ እንድትሳተፉ ፈቃዱን ለሰጡዋቸው ቤተሰቦቻቸውንና የተባበሩዋቸውን ሁሉ በማመስገንና ለሁሉም ጸሎታቸው በማረጋገጥ ማጠቃለላቸው አስታወቀ።








All the contents on this site are copyrighted ©.