2016-04-21 11:25:00

ቅዱስ አባታችን ፍራንቼስኮ "“ልበ ደንዳና እና ወደ ክርስቶስ መቅረብ የማይፈልግ ክርስቲያን አባት እንደ ሌለው ወላጅ አልባ ልጅ ይቆጠራል” ማለተቸው ተገለጸ።


ቅዱስ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳስ ፍራንቸስኮ ዘወትር ጥዋት በቅድስት ማርታ የጸሎት ቤተ መስዋዕተ ቅዳሴ እንደ ምያሳርጉ የሚታወቅ ሲሆን በትላንታናውም ጥዋት ማለትም በሚያዝያ 11,2008 እንደ ተለመደው በርካታ ካህናት እና ምዕመናን በተገኙበት ባደረጉት ስብከተ ወንጌል “ልበ ደንዳና እና ወደ ክርስቶስ መቅረብ የማይፈልግ ክርስቲያን አባት እንደ ሌለው ወላጅ አልባ ልጅ ይቆጠራል” ማለታቸው ተገለጸ።

ከዩሐንስ ወንጌል ከምዕራፍ 10,22-30 ከተነበበው የዕለቱ ምንባብ ለይ ተመርኩዘው እና አይሁዳዊያን ኢየሱስ በየጊዜው የምፈጽማቸውን ታምራትን እና መልካም ተጋባራትን በጥርጣሬ ይመለከቱ እንደ ነበር በማውሳት ስብከታቸውን የጀመሩት ቅዱስነታቸው “እስከ መቼ ልባችንን አንጠልጥለህ ታቆየናልህ? አንተ ክርስቶስ ከሆንህ በግልጽ ንገረን” ብለው መጠይቃቸው የምያሳየው ጻፍቶች እና ፈሪሳዊያን ልባቸው የተዘጋ እና ዓያናቸው ለእምነት የታወረ መሆኑን በተደጋጋሚ በግልጽ ያሳየ ሁኔታ እንደ ነበርም አውስተዋል።

ኢየሱስም “እናንተ ግን በጎቼ ስላልሆናችሁ ብነግራችሁም አላመነናችሁኝም” ማለቱን ቅዱስነታቸው ገልጸው የእግዚአብሔር በጎች ለመሆን ልብን መክፈት ያስፈልጋል ብለኋል።

“በጎቼ ድምጼን ይሰማሉ፣ እኔ አውቃቸኋለው እነርሱም ይከተሉኛል፣ እኔ የዘላለም ሕይወት እሰጣቸኋለው፣ ከቶ አይጠፉም ከእጄ ልነጥቃቸው  የሚችል ማንም የለም” የምለውን የኢየሱስን ቃል በምናይበት ወቅት እነዝህ በጎች ኢየሱስን እንዲከተሉ እና በእርሱ እንድያምኑ ትምህርት ወስደው ነበር ወይ? የሚል ጥያቄ ልያስነሳ ይችላል ብለው፣ እኔ እንደ ምመስለኝ ግን አልተማሩም ምክንያቱም በዝህ ወንጌል እንደ ተጠቀሰው “እነርሱን የሰጠኝ አባቴ ከሁሉም ይበልጣል። ከአባቴ እጅ ማንም ልነጥቃቸው አይችልም” ብሎ ኢየሱስ መመለሱ የምያሳየው እግዚአብሔር አባት ነው እንዚዝህን በጎች  መልካም እረኛ ለሆነው ለእየሱስ በአደራ የሰጠ መሆኑንም ጨምረው ገልጸኋል።

የጻፍቶች እና የፈሪሳዊያን ልበ ደንዳናነት እስከ ኢየሱስ ስቀለት ድርስ የቀጠለ ድራማ መሆኑን በመግለጽ ስብከተ ወንጌላቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው ምንም እንኳን ኢየሱስ ይፈጽማቸው የነበርውን መልካም ሥራ እና ታዓምራትን ቢመለከቱም ወደ ዓለም የተላከ መስሕ መሆኑን ግን ለማመን አልፈለጉም ነበር ብለኋል።

“አስገራሚ ነገር” አሉ ቅዱስነታቸው “አስገራሚው ነገረ ኢየሱስ ሞትን ድል አድርጎ ከተነስ ቡኋላም እንዃን መቃብሩን ይጠብቁ የነበሩ ወታደሮችን ‘እኛ በተኛንበት ወቅት በሌሊት የእርሱ ደቀ መዛሙርት መጥተው የኢየሱስን አስክሬን ሰረቁት ብላችሁ ለሚጠይቃችሁ ሁሉ ንገሩ’” እንዲሉ መምከራቸው ኢየሱስ ከሞት ተነስቱኋል የሚለው የምስክርነት ቃል የማያምኑ ሰዎች ጆሮም እንደ ሚደርስ የምያስረዳ እውነታ መሆኑን አስረድተው ይህም እምነተ ጎዶሎነት የምያሳየው አባታቸው የሞተባቸው ወላጅ አላባ ልጆች መሆናቸውን ነው ብለኋል።

በመጨረሻም “ኢየሱስ የእርሱ ተከታዮች እንድንሆን ይጋብዘናል ብለው ይህንንም ጥሪ ለመመለስ ወደ እግዚአብሔር አባት ፍቅር መቅረብ ወይ መሳብ እንደ ምያስፈልግ ገልጸው ቀለል ባለ ጸሎት “አባታ ሆይ ወደ ኢየሱስ ምራኝ እንዳወቀውም እርዳኝ” ብለን በምንጸልይበት ወቅት እግዚአብሔር አባት መንፈስ ቅዱሱን ልኮ ልባችንን እንዲከፈት እና ኢየሱስን እንድንቀበል ያግዘናል ብለው በአንጻሩም ደግሞ በእግዚአብሔር የማይመራ ማንኛውም ክርስቲያን አባቱ እንደ ሞተበት ወላጅ አልባ ልጅ ስለሚቆጠር ይህንን አስወግደን እግዚአብሄር አባት ወደ ኢየሱስ እንዲመራን መጸለይ ያስፈልጋል ብለው ስብከተ ወንጌላቸውን አጠናቀኋል።

 

 

 

 

 

 

 








All the contents on this site are copyrighted ©.