2016-04-20 16:32:00

Amoris laetitia-የፍቅር ኃሴት ሐዋርያዊ ምዕዳን በቅድስት መንበር ለተለያዩ አገሮች ልኡካነ መንግሥታት በይፋ ቀረበ


ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮ የደረሱት እ.ኤ.አ. ሚያዝያ 8 ቀን 2016 ዓ.ም. በይፋ ለንባብ የበቃው የፍቅር ኃሴት የተሰየመው ሐዋርያዊ ምዕዳን፡ ቤተሰብ ርእስ ዙሪያ የመከረው የኩላዊት ቤተ ክርስቲያን ብፁዓን ጳጳሳት ሁለት ሲኖዶስ ላይ የተመሠረተ ስለ ቤተሰብ ጉዳይ የቤተ ክርስቲያን ሥልጣናዊ ትምህርት ጽማሬ መሆኑ በስፋት መብራራቱ የሚታወስ ሲሆን፡  ይኽ ሐዋርያዊ መልእክት እ.ኤ.አ. ሚያዝያ 19 ቀን 2016 ዓ.ም. በቅድስት መንበር ለተለያዩ አገሮች ልኡካነ መንግሥታና በኢጣሊያ ለሚገኙት ለተለያዩ የዓለም አቀፍ መንግሥታውያን ላልሆኑት ወኪሎች በይፋ መግለጫ እንደተሰጠበት የተካሄደው ዓውደ ጉባኤ የተከታተሉ የቫቲካ ረዲዮ ልኡክ ጋዜጠኛ ማርኮ ጉዌራ አስታወቁ።

በተካሄደው ዓውደ ጉባኤ ሐዋርያዊ ምዕዳኑን በተለያዩ እይኑን የዳሰሰ ማብራሪያ የሰጡት የቤተሰብ ጉዳይ ተንክባካቢ ጳጳሳዊ ምክር ቤት ሊቀ መንበር ብፁዕ አቡነ ቪንቸንዞ ፓሊያና በተባበሩት መንግሥታና ጀነቭ ለሚገኙት በተባበሩ መንግሥታት ድርጅቶች የቅድስት መንበር ቋሚ ታዛቢ ብፁዕ አቡነ ኢቫን ዩርኮቪች መሆናቸው የገለጡት ልኡክ ጋዜጠኛ ጉዊራ አክለው፥

የሰብአዊ ማኅበራት ልኡካን ፍቅር በኃሴት የተሰየመው ሐዋርያዊ ምዕዳን የቤተ ክርስቲያን ሥልጣናዊ ትምህርት ወይንም ፍቅር በተመለከተ በአንቀጸ ሃይማኖት ሥር ያለው ትምህርት የሚቀይር ሳይሆን ያንን ትምህርት በሐዋርያዊ ግብረ ኖልዎ አማካኝነት እግርብ ላይ ለማዋል የሚደገፍ መሆኑ አብራርተው፡ ስለዚህ ስለ ቤተሰብ የሚመለከተው የቤተ ክርስቲያን ትምህርት የማይጨበጥ ረቂቀ ሃሳብ ሆኖ የሚቀር ሳይሆን ተጨባጭ መሆኑ የሚተነትንና በሐዋርያዊ ግብረ ኖልዎ አማካኝነት እንዴት ማቅረብ እንደሚቻል የሚመራ ስልጣናዊ ትምህርት ነው ብለዋል።

ብፁዕ አቡነ ፓሊያ ባስደመጡት ንግግር ቤተ ክርስቲያን ቃል ኪዳን ያለው ምሉእና ጥልቅ ትርጉሙ ከማወጅ አትቆጠብም፡ እንዳውም የቤተሰብ ወንጌ ለወጣት ሙሽሮችና ለትዳር ለሚጠሩት ዜጎች በሚኖሩት ጥሪ ከሁለት ወደ አንድ መሆን የሚሸጋገሩ መሆናቸውን ይኽም አንዱን ሌላውን ሳይጥስና ሳይሰርዝ አንድ መሆን በጋራ ሕይወት በመግለጥ ለኅረተሰብ ክፍት እንዲሆኑና ያንን ቤተሰብአዊ ወንጌል እንዲያበስሩ መጠራታቸው በማነጽ ፍቅር ሃሳብ ብቻ አለ መሆኑ ታስተምራለች ግዴታም አለባት፡ ካሉ በኋላ በተለይ ደግሞ ከጋብቻ ማዶ ያለው ወደ ጋብቻ የሚያበቃው ጥሪና እንዲሁም የጥሪው ዓላማ መቼም ቢሆን እንዳይዘነጋ እንደምታንጽ ሐዋርያዊ ምዕዳኑን በማስደገፍ እንዳብራሩ ጉዌራ ያመለክታሉ።

ብፁዕ አቡነ ዩርኮቪች በበኩላቸውም ቤተ ክርስቲያን ያንን በተለያየ ወቅት የተለያየ ርእዮተ ዓለም መሠረት በማድረግ ለሚከሰተው የቤተሰብ ባህርይ የሚጎዳና በቀላሉም ለሚጠቃው ቤተሰብ የመንከባከቡና የመከላከሉ አገልግሎትዋ ባህርያዊ ነው። ስለዚህ የቤተሰብ ሥነ ሰብአዊ ገጽታው በመከላከልና በማነቃቃት ልዩ ድጋፍ እንደምታቀርብ ይኸው የቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ሐዋርያዊ ምዕዳን ያረጋግጠዋል እንዳሉ የገለጡት ልኡክ ጋዜጠኛ ጉዌራ አክለው፥ ቤተሰብ የሚያጋጥመው ችግር ለቤተ ክርስቲያንና ለማኅበረሰብ አቢይ ተጋርጦ መሆኑ በተካሄደው ዓውደ ጉባኤ የተሳተፉት የአንዳንድ አገሮች ልኡካነ መንግሥታት በሰጡት አስተያየትና ባቀረቡት ጥያቄ የተሰመረበት ሲሆን ይኽ ደግሞ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. የደረሱት ሐዋርያዊ ምዕዳን ከኵላዊት ቤተ ክርስቲያን ውጭ በዓለም አቀፍ መድርኮች ለንጽጽር እንደሚያገለግል የሚያረጋግጥ ሲሆን፡ በቅድስት መንበርና በመንግሥታት መካከል ለሚደረገው ውይይትና ከተለያዩ ኃይማኖቶች ጋር ጭምር ለሚከናወነው የጋራ ውይይትና ግኑኝነት መሣሪያ መሆኑ ብፁዕ አቡነ ዩርኮቪች በማብራራት፡ ምዕዳኑ የቤተ ክርስቲያን የቤተሰብ ባህላዊ ሥነ ሰብአዊ ባህርያዊ ገጽታው ምን ተመስሎው በጥልቀት ተብራርቶ ይገኛል እንዳሉ አስታውቀዋል።

በመቀጠልም የጀነቭ ጉባኤ ሊቀ መንበር ማሪያ ጆቫና ሩጂየሮ ባስደመጡት ንግግር፥ የፍቅር ኃሴት ሐዋርያዊ ምዕዳን በመላ የተለያዩ ካቶሊካውያን ማኅበራትና ድርጅቶች መካከልና አማካኝነትም ለሚከናወኑት ግኑኝነቶች እድል መሆኑ ገልጠው፡ ምዕዳኑ የሚያስተጋባው እሴት እርሱም ቤተሰብ ውህበትና ውህበት መሆኑ ተገንዝቦ ከዚህ ባሻገርም ያለው ማኅበራዊ እሴቱ በመተንተን የኅብረተሰብ መሠረት መሆኑ በጥልቀት የሚያስረዳ ነው እንዳሉ የቫቲካን ረዲዮ ልኡክ ጋዜጠኛ ጉዌራ አመለከቱ።








All the contents on this site are copyrighted ©.