2016-04-19 14:16:00

ቅዱስ አባታችን በቅድስት ማርታ የጼሎት ቤት ስርዓት ቅድሴ ባሳረጉበት ወቅት "መልካም እረኛ ኢየሱስ ብቻ" መሆኑን ገለጹ።


ቅዱስ ርእሰ ሊቃነ ጳጳስ ፍራንቸስኮ ዘወትር ጥዋት በቅድስት ማርታ የጸሎት ቤተ መስዋዕተ ቅድሴ እንደ ምያሳርጉ የሚታወቅ ሲሆን በትላንታናውም ጥዋት ማለትም በሚያዝያ 10,2008 እንደ ተለመደው በርካታ ካህናት እና ምዕመናን በተገኙበት ባደረጉት ስብከተ ወንጌል “የኢየሱስን ድምጽ ብንሰማ እና ብንከተለው የሕይወት መንገድን በፍጹም ልንስት አንችልም” ማለተቸው ተገለጸ።

በዕለቱ የእግዚአብሔር ቃል ከዩሐንስ ወንጌል ከምዕራፍ 10 በተወሰደው ላይ ተመርኩዘው “ኢየሱስ እኔ መልካም እረኛ ነኝ” ያለውን በመጥቀስ ስብከተ ወንጌላቸውን የጀመሩት ቅዱስነታቸው “ወደ ዘላለም ሕይወት የምወስደን መንገድ አንድ ብቻ በመሆኑ ሀብት እና ተመሳሳይ አሳሳች የሆኑ ጉዳዮች ከምያመለክቱን የተሳሳተ ጎዳና ተመልሰን ትክክለኛውን የሕይወት መነግድ መከትል ይኖርብናል” መለታቸውን ጋዜጤኛችን አሌሳንድሮ ጂዝቲ ዘገቡኋል።

“የመግቢያ በር፣ መንገድ እና ድምጽ” በምሉ ሦስት ከዩሐንስ ወንጌል በተወሰዱ ቃላት ላይ ትኩረታቸውን በማድረግ ስብከተ ወንጌላቸውን የቀጠሉ ቅዱስነታቸው እነዝህ 3 ቃላት ለአንድ ክርስቲያን ሕይውት አስፈላጊ መሆናቸውንም ጨምረው ገልጸኋል።

“ኢየሱስ ሁል ጊዜም ቢሆን ሰዎች ይገባቸው ዘንድ ቀለል በሚል አገላለጽ ያስተምራቸው ነበር” ያሉት ቅዱስነታቸው “በእዚያ የነበሩ ሰዎች ሁሉ የአንድ እረኛ ሚና ምን መሆኑን ያውቁ ነበር” ካሉ ቡኋላ “ሁሉም ትክክለኛው እረኛ በመግቢያው በር ብቻ መግባት እንዳለበትም ይረዱ ነበር ብለኋል።

“ነገር ግን በሌላ መስመር መግባት የምፈልጉ ሁሉ ሌቦች ወይንም ወንበዴዎች ብቻ ናቸው” ብለው፣ “እንዲሁም ወደ ኢየሱስ መምጣት የምፈልግ ሁሉ እና ወደ ዘላለማዊ ሕይወት መግባት የምፈልግ ሁሉ መንገዱ አንድ እና እንድ ብቻ ነው ይህም ጌታችን ኢየሱስ የከፈተልን በር ብቻ መሆኑን ልንገነዘብ ያስፈልጋል” ብለኋል።   “የሕይወት በር የምንለው የዘላለም ሕይወትን በር ብቻ ሳይሆን ዕለታዊውንም የሕይወት በርንም ያጠቃለለ መሆን እንደ ሆነም ማወቅ ያስፈልጋል” ብለዋል።

በሁለተኛነትም የተጠቀሰው ቃል “መንገድ የምለው ነው” በማለት ስብከተ ወንጌላቸውን የቀጠሉ ቅዱስነታቸው “መልካም እረኛ በጎቹን ያውቃል ያሰማራቸኋልም፣ ከፊት ለፊታቸው እየተራመደ ይመራቸኋል በጎቹም እርሱን ይከተሉታል” ተክክለኛው መንገድ ይህ ነው “እርሱም ኢየሱስን መከተል ነው” ብለው በየቀኑ በምናደርገው ሕይወት ጎዞ ውስጥ በፍጹም መሳሳት የለብንም “ኢየሱስ ከፊት ሆኖ ይመራናል መጓዝ የሚገባንን መንገድም ያሳየናል” ብለኋል።

“ኢየሱስን የምከተል መንገድ አይሳሳትም! ነገር ግን ብዙን ጊዜ ነግሮችን አጥርተን መመልከት ይከብደን ይሆናል። ኢየሱስ ያሳየንን መንገድ ትተን በሌላ፣ እርሱ በማይፈልግበት መንገድ እንጓዛለን። ዓልም በምያሳየን ጎዳና መመላለስ እንደልጋለን”፣ በማለት ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው “ይህንንም የዓልም ፍላጎት ብቻ በምንፈጽምበት ወቅት ኢየሱስን መከተል እናቆማለን በትክክለኛው መገድ ላይ ሳይሆን እየተጓዝን የምንገኘው በተሳሳተ ጎዳና ላይ ስለሆን መሳሳተችን ተረድተን መመለስ ይጠበቅብናል በለኋል ቅዱስነታቸው።

በሦስተኛነት “መንገድ” የምለውን ቃል በመጠቀም ስብከተ ወንጌላቸን የቀጠሉ ቅዱስነታቸው “በጎቹ ድምጹን ስለ ምያውቁ ይከተሉታል” የምለውን የወንጌል ቃል ተንተርሰው “የኢየሱስን ድምጽ ከሌሎች ማለትም ከወንበዴዎች እና ከሌቦች ድምጽ መለየት የምንችለው በመጀመሪያ ኢየሱስ ባስተማረን መሰረት እርካታን በምያስገኘው መነግድ ላይ መራመድ ስንችል ብቻ ሲሆን በሁለተኛነትም የኢየሱስን ድምጽ ከሌሎች መለየት ከፈለግን ምሕረት ያምያሳይ ተግባራትን ስንፈጽም እንዲሁም በሦስተኛ ደረጃ ኢየሱስ ያስተማረንን አባታችን የምለውን ጸሎት በማስተዋል በምንደግምበት ጊዜ ሁሉ የኢየሱስን ድምጽ መለየት እንችላለን በለኋል ቅዱስ አባታችን።

በመጨረሻም የክርስቲያን ሕይወት በጣም የተወሳሰብ ሕይወት አይደለም ብለው፣ በር የሆነ ኢየሱስ ወደ መልካም መንገድ እንዲመራን እና ድምጹን መለየት የምያስችለንን መልካም እና የምሕረት ተግባራትን ማከናወን ይጠበቅብናል ብለው በድጋሜ እንድታስታውሱ የምፈልገው ነገር ኢየሱስ በር፣ መንገድ እና ድምጽ መሆኑን በመረዳት እርሱ ብቻ መልካም እረኛ የምያደርገን፣ መልካሙን ጎዳና የምያሳየን  እንዲሁም እድማጮች እንድንሆን የምያስተምረን በመሆኑ እነዝህን ነገሮች በሕይወታችን መተግበር እንድንችል የረዳን ዘንድ መጸለይ ይገባናል ብለው ስብከተ ወንጌላቸውን አጠናቀኋል።

 

 

 

 

 

 








All the contents on this site are copyrighted ©.