2016-04-18 16:37:00

ቅዱስነታቸው ልኂቅ ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16 ሰማንያ ዘጠኛውን ዓመት እድሜያቸውን አከበሩ


ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮ እ.ኤ.አ. ሚያዝያ 16 ቀን 2016 ዓ.ም. ወደ ግሪካዊቷ ደሴት ለስቦ ለሐዋርያዊ ጉብኝት በተነሱበ ቀን የቅዱነታቸው ልኂቅ ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ የወለዱበት ቀን መሆኑ በማስታወስ ስለ ቅዱስነታቸው ልኂቅ ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ ሁሉም እንዲጸልይ አደራ በማለት መልካም የልደት ቀን ተመኝተው መላ ቤተ ክርስቲያን ስለ እርሳቸው ትጸልይ ዘንድም ማሳሰባቸው የገለጠው የቅድስት መንበር መግለጫ አክሎ፥

ለእኚህ 89ኛውን ዓመት እድሜያቸውን ላከበሩት ቅዱስነታችው ልኂቅ ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ ክብር እ.ኤ.አ. ሚያዝያ 16 ቀን 2016 ዓ.ም. በሮማ ሰዓት አቆጣጠር ከምሽቱ 6 ሰዓት በፍራንክፈርት የሙዚቃ ጓድ የተመራ በአገረ ቫቲካን ሊዮነ አስራ ሦስተኛ ሕንጻ በሚገኘው የጉባኤ አዳራሽ የሞዛርት ጥዑም የሙዚቃ ቅኝት መቅረቡንም ገልጦ፡ በሳቸው ስም የሚጠራው የባህል ማኅበር ባሰራጨው መግለጫ ሁሉም ለኚህ የእምነት መስካሪ አባት እንደሚጸልይ በመታመን ከሁሉም ከተለያዩ የኃይማኖት መሪዎችና አበይት የቤተ ክርስቲያንና የፍትኃ አካላት የመልካም ልደት መግልጫ መልእክት እንደደረሳቸውም ይጠቁማል።








All the contents on this site are copyrighted ©.