2016-04-13 16:20:00

ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ.፥ በተፈራረቅ እየተካሄደ ያለው የዓለም ጦርነት የሚወገደ በምኅረት መንፈስ ብቻ ነው


ከጳጳሳዊ የፍትሕና የሰላም ምክር ቤት ጋር በመተባበር በዓለም ሰላም የሚያነቃቃው ሰላመ ክርስቶስ የተሰየመው ዓለም አቀፍ ማኅበር፥ ዓመጽ ይወገድ፥ ቅን ሰላም፡ ካቶሊካዊ ግንዛቤ የሚሰጠው አስተዋጽዖና የኢአመጸኝነት ጥረት በሚል ርእስ ሥር ባዘጋጀው እዚህ ሮም በመካሄድ ላይ ወዳለው ዓለም አቀፍ አውደ ጉባኤ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ በሰዎች መካከል ግኑኝነት ዕርቅ በሕዝቦች መካከል ፍትሕ እንዲረጋገጥ በሚደግፍ አገልግሎት መትጋት የተሰኙት እሴቶች በዓለማችን በተፈራረቅ እየተከሰተ ላለው አስከፊው የዓለም ጦርነት መትሔ መሆኑ የሚያብራራ መልእክት ማስተላለፋቸው የቫቲካን ረዲዮ ልእክት ጋዚጠኛ ጋብሬላ ቸራዞ አስታወቁ።

በዓለም የሚታየው የተወሳሰበ ኑሮና ዓመጽ እጅግ አቢይ በመሆኑ ሰላም የሚያነቃቁ አካላት የሚጠበቅባቸው ኃላፊነት በገዛ እራሳቸው በሚኖሩት የኢአመጸኝነት ተመክሮ የሚሸኝ መሆን አለበት ያሉት ቅዱስ አባታችን፥ በእርግጥ ይህ ዓይነቱ አገልግሎት አድካሚ ቢሆንም ቅሉ የጋራ ጥቅም በመሻት ምሉና ዓይነተኛ የጦር መሣሪያ ቅነሣ እንዲረጋገጥ ፍራቻን መዋጋት ቅንና ግልጽ የእርስ በእርስ ውይይት ገቢራዊ ማድረግ ያስፈጋል። ካለን ልዩነት የሚንደረደር የጋራ ውይይት የጋራ ጥቅም ለማረጋገጥ መሠረት በመሆኑ የሚደረሰው የጋራ አካፋይ የሆነው ስምምነት በጽናት ማቀብ ያለው አስፍላጊነት እንዳሰመሩበት ቸራዞ ያመልክታሉ።

ሰላመ ክርስቶስ ዓለም አቀፍ ማኅበር በዓለም ሰላም ለማረጋግጥ የሚሰጠው አወንታዊ አስተዋጽዖ ፍትህ ሰላም የተሰኙት የሰዎች ሁሉ አስተንፍሶዎች እውን ለማድረግ እንደ ማንኛውም የማስተግበሪያ መሣሪያ ሁሉ መታደስ ይኖርበታል። ጥበብ የተካነው ዲፕሎማሲ እርሱም የሃገራት የሥን ግኑኝነት ሥልት ጥበብ የተካነው ጥረት አለ ምንም ማመንታት በሙሉ አቅም መደገፍ ይኖርበታል፡ ባለፈው ዘመን ሰላመ ክርስቶስ ማኅበር የመሠረተውና እንዲሁም ጳጳስዊ የፍትሕና ሰላም ምክር ቤት የተለያየ ርእዮተ ዓለም በሚከተሉና በፖለቲካዊ በማኅበራዊ እንዲሁም በኤኮኖሚያዊ ዓለም ፍትህ እንዲረጋገጥ በሰዎች መካከል ግኑኝነት በሕዝቦች መካከል እርቅ እንዲኖርና ሰላምና ፍትህ ለማነቃቃት ታልሞ ነው። ምክንያቱም ይኽ መንገድ ብቻ ነው በዓለም የሚታየው ተፈራረቅ ጦርነት ለማስወገድ የሚቻለው።

አመጾች ችላ ሊባሉና ወይንም እንደሌሉ ደብቆ መኖርና ሸፋፍኖ ማለፍ አይቻልም

ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራቸስኮ ባስተላለፉት መልእክት ለተጋባእያኑ የሰው ልጅ በጠቅላላ የማኅበረሰብ ግብ ጦርነት ጨርሶ እያንዳይኖር የሚል መሆኑ በመግለጥ ወደዚያ አለ ጦርነት ወደ ሚለው ግብ ለመደረስ አመጾችን ችላ ማለትና ወይንም መደበቅ አያስፈልግም። በአመጽ ተነክሮ ላለ መቅረት አመጽ እንዳለ አስተውሎ የሁሉም የወደፊቱ ዕጣ እድል ሰላም መሆኑ ተገንዝብ አመጽ እንዲፈታና ሰላም ህዝቦችን የሚያገናኝ ቀለበታዊ ሰንሰለት ሆኖ በሁሉ ዘንድ እንዲሰርጽ የሰላም መሣሪያ የሆኑት ሰዎች የሚያካሂዱት ጥረት ያንን ግብ ለመጨበጥ የሚል መሆን ይገባዋል በማለት አበረታተው፥

ወንድማማችነት ማረጋገጥና ግድየለሽነት መዋጋት

እንደ ክርስቲያን መጠን ማንኛው አምሳያችን የሆነው ሁሉ እንደ ወንድም ለማየት ሲቻል ብቻ ነው ጦርነቶችና ግጭቶች ለማስወገድ የሚቻለው። በአሁኑ ሰዓት ይኸንን ዓላማ እያሰናከለ ያለው ሰው የሚገነባው ለያዩ የግድየለሽነት የግንበ አጥር መሆኑ ጠቅሰው። በእውነቱ ይኽ ደግሞ በጣም የሚያሳዝን ተግባር ነው። የዚህ የክፍት ተግባር ተጠቂ የሚሆነውም ሰው ብቻ ሳይሆን መላ ፍጥረትና ተፈጥሮም ጭምር ነው። ጥረቱም የዚህ ዓይነቱ የግድየለሽነት ተግባር ለመቅረፍ መሆን እንደሚገባው ቅዱስነታቸው አበክረው ይኽ የሚከወነውም ልክ በሰማይ እንዳለው አባታችን መኃሪያን በመሆን ብቻ ነው። በፖለቲው ቋንቋ ምኅርት የሚባለው ቃል መተባበር በሚል ቃል የሚገለጠው ሲሆን፡  በዚህ በተገባው የምኅረት ዓመት ቅዱስነታቸው ከተለያዩ መራሔ መንግስታትና ርእሰ ብሔሮች ጋር በተለያየ ወቅት ባካሄዱዋቸው ክሌአዊ ግኑኝንቶች የሞት ፍርድ እንዲሻርና ለበዳዮች ይቅርታን መስጠት የድኾች አገሮች የብድር ጫና መሰረዝ ካልሆነም ተቀባይነት ባለው ደንብ ማስተዳዳር የተሰኙት ተግባሮች እንዲያረጋገጡ የሚያስተላልፉት መልእክት በመካሄድ ላይ ባለው ዓውደ ጉባኤ መስተጋባቱንም የቫቲካን ረዲዮ ልእክት ጋዜጠኛ ቸራዞ ያመልክታሉ።








All the contents on this site are copyrighted ©.