2016-04-11 16:48:00

የቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. የዓለም አቀፋዊ ሐዋርያዊ ጉብኝት መርሓ ግብር


ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ የሁሉም አርመናውያን ፓትሪያርክ ኩላዊ የበላይ መንፈሳዊ መሪ ቅዱስነታቸው ካረኪን ዳግማዊ፡ የአርመን ብሔር ማኅበራትና በአርመን የምትገኘው ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን እንዲሁም ባለ ሥልጣናት ያቀቡላቸው ጥሪ ምክንያት ከሰኔ 24 ቀን እስከ ሰኔ 26 ቀን 2016 ዓ.ም. አርመንን እንደሚጎበኙ የቅድስት መንበር የዜናን ኅትመት ክፍል መግለጫ አመለከተ።

በተመሳሳይ መልኩም የመላ ጆርጃ ፓትሪያርክ ኵላዊ የበላይ መንፈሳዊ መሪ ብፁዕ ወቅዱስ ኢሊያ ዳግማዊ፡ የጆርጃና የአዘርበጃን መንግሥታትና የተለያዩ ኃይማኖቶች የበላይ መንፈሳውያን መሪዎችና እዛው የምትገኘው ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ጥሪ መሠረትም  ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ እ.ኤ.አ. ከመስከረም 30 እስከ ጥቅምት 2 ቀን 2016 ዓ.ም. ጆርጃንና አዘርበጃንን እንደሚጎበኙ የገለጠው የቅድስት መንበር የዜናና ኅትመት ክፍል መግለጫ አክሎም አዲሱ የረፓብሊካዊት ማእከላዊት አፍሪቃ ርእሰ ብሔር ፕሮፈሰር ፋዉስቲን አርቻንገ ቱደራ ቅዱስ አባታን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ እ.ኤ.አ. ህዳር 2015 በአገሪቱ  ላካሄዱት ሐዋርይዊ ጉብኝት አመስጋኝ ግብረ መልስ ለማቅረብ ቅድስት መበርን በመጎብኘት ከቅዱሱ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ጋር ለመገናኘት ያላችው መልካም ምኞች ርእስ ያደረገ ያስተላለፉት መልእክት መሠረት እ.ኤ.አ. ሚያዝያ 18 ቀን 2016 ዓ.ም. በአገረ ቫቲካን አቀባበል ተድርጎላቸው ከቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ጋር እንደሚገናኙ በረፓሊካዊት ማእካላዊት አፍሪቃ የሚገኙት የቅድስት መንበር ሐዋርያዊ ልኡክ የሰጡት መግለጫ ጠቅሶ ይፋ በማድረግ ርእሰ ብሔር አርቻንገ ቱደራ የአገሪቱ ርእሰ ብሔር ሆነው በካቲት ወር ከተመረጡ ወዲህ በቅድስት መንበር የሚያካሂዱት ጉብኝት ቀዳሚ ዓለም አቀፋዊ ጉብኝት እንደሚሆን ይጠቁማል።








All the contents on this site are copyrighted ©.