2016-04-11 16:43:00

ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ.፥ በድኾች ሕይወት የማያሳትፍ ምጽዋት ሓቀኛ ምጽዋት ሊሆን አይችልም


እ.ኤ.አ. ሚያዝያ 9 ቀን 2016 ዓ.ም. ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ የምህረት ዓመት ምክንያት በማድረግ ከውስጥና ከውጭ የተወጣጡ ከ40 ሺህ በላይ የሚገመቱ ምእመናን በተገኙበት በአጸደ ቅዱስ ጴጥሮስ በሰጡት ይፋዊ አስተምህሮ፥ ኢየሱስ እንዳስተማረን እርዳታችን ለሚጠይቅ የእኛ ቢጤ  የምንሰጠው ምጽዋ ቅን አሳቢ ቱክረት የተካነ ብቻ ሳይሆን የድኻውን ሕይወት በመሳተፍ የሚሰጥ መሆን አለበት የሚል ሃሳብ ላይ ያነጣጠረ እንደነበር የቫቲካን ረዲዮ ልኡክ ጋዜጠኛ አለሳንድሮ ደ ካሮሊስ አስታወቁ፡

ተደጋጋሚው ግብረ ምጽዋት

ቅዱስ አባታችን የሰጡት አስተምህሮ ዘወትር እምነት በተግባር የሚል መሆኑ የሚታወቅ ሲሆን፡ እርሱም እምነትና ተግባር ያጣመረ ክርስቲያናዊ ሕይወት በቃልና በሕይወት የሚያሳስብና በእውነቱ ምጽዋት ልክ እንደ መጽሐፍ ቅዱስ ጥንታዊ ነው፡ ስለዚህ ሲወርድ ሲዋረድ የመጣ ግዴታዊ ተግባር መሆኑ ገልጠው። ምንም ነገር የሌላቸው ስደተኞች መበለቶች እንዲታወሱና እንዲመጸወቱ ልዩ ትኩረት እንዲደረግላቸው ብሉይ ኪዳን ደጋግሞ ያሳስባናል። በመጽሓፍ ቅዱስ መጽዋት መስጠት የአንድ ግጥም ወይም ዜማ እንደ ሚደጋገም አዝማች ነው። ይኽ ደግሞ እግዚአብሔር ለእኛ ቢጤዎች የምናስብ እንድንሆን የሚያቀርበው የኃልፊነት ጥሪ የሚያስገነዘብ ነው እንዳሉ ደ ካሮሊስ ያመለታሉ።

ለሚሠዋ ፍቅር ዳኞች

ለድኻው ሲመጸወት ውስጣዊ ደስታ በተሞላው መንፈስ መሆን አለበት፡ ምክንያቱም ድኻው በመንገድ እንደ ተጣለ አሰናካይ ድንጋይ ታይቶ ተዘሎ ወይንም እራስ በማሸሽ እያዩ እንዳላዩ ሆኖ የሚታለፍ በመገድ ላይ የተጣለ አሰናካይ ነገር አይደለም፡ ምህረትን መስጠት ሸከም ወይንም አሰልች ተግባር እንደሆነ በማሰብ ከዚሁ ተግባር እራስን ነጻ ለማውጣት መቻኰል አያስፈልግም። ብዙ ሰው ላለ መመጽወቱ ምክንያት በመስጠት ብድኻው ላይ ይፈርዳል። ምጽዋት ብሰጠው ይጠጣበታል። ስለዚህ ባልሰጠው ይሻላል እንላለን። ነገር ግን የተመጸወተለት ወደ መጠጥ የሚሮጠው እኰ ሌላ መንገድ ስላልቀረበለት ነው ብሎ ማሰላሰል ያስፈልጋል እንጂ፡ መፍረድ አያስፈልግም፡ ብዙዎቻችን ማንም ሳያየን ተደብቀን ማድረግ የማይገባ ነገር እናደርግ ይሆናል። እንተ የምትፈርደው ማን ነህ? ማንም በድኻው ላይ የሚፈርድ ዳኛ ለመሆን አልተጠራም። ልትጣጣበት ምጽዋት ትጠይቃለህ በማልት በድኻው ላይ ልንፈርድ ኃላፊነት የሰጠን ማን ነው?

እግዚአብሔር ከእኛ አይኖችን እንደማያርቅ ሁሉ እኛም አይናችን ከድኻው ልናርቅ እንደማይገባን በቅዱስ መጽሓፍ ዘንድ ያለውን መጽሓፈ ጦቢያ ጠቅሰው፡ እግዚአብሔር አይኖቹ ከአንተ እንደማይርቅ ሁሉ እንተም አይኖችህን ከድኻው አታርቅ። ጥበብ የተካነው ቃል። እግዚአብሔር የሚለን የእኔ አይኖች ባንተ ላይ ናቸውና አይህን በእኔ ላይ ብቻ ይሁኑ ሳይሆን፡ በድኻው ላይ እንዲሆን ነው አደራ የሚለን። እግዚአብሔር ገዛ እራሱን ከድኻው ጋር ያመሳስላል። ኢየሱስ እንዳስተማረን ሁሉ አስፈላጌው አስመሳይነት የእዩልኝ ተግባር ሳይሆን ቆም ብሎ እርዳኝ ለሚለው ጊዜ መስጠት ነው፡ በርግጥ ብዙዎቻችን አዎ ይኸንን እንፈጽም ይሆናል። ስለዚህ ምጽዋት ሲባል ሳንቲም ወርውሮ መንገድን ማቅጠን ሳይሆን። ሳንቲም ወርውሮ ከመሮጥ ቆም ብሎ ጎንበስ ብሎ ጉልበትን አጥፎ የድኻውን ልብ ማዳመጥ ምን እንደሚፈልግ ማስተዋል ያስፈልጋል። ማን መሆኑ መጠየቅ ያስፈጋል። ተነጥሎ ተገሎ በድኽነት የሚኖረውን እውነተኛው ድኻ መለየት ያስፈልጋ።

መጽዋት ለእግዚአብሔ የሚቀርብ አቢይ ትእምርት ነው

ምጽዋት መስዋዕትነት ያካተተ እንጂ የተረፈውን መስጠት ማለት እንዳልሆነም ወንጌል ያስተምረናል፡ ያላትን ሁሉ ሰጠች እንደሚለውም ነው፡ ምክንያቱም መስዋዕትነት የሚጠቅ ስለሆነ። የድኻው ሕይወት መካፈልና የድኻው ተመክሮ መኖር ያስፈልጋል። ስለዚህ በድኻው ሕይወት የማያሳትፍ ምጽዋት እውነተኛ ምጽዋት አይሆንም። ይኽ ደግሞ ጌታ ያስተማረው የምጽዋ ትርጉም ነው እንዳሉ ደ ካሮሊስ አስታወቁ።








All the contents on this site are copyrighted ©.