2016-04-08 17:02:00

የአርመን ብሔራዊ ሐዋርያዊት ቤተ ክርስቲያን ለአርመናውያን ቅርበትና ድጋፍ


የአርመን ኦርቶዶክሳዊት ብሔራዊ ሐዋርያዊት ቤተ ክርስቲያን ኩላዊ የበላይ መንፈሳዊ መሪ ፓትሪያርክ ብፁዕ ወቅዱስ ካረኪን ዳግማዊና በሊባኖስ የአርመናዊት ሐርዋያዊት ኦርቶዶክሳዊት ቤተክርስቲያን የቂልቂያ ኩላዊ የበላይ መንፈሳዊ መሪ ፓትሪያክ ብፁዕ ወቅዱስ አርም ቀዳማዊ በዚያ በስታሊን ሥርዓት ምክንያት የአዘርበጃን ክልል እንዲሆን በተደረገው በብዛት አርመናውያን በሚኖሩበት ናጎርኖ ካራባክ ክልል ባለፉት ጥቂት ቀናት በአርመናውያንና በአዘራውያን መካከል በተፈጠርው አለ መግባባት ምክንያት ውጥረትና ግጭት ወደ ሚታይበት ክልል በመሄድ ለአርመን ጸጥታ አስከባሪ ኃይሎችና ለአርትሳክ ሕዝብ ቅርበታቸው ለመመክር በሚቀጥሉት ቀናት ሐዋርያዊ ግቡኝት እንደሚያካሂዱ የቂልቂያ የአርመን ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያን ኵላዊ ፓሪያርክ ያወጣው ይፋዊ መግለጫ የጠቀሰው ፊደስ የዜና አገልግሎት አስታወቀ።

በዚያ ማለትም በናጎርኖና ካራባክህ ክልል ያለው ግጭት ዘጋዊና ፖለቲካዊ መልክ ያለው የሶቪያት ኅብረት መውደቅ ጋር ተያይዞ የተከተለ ሲሆን አዘርበጃን ከሩሲያ በመገንጠል ሉኣላዊነቷ ካወጀችበት ከ 1991 ዓ.ም. ወዲህ በብዛት አርመናውያን በሚኖርበት ክልል ነተደጋጋሚ ግጭት መቀጣጠሉ የሚታወስ ሲሆን። ያ ለ 30 ሺሕ ሰዎች ለሞት የዳረገው በ 1991 ዓ.ም. የተቀጣጠለው ግጭት እ.ኤ.አ. በ 1993 ዓ.ም. በቶክስ አቁም ስምምነ ከተቋጨ በኋላ በዚያ ክልል አወዛጋቢ የድንበር ጥያቄ አማካኝነት አልፎ አልፎ ግጭት እንዳለ ሆነ፡ ባለፉት ቀናት በተቀሰቀሰው ግጭት ሳቢያም 75 ሰዎች የሞት አደጋ እንደደረሰባቸውና ሲነገር። ይኽ እ.ኤ.አ. ሚያዝያ 5 ቀን 2016 ዓ.ም. በቶክስ አቁም ስምምነት አማካኝነት ዳግም እልባት ያገኘው ግጭት የአዘርበጃን ደጋፊ በሆነቸው በቱርክና በሩሲያ መካከል ያለው የሥነ ፖለቲካ መልክኣ ምድራዊ አቀማመጥ ምክንያት ያላባቸው ውጥረት የሚያንጸባርቅ ሊሆን እንደሚችልም የመካከለኛው ምስራቅ የፖለቲካ ጉዳይ አዋቂዎች እንደሚናገሩ ፊደስ የዜና አገልግሎት ይጠቁማል።

ድጋፍማ ትብብር ለናጎርኖና ካራባክ

በናጎርኖና ካራባክ የተከሰተው ግጭት ኩላዊ የበላይ መንፍሳዊ መሪ ብፁዕ ወቅዱስ ካረኪን አዘርበጃን የቀሰቀሰቸው በማለት ማውገዛቸው የገለጠው ፊደስ የዜና አገልግሎት አክሎ በብዙ ውጣ ወረድ የተደረሰው ሰላምዊ ያብሮ ኑሮ ላደጋ የሚያጋልጥ ነው ሲሉ። ብፁዕ ወቅዱስ አርም ቀዳሚማዊ በበኩላቸውም ድርጊቱን በማውገዝ ለዚያች በማኛውም የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት አባል አገር ተቀባይነ እንደ አገር እውቅና ላላገኘችው ለናጎርኖና ካራባኪ ረፓብሊክ ርእሰ ብሔር ባኮ ሳህክያንን ስልክ በመደወል ትብብራቸውን ያመልክታል።








All the contents on this site are copyrighted ©.