2016-04-07 11:58:00

ቅዱስ አባታችን “በክርስቲያን ማሕበረሰብ ውስጥ ሰላም እና መረጋጋትን ማስፈን የሚቻለው በመንፈስ ቅዱስ እርዳታ ብቻ ነው”


በሚያዝያ 5,2016 ቅዱስ አባታችን ፍራንቼስኮ በቅድስት ማርታ የፀሎት ቤት ባሳረጉት ዕለታዊ ስርዓተ ቅድሴ ላይ  “በክርስቲያን ማሕበረሰብ ውስጥ ሰላም እና መረጋጋትን ማስፈን የሚቻለው በመንፈስ ቅዱስ እርዳታ ብቻ ነው” ብለው “በአንፃሩም መንፈስ ቅዱስን ያልሰፈነበት የክርስቲያን ማሕበርሰብ ግን በጥል እና በክርክር የተሞላ” ማሕበርሰብ መሆኑን በስበከተ ወንጌላቸው ማስታወቃቸው ተገለጸ።

“በሐዋሪያት ጊዜ የነበሩ የመጀመሪያዎቹ ክርስቲያኖች በአንድ ልብ እና መንፍስ ይኖሩ እንደ ነበር” ያስታውሱት ቅዱስ አባታችን “ሁሉም እንደ አስፈላጊነቱ ያላቸውን በጋራ በመካፈል በአንድነት በምኖሩበት ወቅት በእኩልነት ላይ የተመሰረት አንድነት እንደነበራቸው እና ይህም አንድነት በሰላም እና በእኩልነት እዲኖሩ እንደ ረዳቸው” በሐዋርያት ሥራ ላይ መጠቀሱን አውስተዋል።

“ሐዋርያት የነበራቸው ሕብረት ዛሬ እንደ ምታየው ማንኛውም ዓይነት ሕብረት ሳይሆን የነበራቸው፣ ነገር ግን  የእነርሱ ሕብረት መሰረቱን ያደረገው ከእግዚአብሔር በተገኘ የመንፈስ ቅዱስ ስጦታ ላይ መሆኑን” ገልፀው “እኛም ሰላም እና አንድነት ልንፈጥር የምንችለው እኛ በፈለግነው መልኩ በምናደርገው ስምምነት ላይ  ተመርኩዘን ብቻ ሳይሆን ዘላቂ የሆነ ሰላም እና መረጋጋት የሚገኘው ከእግዚአብሔር ብቻ መሆኑን ተረድተን ያንን የመንፈስ ቅዱስ ፀጋ ከእግዚኣብሔር ልንጠይቅ ያስፈልጋል” ብለኋል ቅዱስነታቸው።

“አንድነትን የምያሳዩ ሁለት ምልክቶች አሉ” በማለት ስበከተ ወንጌላቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው “ ይህም በቀድሞቹ ሐዋሪያት እና ክርስቲያኖች ሕይወት ውስጥ የታየው ‘አንድ ልብ እና አንድ መንፈስ’ መሆናቸው ስሆን በተለይም ያለቸውን ንብረት ሁሉ በጋራ እንደ አስፈላጊነቱ ይጠቀሙ እንደ ነበረ የምያሳየው አንድነት እንደ ነበራቸው” መሆኑን ገልጸዋል። “በመንፈስ ቅዱስ ላይ የተመሰረተ ሕብረት ወጤታማ የሆነ አንድነትን ይፈጥራል” ብለው “የአንድነት ጠላት እና የብጥብጥ ሁሉ መንስሄ የሆነው ገንዘብ” መሆኑን አስረድተው ይህ የእራስ ወዳድነት መንፈስ ሊወገድ የሚችለው ልክ የመጀመሪያዎቹ ክርስቲያኖች እንደ ፈጸሙት በመንፈስ ቅዱስ በመታገዝ ብቻ መሆኑን አስረድተኋል።

ገንዘብን እና እግዚአብሔርን በአንድነት ማምለክ አስቸጋሪ መሆኑን የገለጹት ቅዱስ አባታችን ፍራንቸስኮ፣ “ገንዘብ የተፈለገው ለሰው ልጆች መገልገያ ይውል ዘንድ እንጂ የስው ልጆች ጌታ ልሆን እንደ ማይገባ” ገልጸው  አንድነትን ልሸረሽር የምሞክር ማንኛውም ነገር ሁሉ ከማሕበረሰብ ውስጥ ልወገድ ይገባል ብለኋል።

“በመንፈስ ቅዱስ ላይ የተመሰረተ ሕብረት ባለበት ቦታ ሁሉ ፍቅር እና ደግነት አለ” ያሉት ቅዱስ አባታችን “ ለተቸገሩት ሰዎች ሁሉ እጃችንን እንዘረጋ ዘንድ መንፈስ ቅዱስ ስለ ምገፋፋን፣ ሕብረታችን መሰረቱን ማድረግ ያለበት በእግዚአብሔር ላይ ብቻ መሆን እንዳለበት አሳስበኋል።

በሁለተኛ ደረጃ በመንፈስ ቅዱስ ላይ የተመሰረተ አንድነት የባሕሪ ለውጥ እንድናመጣ ይረዳናል ብለው “ሐዋርያት በታላቅ ኃይል  የጌታን የኢየሱስ ክርስቶስን ትንሣኤ ይመሰክሩ እና በዝህም ተግባራቸው ሁሉም ደስታ እና ሞገስ ያገኙ ነበር”  ብለው “ምንም ጊዜ ቢሆን በተለያም በቤተ ክስቲያን ውስጥ ይህን መሰል ሕብረት በምኖርበት ወቅት፣ ይህ ሕበረት ኋይል ስለምሰጣቸው ያለ ምንም ፍርሃት ከሞት የተነሳውን ክርስቶስን በታልቅ ደስታ እና ኋይል መመስከር ይችላሉ በማለት ስበከተ ወንጌላቸውን አጠናቀኋል።

 

 

 

 

 

 








All the contents on this site are copyrighted ©.