2016-04-07 15:36:00

ቅ.አ.ፍራንቸስኮ "በመስቀል ላይ ተሰቅሎ ያዳነን ክርስቶስ ግን ለኋጥያታችን ሁሉ ይቅርታን ያደርግልናል"


በታላንትነው ዕለት ማለትም በሚያዚያ 6,2016 በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ሳምንታዊውን እና ቅዱስ ልዩ የምሕረት ዓመትን አስመልክቶ ቅዱስ አባታችን ፍራንቸስኮ የምያደርጉትን አስተምሮ ለመከታተል ለተገኙ ከ40 ሺ በላይ ለሚሆኑ ምዕመናን እና ሀገር ጎብኝዎች “እያንድ አንዱ ሰው የእራሱ ውድቀ እና ሐጥያት ቢኖረውም በመስቀል ላይ ተሰቅሎ ያዳነን ክርስቶስ ግን ለሐጥያታችን ሁሉ ይቅርታን ያደርግልናል” ማለታቸው ተገለጸ።

በመቀጠልም ቅዱስነታቸው “እንደ አንድ ነጉሥ በዙፋኑ ላይ ቁጭ ብሎ መፍረድ ስችል በታላቅ ቅድስና እና ጥበብ ዝቅ ማለትን የወደደው ክርስቶስ፣ በምስቀል ላይ ሳለ ሁሉም ያፌዙበት እንደ ነበረ እና እግዚአብሔር ሆኖ መቆየት ስችል እራሱን ዝቅ አድርጎ ከሰውም በታች እራሱን አዋርዶ፣ ስቃይን ተቀብሎ ምሕረትን ለሁሉም አስገኘ” ብለኋል ቅዱስ አባታችን።

በመቀጠልም ኢየሱስ  “ከሕዝቡ ጋር መገናኘቱ፣ ወንጌልን ማብሰሩ፣ በሽተኞችን መፈወሱ፣ ከተናቁት ጋር መዋሉ እዲሁም ኋጥያተኞችን ይቅር ማለቱን” ዋቢ በማድረግ አስተምሮኋቸውን ቀጥለው በተለይም ደግሞ ትኩረታቸውን ኢየሱስ ተልዕኮውን በይፋ የጀመረው በመጥምቁ ዩሐንስ ጥምቀት ቡኋላ መሆኑን ገልጸው  “እራሱን እነደ አንድ ትልቅ ሰው አድርጎ ለቤተ መቅድስ ማቅረብ ብችልም ይህንን ግን አላደረገም፣ እንደ አንድ ፈራጅ ዳኛ የዳኛን ልብስ ለብሶ መምጣት ብችልም ይህንንም አላደረገም፣ ከሰላሳ ዓመታት የናዝሬት የድብቅ ሕይወት ቡኋላ ከእራሱ ሕዝቦች ጋር ልክ እንደ አንድ ኋጥያተኛ ለመጠመቅ ወደ ዮርዳኖስ ወንዝ መሄዱ እና ከኋጥያተኞች ጋር ለመጠመቅ ቢሰለፍም ምንም ዓይነት እፍረት ግን  አልተሰማውም” በማለት ገልጸኋል።

ነገር ግን “ከጥምቀቱ በኋላ በመንፈስ ቅዱስ ተሞልቶ ወደ ዓለም የተላከ መሲህ  እንደ ሆነ እና የሰዎችን ችግር ለመፍታት እንደ መጣ፣ እንዲሁም ሰዎችን ሁሉ ወደ አንድነት እና ወደ ምሕረት መጋበዝ እንደ ጀመረ” ገልጸው   ነገር ግን ይህ ሁሉ የተፈጸመው “ ከጥምቀቱ ቡኋላ ማስገንዘብ የፈለገው አዳኝ የሆነውን የእግዚኣብሔር ፍቅር ለሁሉም ፍጹም፣ ንጹሕ እና ነጻ በሆነ መልኩ  ለማቅረብ መምጣቱን” ጨመረው አመልክተኋል።

በመቀጠልም “ኢየሱስ የጥላቻን እና የጠላትነትን መንፈስ ሳይሆን ያመጣልን የፍቅርን መንፈስ ነው” በማለት አስተምሮኋቸውን የቀጠሉት ቅዱስ አባታችን “ያመጣልን ታላቅ የሆነ ፍቅር፣ ለሁሉም ክፍት የሆነ ልብ፣ የሚያድነውን ታላቅ ፍቅር” መሆኑን ገልጸው በተለይም ደግሞ “የተናቁትን በማቅረብ እና የእግዚኣብሔርን ምሕረት በመለገስ ድስታን እና አዲስ ሕይወትን እንደ አጎናጸፋቸው የምያሳየው ኢየሱስ ከአባቱ ዘንድ የተላከው ምሕረትን ለሰዎች ሁሉ ለማዳረስ” መሆኑን ገልጸኋል።

“ይህንን የማጣልንን ታልቅ ምሕረት በተግባር ለማሳየት እራሱን በጎልጎታ በመስቀል ላይ እስከ መሰቀል ድረስ የደረሰው ክርስቶስ በተለይም ደግሞ በመጨረሻው ሕይወቱ በመስቀል ላይ ሆኖ ‘አባት ሆይ የምያደርጉትን አያውቁም እና ይቅር በላቸው’ ብሎ መፀለዩ የምያሳየው የፍቅሩን ኋያልነት” መሆኑንም  ቅዱስ አባታችን ጨምረ ገልጸኋል።

“በመስቀልም ላይ በነበረበት ወቅት የሁላችንም ኋጥያት እግዚአብሔር ይቅር ይለን ዘንድ ደሙን በማፍሰስ ለእግዚአብሔር እንደ መስዋዕት አቅርቦኋቸዋል” ያሉት ቅዱስ አባታችን “በዝህም ተጋባሩ ኢየሱስ የሁላችንን ኋጥያት በመስቀል ላይ እንዲደመሰሱ አድርግኋል” በማለት አስረድተኋል።

“እኛ አሁን ማድረግ የሚጠበቅብን ነገር ቢኖር በሚስጢረ ንስሐ ታግዘን እራሳችንን ለእግዚኣብሔር ማቅረብ እና በእርሱ ላይ እምነታችን መጣል መሆን ይኖርበታል” ብለው “ማንኛውንም ዓይነት ከእግዚአብሔር ምሕረት የምያርቀንን ተግባራት በማስወገድ ዘወትር ለእርሱ ታማኝ ሆነን ለመኖር መሞከር ይኖርብናል” ብለው አስተምርኋቸውን አጠናቀኋል።

 

 

 

 

 

 

 

 

 








All the contents on this site are copyrighted ©.