2016-04-06 16:15:00

በማኅበራዊ ዘርፍ የሁሉም ሃይማኖቶች የጋራ ግኑኝነት ባህል ማስረጽ


በተለያዩ ኃይማኖቶች መካከል መቀራረብና መተዋወቅ እንዲኖር በሚል ዓላማ በንጉሥ አብዱላህ ቢን አቡድላዚዝ ስም የሚጠራው በ 2012 ዓ.ም. ከቅድስት መንበር ጋር በመተባበር የተመሠረተው ዓለም አቀፍ ማኅበር በመካከለኛው ምስራቅ በወጣቶች መካከል መከባበር የጸናበት ጤናማ ግኑኝነት እንዲኖር የሚያንጽ የሁሉም ኃይማኖቶች ባህሎች የጋራ ውይይት ማእከል በሃይማኖት ስም የሚፈጸም ዓመጽ ለማስወገድ የሚል ሃማኖት የሰላም መሣሪያ መሆናቸው የሚመሰክርና ይኸንን እውነት ለሁሉም በተለይ ደግሞ ለወጣቱ ትውልድ ለማሳወቅ የሚያገለግል ሲሆን። በዓለም አክራሪያን ኃይሎች የሚነዙትና እያስፋፉት ያለው ጸረ ሰብአዊ ጸረ ሃይማኖታዊ ዓላማ በባህልና በሕንጸት ዘርፍ ለመቃወም በዮርዳኖስ ርእሰ ከተማ አማን ከሊባኖስ ከፍልስጥኤም ከሶሪያና ከዮርዳኖስ ለተወጣጡ 300 ወጣቶች በተለያዩ የመገናኛ ብዙኃን አማካኝነት አክራሪያን የሚነዙት ርእዮተ ዓለም ተገቢ መልስ መስጠ በሚል ርእስ ሥር ማኅበሩ ባዘጋጀው ዓውደ ጥናት መሳተፋቸው ሲር የዜና አገልግሎት አስታወቀ።

በመካሄድ ላይ ያለው ዓውደ ጥናት የመካከለኛው ምሥራቅ ወጣቶች በቀላሉ ባክራሪያን ወጥመድ ውስጥ እንዲገቡ የሚያደርጉዋቸው ምክንያቶች ሁሉ በመለየት አክራሪነት የሚያሰጣቸው ምንም ዓይነት ተገቢ መልስም ሆነ ተስፋም ሊኖር እንደማይችል የመገንዘቡ አቅማቸውን እንዲያበረቱና በርትተው በተራቸው የጽናቱን መንፈስ ለቢጠዎቻቸው ለማሰተላለፍ እንዲችሉ የሚያበቃቸው ሕንጸት እንዲቀስሙ ለማድረግ ያቀደ መሆኑ የሃይማኖቶችና ባህሎች ግኑኝነት ማእከል ጠቅላይ አስተዳዳሪ ፋሃድ ኣቧልናስር መግለጣቸው ያመለከተው ሲር የዜና አገልግሎት አያይዞ ወጣቱ የኅብርተሰብ ክፍል በመገናኛ ብዙኃን አማካኝነት ሰላምና ሰላማዊ የጋራ ኑሮ ለማነቃቃት በሚደረገው ጥረት ተቀዳሚ ሚና እንዲኖረው ለመደገፍም ነው እንዳሉ ገልጠዋል።

በኃይማኖት ስም የሚፈጠረው አመጽ በጋራ ለመቃወም

ይኽ የማእከሉ ጅምር እ.ኤ.አ. በቪየና ህዳር 19 ቀን 2014 ዓ.ም. በኃይማኖት ስም የሚፈጠረው አመጽ በጋራ መቃወም በሚል ርእስ ሥር ባነቃቃው ጉባኤ ተሳትፈው የነበሩት ከመካከለኛው ምስራቅ የተወጣጡ የተለያዩ ኃይማኖቶች የበላይ መንፈሳውያን መሪዎች ሁሉም ኃይማኖቶች የሰላም መሣሪያ መሆናችው ተገንዝቦ ማስገንዘብ በአሁኑ ወቅት በዓለም በተለይ ደግሞ በመካከለኛው ምስራቅ ክልል አገሮች ያለው አስፈላጊነት እንዳሰመሩበት ያስታወሰው ሲር የዜና አገልግሎት አክሎ የሚቀጥሉት አራት ዓውደ ጥናቶች በግብጽ ከዛብ በኢራቅ በቱኒዚያና በኤመሪት አረብ ሊካሄድ በእቅድ መያዙንም የማእከሉ መግለጫ ጠቅሶ አስታውቀዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.