2016-04-05 13:32:00

ንጉሥ ዳዊት በሠራው ኋጥያት ተጸጽቶ ወደ እግዚአብሔር ያቀረበው የመማጸኛ ጸሎት


ቅዱስ አባታችን ፍራንቸስኮ በቅዱስ ጴትሮስ አደባባይ ለተሰበሰቡ መዕመናን እና ሀገር ጎብኝዎች ያስተላለፉት አስተምዕሮ በመዝሙር 51 ላይ ትኩረቱን ያደረገ ስሆን የምያውሳውም “ንጉሥ ዳዊት በሠራው ከፍተኛ ኋጥያት ተፀፅቶ ወደ እግዚአብሔር ያቀረበውን የምሕረት ለቅሶ” የተመለከተ ነበር።

ንጉሥ ዳዊት የፈጸማቸው በደሎች በሁለት ይከፈላሉ። ( 2ሳሙኤል 11)

  1.  የመጀመሪያው የንጉሥ ዳዊት ኋጥያት ነው። ንጉሥ ዳዊት በቤተመንግሥቱ መስኮት አሻግሮ በተመለከት ጊዜ በወንዝ ውስጥ ሁና ሰውነቷን የምትታጠብ ሴት ባዬ ጊዜ በውበቱኋ ተማረክ። መማረክ ብቻ ሳይሆን ሰው ልኮ ማንነቱኋን አጣራ፣ የኦሪዮን ሚስት ቤርሳቤህ እንደሆነችም አረጋገጠ። 

      2. ሁለተኛው የንጉሥ ዳዊት ትልቁ ኋጥያት ደግሞ ኦሪዮን እንዲገደል ሁኔታዎችን ማመቻቸቱ ነበር።

እኛ የዛሬ ክርስቲያኖች ከላይ የተጠቀሰው እና ንጉስ ዳዊት ከፈጸመው በደል ምን እንረዳለን ? ምንስ እንማራለን? የእዝህ ዓይነት ተግባር ፈጽመን እናውቃለን ወይ? እስኪ እራሳችንን እንመርምር የተወደዳችሁ ወንድሞቼ እና እህቶቼ።

በሕይወታችን እያወቅን ስንት ጊዜ ስህተት ፈጽመናል? የፈጸምነውን ስህተት ለመሸፈን በማሰብ ስንት ጊዜ ያከፋ ኋትያት ፈጽመናል?

ማመንዘር ማለት የግድ ከሌላ ሰው ሚስት ጋር ሩካቤ ሥጋ መፈጸም ተደርጎ ሊወሰድ ብቻ አይገባም። እኛ ክርስቲያኖች ለእግዚኣብሔር ብቻ የታጨን ምርጥ ሕዝቦቹ ነን። ስለዝህም ሁል ጊዜ መመላለስ ያለብን እግዚአብሔር በሚፈልገው መንገድ ላይ ብቻ ልሆን የገባል። ይህንን መንፈሳዊ አላፊነታችንን እረስተን፣ ከተቀበልነው ክርስቲያንዊ መንገድ እያወቅን ልክ ንጉስ ዳዊት የሰው ሚስት መሆኑኋን እያወቀ እንዳ መነዘረ ሁሉ እኛም በማወቅ ከእግዚአብሔር መንገድ በማንኛውም ሁኔታ ሸሽተን የምንሄድ ከሆን ለጠራን እግዚአብሔር ታማኝ ባለመሆናችን እና እያወቅን እግዚአብሔር ካሳየን መንገድ ውጭ በመሄዳችን በእግዜብሔር ላይ ተጨማሪ ነገር በማምለካችን በእርሱ ላይ አመንዝረናል ማለት እንችላለን።

ይህንንም ስህተታችንን ለመሸፈን በማሰብ የተለያዩ ያልተገቡ ድርጊቶችን እንፈጽማለን ይበልጡኑ ከእግዚኣብሔር እንርቃለን።

ስንት ጊዜ በምላሳችን ሰውን ገለናል?

ስንት ጊዜ የእኛ ያልሆነውን ነገር የእኛ እንዳልሆነ እያወቅን ተመኝተናል? የመሳሰሉትን ጥያቄዎች እራሳችንን መጠየቅ ይገባናል።

እግዚአብሔር ግን እንደ ሰው አይደለም የተከበራቸሁ  ወንድሞቼ እና እህቶቼ።

“ሐሳቤ እንደ ሐሳባችሁ መንገዴ እንደ መንገዳችሁ አይደለም ይላል እግዚኣብሔር። ሰማይ ከምድር ከፍ እንደሚል መንገዴ ከመንገዳችሁ ሐሳቤ ከሐሳባችሁ እንዲሁ ከፍ ያለ ነው” ይላል እግዚኣብሔር። (ኢሳ. 55,8-9)።

እግዚአብሔር መሓሪ አምላክ በመሆኑ ዳዊት ከገባበት ውጥረት እና ነውር ውስጥ ልያወጣው በማሰብ ነቢዩ ናታንን ነጉሥ ዳዊትን ይገሥጸው ዘንድ ላከው ይለናል 2ሳሙኤል 12 ላይ። እንደ ሰው ያልሆነው እና ሁል ጊዜም ኋጥያት በምንሥራበት ወቅት ወደ ንስሐ የምጋብዘን መሓሪው እግዚአብሔር አማላካችን ስሙ የተመሰገን ይሁን።

ነቢዩ ናታን በታላቅ ጥንቃቄ እና ምሳሌያዊ በሆነ ቋንቋ “በአንድ ከተማ የሚኖሩ ሁለት ሰዎች እንደ ነበሩ እና አንዱ ሀብታም አንዱ ግን ድኻ እንደ ሆነ ገልጾ፣ ድኻው ሰው እንደ እራሱ የምወዳት አንዲት ጠቦት ነበረችው። አንድ ቀን ያ ሀብታም ሰው እንግዳ ወደ ቤቱ በመጣ ጊዜ ከእራሱ ጠቦቶች መኋከል መርጦ ለእንግዳው ከማረድ ይልቅ፣ የድኻውን ሰው አንድ ጠቦት ወስዶ ለእንግዳው አረደለት” በማለት ለዳዊት ነቢዩ ናታን ይተርካል።

ይህ ባለጸጋ ሰው የፈጸመው ድርጊት በጣም ያስቆጣው ንጉሥ ዳዊት ባለጠጋው ሰው ያደረገውን ድርጊት በከፍተኛ ሁኔታ ባወገዘ ጊዜ “ያ ሰው እኮ አንተ እራስህ ነህ። እግዚአብሔር ብዙ በረከት ሰቶህ እያለ የድኻውን የኦርዮን ሚስት መቀማትህ ሳያንስህ ኦርዮንን አስገድልክ” ባለው ጊዜ እንደ ተጸጸተ እና “እግዚአብሔርን  በድያለው” ብሎም በጣም እንዳዘነ መጻሐፍ ቅዱሳችን ይገልጻል።።

እኛም ከእግዚኣብሔር መንገድ እርቀን፣ የእሱን ፍቃድ ቢቻ መፈፀም ሲገባን፣ በእርሳችን ጎዳን ተጉዘን በኋጥያት ውስጥ በምንዘፈቅበት ወቅት እግዚአብሔር በተለያየ ዜዴ ወደ ትክክለኛው መንገድ እንድንመለስ ያደርገናል። ነገር ግን ብዙን ጊዜ ልባችንን እናደነድናለን። ከክፉ መንገዳችን መመለስ ይቸግረናል። በኋጥያት እንደ ተዘፈቅን መኖር እንመርጣለን።

ኋጥያትን በምንፈጽምበት ወቅት የእግዚአብሔር ፀጋ ይርቀናል የተከበራችሁ ወንድሞቼ እና እህቶቼ። የእግዚአብሔር ፀጋ ራቀን ማለት ደግሞ ከሕይወታችን ወስጥ ደስታን፣ ተስፋን እና በረከትን እናጣለን ማለት ነው። ደስታ፣ ተስፋ እና በረከት የሌለው ሰው ምን ዓይነት ሕይወት እንደ ሚኖር መገመት አያዳግትም።

ነገር ግን ኋጥያት በምንሠራበት ወቅት የምናጣውን የእግዚኣብሔር ፀጋ መልሰን መግኘት የምንችለው እግዚአብሔር በተለያየ መንገድ የምያቀርብልንን የምሕረት ጥሪ ተቀብለን እንደ ነብዩ ዳዊት “ በእውነት እግዚአብሔርን በድያለው” ብለን በንስኋ ወደ እርሱ መመለስ ስንችል ቢቻ ነው።

በተለይም በዝህ ባለንበት ቅዱስ የምሕረት ዓመት ቅዱስ አባታችን ፍራንቸስኮ “እኛ ነን እንጂ እግዚኣብሔርን ሆይ ይቅር በለን ማለት የምንታክተው፣ እግዚኣብሔር ግን እኛን ይቅር ማለት በፍጹም ታክቶ አያውቅም” ይሉናል።

ኋጥያት ከእኛ የእግዚአብሔርን ፀጋ ያርቃል። ኋጥያት በጨላማ እንድንጓዝ ያደርገናል። ኋጥያት ደስታችንን ይነፍገናል። ኋጥያት የክፋት ሁሉ ምንጭ በመሆኑ ከወንድም እና ከእህቶቻችን ጋር በሰላም እንዳንኖር ያደርገናል። በጨረሻም ኋጥያት በመከራ እና በፈተና ውስጥ እንድንዘፈቅ በማድረግ ለሕይወታችን ትርጉም እንድናጣ ያደርገናል።

የተወደዳችሁ ወንድሞቼ እና እህቶቼ

ንጉስ ዳዊት በሠራው ኋጢያት ተጸጽቶ አለቀሰ ወደ እግዚአብሔርም መጸጸቱን የሚገልጽ የኋጢያት ኑዛዜ  በመዝሙር 51 ላይ እንደ ተጠቀሰው ወደ  እንዲህ ስል ወደ እግዚአብሔር የመማጸኛ ጸሎት አቀረበ “እግዚኣብሔር ሆይ እንደ ቸርነትህ መጠን፣ ምሕረትን አድርግልኝ እንደ ርኋራሄህም ብዛት መተላለፌን ደምስስ” በማለት እግዚአብሔርን ተማጸነ በሠራውም ኋጥያት ሐዘነ፣ አለቀሰም።

እኛም በኋጥያታችን ተጸጽተን እግዚአብሔር ሆይ አንተን በድያለው እና ማረኝ ብለን ብንማጸነው እግዚአብሔር ይቅርታን ያደርግልናል ኋጥያት በሰራንበት ወቅት ያጣነውን ፀጋ እና የልጅነት መንፈስ መልሶ ያጎናጽፈናል፣ እግዚአብሔር ሁል ጊዜም መኋሪ አምላክ ነው እና።

ከኋጥያቱ ለመውጣት የምሞክረውን ሰው ሁሉ እግዚኣብሔር በመንፈሱ ያግዘኋል፣ ከኋጥያቱ እንዲነጻም ያደርገኋል። ባለንበት የጾም ወቅት እና ቅዱስ ልዩ የምሕረት ዓመት የእግዚአብሔርን ፀጋ እና ምሕረት የምንለምንበት ወቅት እንዲሆን ያስፈልጋል።

ቅዱስ አባታችን ፍራንቸስኮ በአስተምዕርኋቸው “ኃጢያተኛ ሰው ከውድቀቱ እስክነሳ ድረስ እግዚአብሔር ዘወትር በትዕግስ ይጠባበቃል” ማለታቸው ይታውቃል። በተጨማሪም “እኛ ከምንገምተው በላይ የእግዚአብሔር ምህረት ዘወትር ሰፊ ነው። እግዚአብሔር በእኛ ወስጥ ያለውን ኋጥያአት ነቅሎ እንድያስወግድ ከፈለግን እኛም ወንድሞቻችንን እና እህቶቻችንን ይቅር ማለት ይጠበቅብናል” ማለታቸውም ያታወሳል። ይህ የምያሳየው እኛ የቅር ካለትባባልን እግዚኣብሔርም እኛን ይቅር ሊለን አይችለም ማለት ነው።

ቅዱስነታቸው “አንድ ሕፃን ልጅ በእናቱ ወይም በአባቱ እቅፍ ታግዞ ለመነሳት እንደ ሚሞክር ሁሉ ከውድቀቱ ለመነሳት የምፈልግ ማንኛውንም ኋጥያተኛ እንደ እናት እና እንደ አባት ደግ የሆነ አምላካችን ከወደቀበት የኋጥያት ጎዳና ለመነሳት የምጥረውን ኋጥያተኛ ልያነሳ ሁሌም ዝግጁ ነው” ማለታቸውም ያታወሳል።

ቅዱስ አባታችን በያዝነው ዓምት እየተከበረ ባለው ልዩ የምሕረት ኢዩበሊዩ ዓመት ምክንያት በማድረግ የምያስተላልፉኋቸው መልዕክቶች በአብዛኛው ምሕረትን የተመለከተ ስሆን ይህም የምያሳየው መኋሪ ወደ ሆነው እግዚኣብሔር ሁል ጊዜ ያቅርታን ያድረግልን ዘንድ መቅረብ እንደ ሚገባን ለማሳአብ ፈልገው ጭምር ነው።

በተለይም አሁን በምንገኝበት የፃም ወቅት ለሰራናቸው ስህተቶች ሁሉ ከእግዛኣብሔር ምሕረትን የምንለምንበት ወቅት ሊሆን ይገባል። ሳንፈራ አባት ወደ ሆነው እግዚአብሔር ይምረን ዘንድ ወደ እርሱ መጓዝ እንድንችል የደካሞች ሁሉ ረዳት በሆነችው በእናታችን በቅድስት ማሪያም አማላጅነት እንለምናለን።

አሜን።

 

 

 

 








All the contents on this site are copyrighted ©.