2016-04-04 15:39:00

"ፍቅር እና ደስታ" በሚል አርዕስት የተጻፈው እና ፍቅር በቤተስብ ውስጥ ስለ ምጫወተው ከፍተኛ ሚና የሚዳስስው ሐዋሪያዊ ምዕዳር በሚያዚያ 8.2016 ይመረቃል።


“Amoris  laetitia” ፍቅር እና ደስታ በሚል አርዕስት የተጻፈው እና ፍቅር በቤተስብ ውስጥ  የሚጫወተውን ከፍተኛ ሚና የምዳስስው ሐዋሪያዊ ምዕዳር በሚያዚያ 8.2016 በቅድስት መንበር የዜና እና የህትመት ክፍል በይፋ ለንባብ እንደ ሚበቃ ታወቀ።

ቀደም ስል በ2014 በተዘጋጀው እና ትኩረቱን በቤተሰብ ዙሪያ ስለ ሚካሄደው ሐዋሪያዊ ሥራ እና ተግዳሮቶች የምያውሳው ልዩ የጳጳሳት ጉባሄ የመነጋገሪያ አርስት ሆኖ ቀርቦ የነበረው እና በተጨማሪም ከዓለም ዙሪያ የተውጣጡ ከ190 በላይ ጳጳሳት የተሳተፉበት እና በጥቅምት ወር 2015 በተካሄደው መደበኛ የጳጳሳት ጉባሄ ላይ ለውይይት የቀረበው የቤተስብ ተልዕኮ እና ጥሪ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ እና በአለንበት ዓለም በምል አርስት ላይ ትኩረቱን አድርጎ የነበረው በቅዱስ አባታችን ፍራንቸስኮ የተዘጋጁ ሐዋሪያዊ ምዕዳር እና በሁለቱ ጉባሄዎች የተካሄዱትን ውይይቶች ያሰባሰበ እና የተውሰኑትን ውሳኔዎች እና የተላለፉትን መመሪያዎች ያካተም ሐዋሪያዊ ምዕዳር እንደ ሆነም ታውቁኋል። 

በእዝህ ሐዋሪያዊ ምዕዳር ምረቃ ወቅት ብፁዕ ካርዲናል ሎሬንሶ ባልዲሴሪ የብፁዕን ጳጳሳት ጉባሄ የበላይ ጸሐፊ እና ካርዲናል ክሪስቶፍ ስኮንቦርን የቬና ሊቀ ጳጳስ እንደ ሚገኙ የታወቀ ስሆን በተጨማሪም በትዳር ሕይወት ውስጥ የሚኖሩ ተጋባዥ እንግዶችም በዕለቱ የሕይወት ምስክርነት እንደ ምሰጡም ታውቁኋል።

ይህ በቅድስ አባታች የተዝጋጀው ሐዋሪያዊ ምዕዳር ከእዝህ በፊት የተካሄዱትን እና ትኩረቱን ባለንበት ወቅት በቤተሰብ ሕይወት ውስጥ ስላለው ደስታ እና ተግዳሮቶች ትኩረት አድርጎ ተካሂደው የነበሩ ሁለት የጳጳሳት ጉባሄዎች ማጠቃለያ ስሆን ስለ ቅድመ ጋብቻ ዝግጅት፣ በቤተሰብ ሕይወት ውስጥ ስለሚፈጠሩትን ግጭቶች እና ጥቃቶችን የምዳስስ እና ሐዋሪያዊ መፍትሄዎችን የሚጠቁም ሐዋሪያው ምዕዳር እንደ ሆነም ለመረዳት ተችሉኋል።

 

 

 

 

 

 

 

 

 








All the contents on this site are copyrighted ©.