2016-04-04 16:35:00

ብፁዕ ካርዲናል ቫሊኒ፥ ለሮማ ከተማ አቢይ ጸጋ


እ.ኤ.አ. ሚያዝያ 2 ቀን 2016 ዓ.ም. የንኡሳን ማኅበረ ክርስቲያን ተጓዦች በሮማ ከተማ በተለያዩ 100 ጎዳናዎች አስፍሆተ ወንጌል ማካሄዳቸው የቫቲካን ረዲዮ ልኡክ ጋዜጠኛ ሚሸለ ራቪያርት ገለጡ።

በዚህ ከእግዚአብሔር ጋር መገናኘት በሚል ርእስ ሥር ተመርቶ በተካሔው ሐዋርያዊ ግብረ ኖልዎ ቃለ እግዚአብሔር በማስተላለፍና በቃል ብቻ ሳይሆን ከእግዚአብሔር ጋር በኢየሱስ ክርስቶስ አማካኝነት የሚጸገወው ግኑኝነት ብሎም ከኢየሱስ ጋር መገናኘት ከወንድም እህት ባለእንጀራ ጋርና ከእራስ ጋር ለሚኖረው እውነተኛው ግኑኝነት መሠረት መሆኑ የንኡሳን ማኅበር ክርስቲያን ተጓዦች የሰጡት ምስክርነት የሮማ ሰበካ ኅየንተ ብፁዕ ካርዲናል አጎስቶኖ ቫሊኒ መርሃ ግብሩ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ልክ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከእኛ ጋር ለመገናኘትና የእግዚአብሔርን የማዳን እቅድ ሊያረጋግጥልን ከገዛ እራሱ ወጥቶ ወደ እኛ እንደመጣ ሁሉ ከገዛ እራስ ተወጥቶ ወደ የከተሞቻችንና የህልውና ጥጋ ጥግ ክልሎች በመውጣት ወንጌልን በቃልን በሕይወት እንዲበሰር አደራ በማለት የሚያስተላልፉት ጥሪ የተከተለ መሆኑ ስለ መርሃ ግብሩ በማስመልከት ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ ገልጠዋል።

በተለይ የተገናኘኸው ክርስቶስ ማበሰር በእውነቱ በምትሰጠው ምስክርነት አማካኝነት ሌላውን ወደ ክርስቶስ እንዲቀርብና በክርስቶስ እንዲማረክ ለማደግ ያግዛል። ጸጋም ነው፡ መለወጥ ጸጋ ቢሆንም ቅሉ የተለወጠ ሁሉ ለለውጥና ለህዳሴ መሣሪያ ሆኖ ሲገኝ በከተሞቻችን የመለወጥ ጸጋ ሲበዛ ገዛ እራሳችንን አድሰን ከተማችንና የከተማ ነዋሪው ሁሉ እንዲታደስ ይደግፋል ከተሞቻችን ደግሞ ሰብአዊ ልክነት እንዲኖራቸው ያግዛል ብለዋል።

ክርስትናችን አሳማኝ የሚሆነው እኛ ክርስቲያኖች የሚኖረን ክርስትናዊ ሕይወት አቢይ ሚና አለው። እምንት ጸጋ ነው። ሆኖም ታማኝ የእምነት መስካሪያን ማለትም የቀደምት ክርስቲያኖች አብነት በመኖር የሚመሰክረው እምነት ታማኝ ነው። በዚህ በምኅረት ዓመት ከእግዚአብሔር ርቆ ለሚኖር ሁሉ የእግዚአብሔር ምኅረት በማበሰር ቤተ ክርስቲያን የዚህ ምኅረት ቅድስት መሣሪያና እናት መሆንዋ ማሳወቅ የሁሉም ክርስቲያን ጥሪ ነው። በዕለታዊ ሕይወት ክርስትናን መኖር አስፍሆተ ወንጌል ነው በማለት ያካሄዱት ቃለ ምልልስ አጠቃለዋል።   








All the contents on this site are copyrighted ©.